የመንግስት አዋጅን ተከትሎ በሻሸመኔ በርካታ ሰዎች እየታሰሩ ነው ።

በሻሸመኔ ሀይሌ ገ/ስላሴ ሆቴል በ01/02/2009 የፌደራል ፖሊሶች አዋጁን በመንተራስ በመዝናናት ላይ ያሉ ሰዎችን በመያዝ ወደማጎርያቸው ወስደዋቸዋል ።

በተመሳሳይ በዛው ቀን ሞቢል በተለምዶ ሞቢል ሰፈር በሚባለው ቦታ የአዋሽ ባንክ በስራ ሰአት የታጠቁ የፌደራል ፖሊሶች በስራ ገበታው ላይ ያለን አንድ ሰው ውስጥ ድረስ በመግባት ከቢሮው ላይ አንስተው ወስደውታል ።

በርካታ የግለሰብ ቤቶች እየተፈተሹ ሰዎች እየታሰሩ ሲሆን ከፍተኛ ድብደባም እየተፈፀመባቸው ነው ።

ከተማዋ ወደቀደመው እንቅስቃሴዋ የተመለሰች ሲሆን መረጋጋቱ የተፈጠረው ህወሀት ኢሀዴግ እንደሚለው እራሱን ለማደስ ባለው ቁርጠኝነት ከህብረተሰቡ ጋር በደረሰው ስምምነት ሳይሆን አዋጁን ተንተርሶ እየወሰደ ባለው የመብት ጥሰት በሚፈፅማቸው ጭካኔያዊ ተግባሮቹ ነው ።

ህወሀት ኢሀዴግ የህዝብ ጥያቄ ተገቢና ፍትሀዊ ነው በማለት ለይስሙላ ይናገር እንጂ ጥያቄ ያነሱ ዜጎች ላይ ዛሬም የመብት ጥሰት በማድረግ እየገደለና እያሰረ ነው ።

የምንታገለው ህወሀት ኢሀዴግ እንዳሻው በሚደነግጋቸው ህጎችና አዋጆች ላለፉት 25 አመታት ህዝብን በጎሳና በቛንቛ ከፋፍሎ ኢትዮጲያን የማፍረስ አላማውን በመሆኑ ዛሬ የሚወጡ ህጎችና አዋጆች አዲስ አይደሉም ። ስለዚህ ለነፃነታችን የምናደርገውን ተጋድሎ አያስቆሙትም ።

በሻሸመኔ ከተማ እየተፈፀመ ያለው የመብት ጥሰት ህወሀት ኢሀዴግ በመላው ሀገራችን እየፈፀመ ያለው መንግስታዊ ሽብር አካል ነው ።

በህወሀት የበላይ ቁጥጥር የሚመሩ ሚዲያዎች በእውነታ ላይ ፈርደው ለውሸት ማጎብደዳቸው የህዝብ ጠላት ስለሆኑ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳቸው አይበግረንም ።

ማንም ለነፃነቱ የሚተጋ የንቅናቄያችን አጋር ወደትግል የገባው የህወሀት ኢሀዴግን ጨካኝ እርምጃ እያወቀ በመሆኑ የትኛውም አይነት እርምጃ ወደሁዋላ አይመልሰውም ።

በዚህ አጋጣሚ የንቅናቄያችን ግንባር መሪ ለሆኑት ክቡር ፕሮፌሰር አርበኛ ብርሀኑ ነጋ እና ለመላው የአርበኞች ግንባር ግንቦት ሰባት አባላትና ደጋፊዎች ፡ ለኢትዮጲያዊያን አይንና ጆሮ ለሆነው ህዝባዊ አጋር ኢሳት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ፡ ያለንን ክብርና ቁርጠኛ አጋርነት ዛሬም እያረጋገጥን ለደ አለምነው ድል እንገሰግሳለን !! መቆም የለም !!

ሞት ለአፋኙና ገዳዩ ስርአት !!!
ህዝባዊነት ያሸንፋል ።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: