በታችና ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ የወያኔ ጦር አባላት ተገድለዋል

በታችና ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ የወያኔ ጦር አባላት ተገድለዋል
ከትናንት ጀምሮ በታችና ምዕራብ አርማጭሆ የተለያዩ አካባቢዎች የዐማራውን መሣሪያ መቀማት በሚል የወያኔ ጦር በዐማራው ገበሬ ላይ ይፋ ጦርነት ገጥሟል፡፡ በታች አርማጭሆ ዶጋው አካባቢና በምዕራብ አርማጭሆ አብደራፊ አካባቢ ከ50 በላይ የወያኔ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡
አበራ ጎባው እና ደጀኔ ማሩ የተባሉ አርበኞችን ቤት በድንገት በመክበብ ለመግደል ሙከራ ያደረገ ቢሆንም በአካባቢው ተሰልፎ የነበረው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ መውደሙን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ አንድ አርበኛ ከዶጋው አካባቢ ጉዳዩን አስመልክተን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹የዛሬው ከበድ ያለ ጦርነት ነበር፤ 8፡00 አካባቢ መጥተው የደጀኔ ማሩን ቤት ከበው ለማፈን ባደረጉት ሙከራ የወያኔ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ አመድ ሆነዋል›› ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የሞቱ የጠላት ወታደሮችን በተመለከተ ደግሞ ‹‹ኧረ የሚሞተውን ወታደር በተመለከተማ ስንቱን ቆጥረነው! በየጫካው አይደል ተፈንድሶ ተፈንድሶ የምታገኘው! እንዴው ገምት ካልከኝ አሳንሼ ቁጥሩን ከ50 ይበልጣል›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በጎንደርና በጎጃም የዐማራ አካባቢዎች በተወሰነ መልኩ ሰላማዊ የሆነ ቢመስልም ወያኔ የገበሬውን መሣሪያ እቀማለሁ በማለቱ ምክንያት እንደገና ሰላሙ ደፍርሷል፡፡ በሰሜን ጎንደር የአርማጭሆ፣ የጠገዴና የወልቃይት አካባቢዎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩን ነው ምንጭቻችን የሚገልጹት፡፡
የመሣሪያ ትጥቅን ማስፈታት በተመለከተ በወያኔ መንግሥት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በዋናነት የአርማጭሆና የወገራ አካባቢዎችን ቁጥር አንድ አድርጎ ፈርጇቸዋል፡፡

ጀግናው አርበኛ አበራ ጎባው በዛሬው እለት በተደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ ብቻውን ከ15 በላይ የወያኔን ወታደር ገድሎ እንዲሁም ከትግል አጋሮቹ ጋር በመሆን ከ55 በላይ ወታደሮችን በገደለበት የትግል ውሎ ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 7፡30 ድረስ በከፍተኛ ተጋድሎ ወጊያውን ሲመራ ከቆየ በኃላ በጀግንነት ተሰውቷል፡፡ ይህ ጀግና ጣጋይ ይሞታል እንጂ ትግል ግን አይሞትም በሚል መርህ ያነፃቸው የተግል ጓዶቹ እሱ ቢሰዋም ተጨማሪ ጥቃት በማድረስ በወጊያ ላይ ናቸው ፡፡ ይህ አርበኛ ለ15 አመት ያህል የወያኔን የማፊያ ቡድን በቆራጥነት ሲታገልና ሲያታግል ከቆየ በኃላ በታላቅ ጀግንነት በዛሬው እለት ተሰውቷል ፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to በታችና ምዕራብ አርማጭሆ አካባቢዎች በተቀሰቀሰ ግጭት ከ50 በላይ የወያኔ ጦር አባላት ተገድለዋል

 1. Ras Dejen says:

  Ethiopians have no ear and fear to the TPLF gang. No, everyone should use any tool to trim off (kill) any TPLF or its core servant. Our traditional which were also used to vanquesh colonial aggressors can be used trim off the TPLF gang:
  – swords
  – shields
  – spears
  – bows
  – arrows
  – slingshots,
  – rolling boulders
  – etc
  can be used against TPLF and its core servants.

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: