የወያኔ ወሮበላ ቡድን የግብጽ መንግሥት ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን ከቆመ የዐማራው ሕልውና አደጋ ላይ እንደሆነ አድርጎ ፕሮፖጋንዳ እየሠራ ነው

የዐማራውን ሕዝብ ትግል የሚፈታተኑ ጥቂት ጉዳዮች ሰሞኑን ተከስተዋል፡፡ አንደኛው በተቃዋሚ ተርታ የተሰለፉ ግለሰቦች ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በአገዛዙ ነው፡፡
አገዛዙ ባለፈው ነሐሴ ወር በነበረው የዐማራ ተጋድሎ አገዛዙ ዐማራውን ብቻውን ለመጨፍጨፍ የኦሮሞውን ትግል ‹‹አግባብነት ያለው›› እንደሆነና መልስም የሚያስፈልገው መሆኑን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ነበር፡፡ በተቃራኒው የዐማራው ሕዝብ ትግል ደግሞ ‹‹በምርጥ ዘሮች›› ላይ የተነሳ በመሆኑ ሲወገዝ ሰንብቷል፡፡ ያ እንደማያስኬድ የተገነዘበው ወያኔ ሰሞኑን የባለፈውን ሀሳቡን ገልብጦ እያቀረበ ነው፡፡
አንድ ዓመት የደፈነውን የኦሮሞን ሕዝብ ትግል በግብጽ መንገሥት ሲመራ እንደነበር አድርጎ በመሳል የዐማራውን ሕዝብ ‹‹ታሪካዊ ጠላቶችህ ግብጾች መጡብህ›› ዓይነት ተራ ፕሮፖጋንዳ እየሠራበት ይገኛል፡፡ ይህም የግብጽ መንግሥት ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን ከቆመ የዐማራው ሕልውና አደጋ ላይ እንደሆነ አድርጎ ፕሮፖጋንዳ እየሠራ ሲሆን በቀጣይ ሳምንታት ደግሞ አጠናክሮ እንደሚሄድበት አመላካች መረጃዎች አሉ፡፡ በዚህ ለዐማራው ታጋይ የማስተላልፈው መልእክት እኛ ጠባችን ከትግሬው ፋሽሥታዊ ሥርዓት ጋር ብቻ እንደሆነ እንድንገነዘብ ነው፡፡ የኦሮሞን ሕዝብ ትግል መደገፍ ብቻ ሳይሆን አብሮም የትግላቸው አካል መሆን ግድ ይለናል፡፡
በጠላትነት ደረጃ ብናወዳድር እንኳ ከግብጽ ይልቅ የዐማራው ጠላት ወያኔ ነው፡፡ ምንም አይወዳደርም፡፡ በድርቡሽ መሀዲስት በዐማራው ሕዝብ ላይ ከደረሰው ጉዳት ይልቅ በወያኔ በሕዝባችን የደረሰው በደልና ግፍ ይበልጣል፡፡ ወያኔ በዐማራው ላይ ያደረሰው ግፍ ሁሉም የውጭ ወራሪ ኃይሎች ያደረሱት በአንድ በኩል ብቻውን ሆኖ ቢመዘን እንኳ ሲሦውን አይመዝንም፡፡ ይልቁንስ በላያችን ላይ የወደቀውን ፋሽስታዊ ቀንበር ለመሰባበር የጀመርነውን ትግል አጠናክረን እንቀጥል፡፡
ሁለተኛው ግን በተቃዋሚ በኩል የሚሠማው ነው፡፡ ኦሮሞዎች የራሳቸውን ነጻ መንግሥት ለመመሥረት እየተንቀሳቀሱ ነው የሚል ነው፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት ከሆነ በምንም መልኩ ማዳፈን አንችልም፡፡ የዐማራው ሕዝብ በኦሮሞ ሕዝብ መጻኢ እጣ ፈንታ ላይ የመወሰን ሥልጣን የለውም፡፡ ዐማራው ማድረግ የሚጠበቅበት የራሱን ቤት አጠንክሮ በአንድ አገርም ወይም ጎረቤቶችም ሆነን በትብብር እንዴት አብረን መዝለቅ እንዳለብን ሕልውናችን እንዴት ማስቀጠል እንደምንችል ነው መጨነቅ የሚገባን፡፡ እንደ 1983ቱ ዐማራ በሌለበት የሚመሠረት መንግሥት አይኖርም፡፡ በዚህ እርግጠኞች መሆን አለብን፤ ለዚህም አበክረን መታገል ግድ ይለናል፡፡ ዐማራ የሌለበት አይደለም የሚገባውን ውሳኔ ያላሳረፈበት ስብሰብ ከንቱ ቅዥት ነው፡፡
አንዳንድ ግለሰቦች እነከሌ እነከሌን ያካተተ ስብስብ እያሉ በሚጽፉት ዐማራው መደናገጥ የለበትም፡፡ ይህ ትግላችን ከማጓተት የዘለለ ፋይዳ የለውም፡፡ አሁን በአንድነት ትኩረታችን ወያኔ እና ወያኔ ከተባለው ጥቁር ፋሽስታዊ አገዛዝ ላይ ይሁን፡፡

የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!! ወደፊት!!ሙሉቀን ተስፋው’

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: