ህወሃት/ኢህአዴግ በአማራና በኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት መካከል ግጭት ለመፍጠር እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ የአርሲ ነገሌ ከተማ
ከንቲባና በከተማዋ የቀበሌ 01 ሊቀመንበር አስተባባሪነት በኦሮሞዎችና
በአማሮች መካከል ግጭት ለመፍጠር የተጠናከረ እንቅስቃሴ መደረጉን
በዚህም ሂደትም ጉዳት መከተሉን የአይን ምስክሮች ለኢሳት ገለጹ።
ዛሬ አርብ ከስፍራው ለኢሳት በደረሰው መረጃ መሰረት ባለፉት ሁለት
ቀናት ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ 70 ያህል ሰዎች በአጋዚ የተገደሉ
ሲሆን፣ ከተማዋ በአጋዚ ኮማንዶ ቁጥጥር ስር ወድቃለች።
በከተማው ውስጥ የተካሄደውን ግድያ ተከትሎ በገጠር የሚኖሩ የኦሮሞ
ተወላጆች በከፍተኛ ቁጥር ወደ ከተማ መንቀሳቀስ ሲጀምሩ፣ አማራን
ለማጥቃት እየመጡ ነው በሚል አማሮችን ከኦሮሞዎች ጋር ለማጋጨት
እንቅስቃሴ መጀመሩን ይህንንም የሚመሩት በአካባቢው ከሰፈረው
የአጋዚ ሃይል አዛዦች መመሪያ ወስደው የሚያስፈጽሙት ሚልኪሳ
የተባሉት የከተማዋ ከንቲባ መሆናቸውን መረዳት ተችሏል።
በህዝብ ውስጥ ሰርገው የገቡ ታጣቂዎችና በካድሬዎች አቀናባሪነት
የተጀመረውን ግጭት ለማስቆም የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች
በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ታውቋል። የአርሲ ነገሌ ምንጮች
እንደሚናገሩት አሁን መቀዝቀዝ የጀመረውን ግጭት ለማባባስ ታዋቂ
የኦሮሞ ወይንም የአማራ ተወላጆችን ለመግደል እቅድ ስለመኖሩ
የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ህወሃት/ኢህአዴግ በአማራና በኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት መካከል ግጭት ለመፍጠር እየሞከረ መሆኑ ተገለጸ

  1. taye says:

    የሁሉም ኢትዪጲያዊያን ጠላት አግአዚ ጦርና እና የኢሀድግ ተላላኪዎች ብቻ ስለሆኑን ህዙቡ ይህንን ነቅቶ አዉቆ የተንኮል ሴራዎቻቸዉን በጣጥሶ በጽንአት በጋራ ከተዋጋቸዉ ወያኔ ሴራ እድሜ ስለማይኖረዉ እንደ ጣሊያን የአርበኝነት ዘመን ሁሉም በጽንአት ሊዋጋዉ ይገባል፡፡

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: