በወገራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የተንቀሳቀሰው የወያኔ ሠራዊት በሽንፈት ተመልሷል

ሙሉቀን ተስፋው
በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት የሄደው የወያኔ መከላከያ ሠራዊት በሄደበት እግሩ አፍሮ ተመልሷል፡፡ የአካባቢውን ባንዳ የወያኔ ባለሥልጣናት በመጠቀም አንቃሽ በተባለው ቀበሌ ምሕረት እንዲጠይቁ የሚያግባባ ኮሚቴ የዐማራ ፖሊስ በመያዝ ዛሬ ረፋዱ ላይ ሔደ፡፡ ገበሬዎች ስብሰባ በተቀመጡበት ሰዐት አፋኝ የወያኔ መከላከያ ዘግይቶ ቀድመው የሄዱትን ባንዳዎች ተከተለ፡፡ በማታለል ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታትና ለማፈን ከኋላ የተከተለ የወያኔ ወታደር እንዳመጣ መረጃው ለገበሬዎች ደረሰ፡፡
እነዚህ ቁርጥ የዐማራ ጀግኖች በመተባበር መከላከያ ሠራዊትን ጎድበው ጠበቁት፡፡ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ማዶ ለማዶ ከገበሬዎች ጋር ተፋጦ የዋለው መከላከያ ሠራዊት ከሰዐት በኋላ ወደ ጎንደር ተመልሷል፡፡ ገበሬዎቹን ሰብስበው የነበሩት ባንዳዎችን ሁሉም ላይ እርምጃ መውሰድ የሚገባ ቢሆንም በሽምግልና እንዲህ ዓይነት የባንዳ ማታለል ሥራ እንዳይለምዳቸው በማስጠንቀቅ ለቀዋቸዋል፡፡ የዐማራ ፖሊስ አባላት ግን ወታደር እንደሚከተልና ማታለል እንደነበረበት እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: