የኃይለማሪያም ደሳለኝን የዛሬ ውሸት በትኩሱ ሲጋለጥ ***

በዛሬው እለት አቶ ኃይለማርያም አስገራሚ ውሸት ተናግሯል። በ2007 አም በተደረገው ምርጫ 49% የሚሆነው ኢትዮጵያዊ ለተቃዋሚ ፖርቲ ድምፅ የሰጠ ቢሆንም በምርጫ ሕጋችን ምክንያት የዚህ ሁሉ መራጭ ድምፅ በፓርላማ ሊወከል አልቻለም ብሏል። ይህ ፍጥጥ ያለ ውሸት ነው። የራሱ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ በ2007 አም የተደረገውን ምርጫ ውጤት በገለፀበት ሪፖርት ላይ ኢህአዴግ በትግራይ በአማራ በኦሮሚያ በደቡብ ክልል በሃረሪ በድሬዳዋ እና በአዲስ አበባ ተወዳድሮ ዋጋ ካለው 33,201,969 ድምጽ ውስጥ 27,347,332 (82.4%) ድምጽ በማግኘት በሁሉም አሸንፏል በማለት አስታወቆ ነበር። ቀሪውን ደግሞ አጋር ድርጅቶች ማሸነፋቸውን ገልፆ ነበር።

በክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ደግሞ :-

1. በትግራይ ህወሓት/ኢህአዴግ 2,374,574 (99.39%) ድምጽ በማግኘት 152 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

2. በአፋር ክልል 9 አብዴፓ 817,107 (99.8%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 93 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል, አህዴድ 8253 (97.17%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 3 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

3. በአማራ ክልል 13 ብአዴን/ኢህአዴግ 7,314,564 (96.92%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 294 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

4. በኦሮሚያ ክልል ኦህዴድ/ኢህአዴግ 10,877,190 (93.12%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 537 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

5. በኢ/ሶማሌ ክልል ኢሶህዴፓ 2,621,088 (99.97%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 273 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

6. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቤጉህዴፓ 222,790 (81.03%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 99 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

7. በደ/ብ//ህ ክልል ደኢህዴን/ኢህአዴግ 5,836,849 (93.74) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 345 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

8. በጋምቤላ ክልል ጋህአዴን 195,335 (100%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 155 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፣

9. በሃረሪ ክልል
· ሐብሊ 19791(50%) ድምጽ በማግኘት በተወዳደረባቸው 18 ወንበሮች በሙሉ አሸንፏል፡-
· ኦህዴድ/ኢህአዴግ 84097 (50%) ድምጽ በማግኘት በሙሉ አሸንፏል ተብሎ ነበር።

ይህ እንግዲህ የምርጫ ቦርድ ኦፊሻል የምርጫ ውጤት ነው። ታዲያ በየትኛው የሂሳብ ስሌት ነው ተቃዋሚዎች 49% የሚሆን ድምፅ አግኝተው ነበር የሚሉን?!?!?! ወይስ ምርጫ ቦርድ ዋሽቷል እያሉን ይሆን?!?!

14088937_624973021001365_1677821973_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: