የጀርመኗ ቻንስለር በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ

በሚቀጥለው ሳምንት ወደ አዲስ አበባ የሚመጡት የጀርመኗ መራሒተ መንግሥት (ቻንስለር) አንገላ መርከል በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ንግግር አያደርጉም ተባለ፡፡ ምንም እንኳን መንግሥት ቻንስለሯን በፓርላማ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ቢጠይቅም፣ መርከል ግን ‹‹በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር ሥር በዋለ ፓርላማ ውስጥ ንግግር ማድረግ ምንም ለውጥ አያመጣም፤›› በማለት ግብዣውን እንዳልተቀበሉት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ቻንስለሯ ከእሑድ ጀምሮ ሦስት የአፍሪካ አገሮች የሚጐበኙ ሲሆን፣ በመጀመሪያ ወደ ማሊና ኒጀር ተጉዘው ኢትዮጵያ ሲመጡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ይገናኛሉ፡፡ በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረትን ይጐበኛሉ ተብሏል፡፡ ቻንስለሯ አዲስ አበባ ሰኞ አመሻሽ ላይ እንደሚደርሱ፣ አብሯቸውም የጀርመን ፌዴራል ጽሕፈት ቤት ባልረደቦች ብቻ እንደሚመጡ ተገልጿል፡፡ ከቻንስለሯ ጋር ምንም ዓይነት የቢዝነስ ልዑካን የማይመጣ ሲሆን፣ ይህም በሎጂስቲክስ ችግር መሆኑ ታውቋል፡፡ ቻንስለሯ ሰኞ አመሻሽ ላይ ከገቡ በኋላ ማክሰኞ በብሔራዊ ቤተ መንግሥት አቀባበል የሚደረግላቸው ሲሆን፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ረቡዕ ይገናኛሉ፡፡

ምንጮች ለሪፖርተር፣ ‹‹ቻንስለር መርከል በአገሪቱ በተፈጠረው ተቃውሞ የፀጥታ ኃይሎች ዜጐች ላይ እየወሰዱት ስላለው አላስፈላጊና ከመጠን ያለፈ ኃይል ከመንግሥት ጋር ይወያያሉ፤›› ከዚህም ባለፈ፣ ‹‹በቁጥጥር ሥር በተከፈተ›› የአገሪቱ የፖለቲካ ምኅዳር ላይ ይወያያሉ ብለዋል፡፡ ቻንስለሯ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሚኖራቸው ውይይት ስደተኞችን በተመለከተና ሽብርተኝነትን በመዋጋት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራሉ ተብሏል፡፡

ቻንስለሯ መርከል በአዲስ አበባ ቆይታቸው ወቅት፣ ከተመረጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡ እንደ ምንጮች ገለጻ፣ ቻንስለሯ ስድስት ከሚሆኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በጀርመን ኤምባሲ ይወያያሉ፡፡ ሆኖም የውይይቱ አጀንዳንና ተሳታፊዎቹ ማን እንደሆኑ ምንጮች ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

በቅርብ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ የአገር መሪዎች በተለየ ቻንስለሯ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችን ያነጋግራሉ ተብሏል፡፡ በቅርብ ዓመታት የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ፣ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ፣ የደቡብ ኮሪያዋ ፕሬዚዳንት ፓርክ ጉዊን ሃይና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔትኒያሁ ከተቃዋሚዎች ጋር አለመገናኘታቸው ይታወሳል፡፡

ቻንስለሯ በአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘውን አዲሱን የጁሊየስ ኔሬሬ የሰላምና ደኅንነት ሕንፃ ማክሰኞ የሚመርቁ ሲሆን፣ በኅብረቱ አዳራሽም ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡ ከኅብረቱ ሊቀመንበርንና ከሌሎች የኅብረቱ አመራሮች ጋር ይወያያሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡ አዲሱ የሰላምና ደኅንነት ሕንፃ እንዲገነባ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው የጀርመን ፌዴራል የውጭ ጉዳይ ሲሆን፣ ሕንፃው የተገነባውም በጂአይዜድ ነው፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: