ይህ መልዕክት የተጻፈው በጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴ ነው ፡፡

እንደሚታወቀው መንግስት ተብየው የማፊያ ቡድን ራሱን የትግራይ ነፃ አውጭ እያለ ከሚጠራው በቀጥታ የራሱን ፍላጎት ማስፈፀም ሲያስቸግረው በፌደራል መንግስት ተቋም ሽፋን በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በኦሮሞው እና በአማራው ላይ ከፍተኛ የሆነ የእልቂት እና ንብረት ቅሚያ በተለይም ትጥቅን የማስፈታት ስራ ለመስራት ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር ለመግባት ወታደራዊ ስምሪት ለመስጠት የሰአታት ጊዜ ቀርተውታል ፡፡ ቀደም ሲል እንደሚታወቀው የኦሮሞን ህዝብ እና አማራውን ህዝብ እንወክልሀለን የሚሉት ኦህዴድ እና ብአዴን ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ያነሱ ፖለቲከኞችም ሆኑ የክልሉ ተወላጆች በኦሮሚያ “ ኦነግ “ በአማራ ደግሞ ግንቦት 7 በማለት ብዙዎችን የምድር ፍዳቸውን ሲቀበሉ መታደጉ ቀርቶ ጉዳያቸውን በሀገሪቱ ህግ መሰረት መታየት አለበት ብሎ ከኦህዴድም ሆነ ከብአዴን የተሟገተ የለም ፡፡ ከዚህ አንፃር የእኩይ ድርጊቱ ተጠያቂ ጉልበተኛው ሕውሐት ብቻ ነው ማለት ገራገርነት ነው ፡፡ የገዛ ወገናቸውን ራሱን ትግራ ነፃአውጭ ብሎ ለሚጠራ የማፊያ ቡድን እንደ እየሱስ ክርስቶስ ዘመኑ አስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፈው የሰጡት ኦህዴድም ሆነ ብአዴን ጭምር የድርሻቸውን መውሰዳቸው አይቀሬ ነው ፡፡ በዚህም መነሻነት ጥቄዎች መልስ እስካላገኙ ድረስ የቱንም ያህል የእስር ቤት ደጆች ቢጨናነቁ ፣ የቱንም ያህል የእስረኞች ሰቆቃ እያደር ቢበረታ በኦሮሚያም ሆነ በአማራ እነዲሁም በሌሎች ቦታዎች በፍርሀት ዝም ፣ ጭጭ ብሎ የሚተኛ ባለመኖሩ ይህም በይፋ በመታየቱ እና እንደ ከዚህ ቀደሙ ዝም ብሎ የሚሞት ሳይሆን ስርአቱን እኩይ ስራ በመገንዘብ የተጠቀሱት የድርጅት ሰዎችም (በኦህዴድ ፣ ብአዴን) ያሉ አመራሮች ለሆዳቸው የአደሩ በሆድ ሚገዙ ሲሆን ፖለቲካውም ሆድ ፖለቲካ ስለሆነ ይህም *የሆድ ፖለቲካ* ኩራትን አያውቅም ፡፡ ኩራትን የማያውቅ ደግሞ ክብርን አያውቅም ክብሩን የጣለ ደግሞ ከዚህ በላይ የሚጥለው ምንም ሊኖረው አይችልም ፡፡ በመሆኑም ህውሀት በቅርቡ የታየውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ቀደም ሲል ይደርግ እነደነበር ቀላል አለመሆኑን በመገንዘብ ለተከታታይ 5 (አምስት) ቀናት ማለትም ከመስከረም 23 እስከ 28 /2009 ዓ.ም ድረስ ባደረገው ዝግ  ስብሰባ ይህን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚል አዘጋጅቶ በማምጣት ለይስሙላ በተቀመጡት የፌደራል ተቋማት ሽፋን በመጠቀም አብዛኛውን ህዝብ በተለይም የአማራውን ህዝብ ትጥቅ አልባ (disarmed )ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቆ ወደ ተግባር ለመግባት ሰአታት ቀርተውታል ፡፡ እንደሚታወቀው አምባገነኖች እብሪታቸውን እንዲተገብሩ ያስቻላቸው የታጠቀው ሀይል ( ጦር ሰራዊቱ ፣ ደህንነቱ እና ፖሊስ ) ተጠሪነቱን ከህግ ይልቅ ለግለሰቦች (ለገዥው ፓርቲ) እንዲሆን በማድረጋቸው ነው፡፡አሁን የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደሚያሳየን ከመከላከያ ፣ ከደህንነት ፣ ከብሄራዊ መረጃ ፣ ከፌደራል ፖሊስ ፣ ከክልል ፖሊስ እና የክልል ልዩ ሀይል እናታ የፀጥታ አካላትን በአንድ እዝ በማስገባት ተጠሪነታቸው ለኮማንድ ፖስቱ እንደሚሆን ሲገልፅ ቀድሞውንም መከላከያና ብሄራዊ መረጃ ፣ የፌደራል ፖሊስ በነማን እጅ እነደሆኑ ስንገመግም በህውሀት እጅ መሆናቸውን እንረዳለን ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ህውሀት የአማራን ህዝብ እነደፈለገ ለማድረግ ህግ ድጋፍ መስተቱን እናያለን በዚህም መነሻነት በአማራ ክል የበቀል እርምጃ በመውሰድ ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴውን ጀምሯል ፡፡ አሁን እኛ የጎንደር ህዝባዊ እምቢተኝነት በክልሉ ከሚገኙ የህዝባዊ እምቢተኝነት አስተባባሪ ኮሚቴዎች ጋር በአደረግነው ውይይት በማንኛውም መንገድ ሁኔታዎችን በተመከታተል ለህዝባችን መረጃ መስጠት እንዳለብን ከምንም በላይ በመረዳት ለአሁኑ በሰሜን ጎንደር ትጥቅ ለማስፈታት በሚደረገው የተግባር ስራ ወስጥ ፡-

1- አቶ ሙሉጌት ወርቁ . . . . . .የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ

2- አቶ ዘላለም ልጅአለም. . . . . . . . . . . . ክልል መረጃ

3- ከመከላከያ የተመደቡ 3 አመራሮች

4- ከደህንነት ብሄራዊ መረጃ 2 ሰዎች

5- ከፌደራል ፖሊስ 2 ተወካዮች

6- አቶ መኳንንት መልካሙ. . . . .. . . . . .የሰሜን ጎንደር የአስተዳደር እና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ በተገኙበት በሰሜን ጎንደር የስብሰባ አዳራሽ ላይ ስብሰባቸውን ያደረጉ ሲሆን የስብሰባው አጀንዳም ፡- – በዞኑ ባሉ ወረዳዎች የታጣቂዎች ብዛት በቁጥር ማወቅ – ህዝቡ የታጠቀው መሳሪያ ዓይነት – የአደገኛነታቸውን ደረጃ ምን እንደሚመስል ገምግመዋል ፡፡ በዚህም መነሻነት በዞኑ በህጋዊ መንገድ ፈቃድ ያላቸው ታጣቂዎች ስም ዝርዝር ፣ የመሳሪያ አይነት የሚጠቅስ ሰነድ የዞኑ አስተዳደር እና ጸጥታ መምሪያ ሀላፊው አቶ መኳንንት መልካሙ ከየወረዳው የመጣውን ዝርዝር ይዞ ሲቀርብ ብዛት ተለይቶ አልቋላ ፡፡ የታጠቁት የመሳሪ አይነት አብዛኛው አውቶማቲክ መሆኑን ለይተዋል በአደገኝነት ደረጃም

1፡- ታች አርማጭሆ ፣ ምእራብ አርማጭሆ ወረዳዎች በአንደኝነት ደረጃ ተቀምጧል

2፡- ወገራን ፣ ዳባትን ፣በለሳ በሁለተኛ ደረጃ ተመድበዋል

3፡- መተማን ፣ አለፋ ጣቁሳ በሶስተኛ ደረጃ ተፈርጀዋል ፡፡ በመቀጠል እርምጃ አወሳሰድን በተመለከተ የተወያዩ ሲሆን እንዴት ይወሰድ በሚለውም 3 የመወያያ ነጥቦች ቀርበዋል ፡፡ እነሱም

1ኛ ፡- ታጣቂዎችን በሚቀርቧቸው ሰዎች ማለትም በቄሶች ፣ በታዋቂ ግለሰቦች ፣ በሽምግልና መልክ እንያቸው ወይም እንቅረባቸው የሚል ሲሆን ይህን ከተወያዩበት በኃላ በሁለት ከተሞች ማለትም በወገራ እንቃሽ ተሞክሮ ወጤት አላመጣም ፣ በባህር ዳር ዙሪያም በአንዳሳ ተሞክሮ ውጤት አላመጥም ስለዚህ በዚህ መቀጠል ጊዜ ከመፍጀት ውጭ ሌላ ውጤት የለውም ተብሎ ውድቅ ተደረገ ፡፡

2ኛ ፡- በአንዳንድ ወረዳዎች በአገኛ ቦታዎች ህብረተሰቡን ያስተባብራሉ ተባሉት ቀንደኛ ሰዎች በመለየት በራሳቸው ሰዎች ላይ እርምጃ ማስወሰድ የሚል ነው ፡፡ ይህም ጥሩ እንደሆነ ተነጋግረው ምንም እንኳን ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስወታ ቢሆንም ይህ ድርጊት መሞከር አለበት የሚል አብዛኛው ተሰብሳቢ ሲስማማ ከመከላከያ የተወከሉት አሁን ባለው እንቅስቃሴ ለዚህ ተግባር የሚሆኑ ሰዎችን ማግኘት እጅግ ከባድ ነው ፡፡ ቀደም ሲል በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ተሚክሮ መክሸፉ ቀጣይ ሚስጥሩ ሲዎጣ ደግሞ መዳማት የሚፈሩ በመሆናቸው ስቸጋሪ ይሆናል የሚል ሀሳብ በመቅረቡ ሌላ አማራጭ እንይ እና ይህን በተጨማሪ እንይዘዋለን ተብሏል ፡፡

3ኛ፡- ያው እንቅስቃሴ ደረጃው ከፍ ያለ እና አብዛኛው ህዝብ በዚህ እምቢተኝነት ተሳተፉ በመሆናቸው ጠንከር ያለ የቡድን ላይ እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል የሚል የመወያያ ሀሳብ ቀርቧል ፡፡ ይህን 3ኛውን ሃሳብ በተመለከተ በህጋዊ መንገድ ሆነ በህገ ወጥ መንገድ ትጥቅ የታጠቀው የህብረተሰብ ክፍል በቁጥር በዛ ያለ ከመሆኑም በላይ ትጥቅን በቀላሉ መስጠት እንደማይፈልግ አብዛኛው ህብረተሰብ ክፍል ምልስ ወታደር ፣ ነባር ታጋዮችና የቀድሞ ጦር ሰራዊት አባላት እና ሽምቅ ታጣቂዎች የነበሩ ከመሆናቸው በላይ ወታደራዊ ችሎታ ባላቸው ቦታውንም በሚገባ ጠንቅቀው የሚያውቁት ከመሆኑ አኳያ በወታደራዊ ስምሪት የቡድን አባላት እርምጃ መውሰድ እና ትጥቅ ማስፈታቱ ስራ ቢሰራ ጥሩ ነው በማለት የቀረበው ሀሳብ አብዛኛዎቹ በቁጥር 2 ከቀረበው የእርምጃ ሀሳብ ጋር በማጣመር እንዲወሰድ ተስማምተዋል ፡፡ በመሆኑም ለዚህ ተግባር ሚሰማሩ ከመከላከያ የተመረጡ ወታደሮች ፣ ከፌደራል ፖሊስም እንደዚሁ ወደ ዞኑ ገብተው የኦረንቴሽን ስራው አልቋል ፡፡ ቡድን ስምሪቱ ተጨርሷል መጠሪያውም * ወታደራዊ ስምሪት * በሚል ሲጠራ አስፈላጊውን የሰው ሀይል ፣ በጀት ፣ ሎጅስቲክስ አቅርቦት ተሰርተው አለቋል ፡፡ ስለሆነም ይህን ተግባር መንግስት መፈፀም እንዳለበት በሙሉ የወሰነ እና ለተግባር ዝግጅቱን የጠናቀቀ ,መሆኑን ስናይ ህዝባችን ይህን አውቆ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ስራዎች እና መከላከል ስራዎች እንዲሰራ ስንመክር መንግስት ይህን እርምጃ አሁን መውሰድ የፈለገው እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ሀምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በወልቃይት የማንነት ኮሚቴዎች ላይ ኦፐሬሽን የከፈተው የአገር አቀፍ 12 ክፍል ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተና በሚወስዱበት ሰዓት መሆኑን እነዲሁም በጎንደር ከተማ ቁጥራቸው 22 በላይ ታዋቂ ግለሰቦችን ባለሃብቶችን የማሰር ስራ ሰራው የአዲስ አመት ዋዜማ ላይ መሆኑን ስናይ አሁን ትጥቅ የማስፈታት እና የበቀል እርምጃውን ገበሬው አዝመራ በሚሰበስብበት ወቅት ለማድረግ መዘጋጀቱን ስንረዳ ህብረተሰቡ ይዘናጋል ብሎ በማሰብ ይህ የትግራይ ነፃ አውጭ የማፊያ ቡድን ለህዝቡ ህይወት ፣ ሀብት ደንታ የሌለው መሆኑን ያሳያል ፡፡ ይህ የማፊያ ቡድን ይህን እኩይ ስራ ለመስራት ሚንቀሳቀሰው ብቻውን ሳይሆን ከመግቢያው እነደጠቀስነው ሆድ አደር ሆኑ አማሮችን በመያዝ እነደሆነ ስነገልፅ  በዚህ ትጥቅ የማስፈታት እና የበቀል እርምጃ ላይ በመሪነት የሚንቀሳቀሱትን ሁለቱን ማለትም

1- አቶ ሙሉጌታ ወርቁ ማን ነው

2- አቶ ዘላለም ልጃለም ማን ነው የሚለውን ህብረተሰቡ እንዲለያቸው ሙሉ አድራሻቸውን ፣ ፎቷቸውን ፣ የኃላ ታሪካቸውን ጭምር በቀጣይ አጠናቅረን እንደጨረስን እናቀርባለን ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !!!

04356-barefoot2btplf2bsoldiers2b-2bethiopia

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: