በጎንደር ትጥቅ ለማስፈታት ከሚሰራው የህወሃት ኮማንድ ፖስት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የብዓዴን ሰዎች ተለይተው ታወቁ

በሳምንቱ መጨረሻ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ በአማራ ክልል ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ ለማካሄድ መወሰኑ ተመለከተ። የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ ለኢሳት ባደረሰው መረጃ መሰረት አዲስ ከተዋቀረውና በህወሃት ሰዎች በሚመራው ኮማንድ ፖስት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ የብዓዴን ሰዎች ታውቀዋል።
ከመከላከያ ከፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም ከደህንነት የተውጣጣውና በህወሃት ሰዎች በመሪነት በብዛት የሚሳተፉበት ኮማንድ ፖስት በአማራ ክልል ትጥቅ ለማስፈራት እንቅስቃሴ ጀምሯል።
በተለይ በጎንደር የትጥቅ ማስፈታቱን ስር ለመከወን ከኮማንድ ፖስቱ ጋር በቅንጅት የሚሰሩት የሰሜን ጎንደር አስተዳዳሪ አቶ ሙሉጌታ ወርቁ እና የአማራ ክልል መረጃ ሃላፊ አቶ ዘላለም ልጅ አለም እንዲሁም የሰሜን ጎንደር አስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ መሆናቸው ተመልክቷል።
ከመከላከያ እንዲሁም ከደህንነትና ከፌዴራል ፖሊስ የተውጣቱ 7 ተወካዮች ከላይ ለተዘረዘሩት ሶስት ግለሰቦች ጋር በመሆን ባደረጉት ስብሰባ ማሳሪያ ማስፈራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከመምከር ባሻገር አካባቢዎችን አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ በሚል በአደገኛነት ፈርጀዋል።
ታች አርማጭሆና ምዕራብ አርማጭሆ በአንደኛ ደረጃ በአደገኛነት ሲቀመጡ ወገራና ዳባት በሁለተኛ ደረጃ ተመድበዋል፥ መተማና አለፋ ጣቁሳ በሶተኛ ድረጃ የተቀመጡ ሲሆን፣ አርሶ አደሩ የታጠቀው መሳሪያ በአብዛኛው አውቶማቲክ እንደሆነም ግንዛቤ መጨበጡን መረዳት ተችሏል።
አርሶ አደሮቹ የያዙትን የመሳሪያ አይነት እንዲሁም የአካባቢዎቹን አደገኛነት ደረጃ ከተሰጠው በኋላ ትጥቁን እንዴት እናስፈታ በሚለው በተደርገው ውይይት በቀሳውስት፣ በሃገር ሽማግሌዎችና በሚቀርቧቸው ሰዎች ታጣቂዎቹን አግባብቶ መሳሪያ ማስፈታት በቀዳሚ መፍትሄነት የተነሳ ቢሆንም፣ ከዚህ ቀደም ተሞክሮ ውጤት አለማምጣቱ ወገራ እና ባህርዳር ዙሪያ በአብነት ተጠቅሰዋል።
በየአካባቢው አስተባባሪ ተብለው የሚጠቀሱ ወይንም ዕምነት የሚጣልባቸውን ሰዎች በራሳቸው አካባቢ ሰዎች ዕርምጃ ማስወሰድና የሃይል አማራጭ በሰራተኛና በሶስተኛ ደረጃ መቀመጣቸውንም የጎንደር ህዝባዊ ዕምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ በዝርዝር የደረሰውን ደረጃ ለእሳት አድርሰዋል።
በዚህም መሰረት “ወታደራዊ ስምሪት” በሚል ስያሜ የትጥቅ ማስፈታቱ ዕርምጃ እንዲቀጥል ስምምነት ላይ ተደርሷል።
አርሶ አደሩ አዝመራውን ለመሰብሰብ በተዘጋጀበት ወቅት የትጥቅ ማስፈታቱ ተግባር በሃይል ሊፈጽም መሆኑን አስተባብሪ ኮሚቴው ገልጿል። በዚህ ተግባር የተሳተፉትንና ከህወሃት የመከላከካይ የደህንነት ሰዎች ጋር በትብብር የሚንቀሳቀሱትን የክልል ባለስልጣናት በተመለከተ በስም፣ በፎቶግራፍና በአድራሻ የተዘረዘረ መረጃ እንደሚያስፈልግ የጎንደር ህዝባዊ ዕምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ ገልጿል።

04356-barefoot2btplf2bsoldiers2b-2bethiopia

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: