ሰበር ጥብቅ መረጃ . . የህወሃታዊያን ብሔራዊ መረጃ የመሐበራዊ ድህረ ገጽን በተለይም የፌስ ቡክ መረጃዎችን እየተጠቀመ የቅድመ ዝግጅት ወረራ እንደሚያካሂድ ከዉስጥ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

እንደ ምንጫችን ከሆነ ብሔራዊ መረጃ ያሰማራቸዉ መደበኛ የኮምፒዉተር መሐበራዊ ግጽ ቃኚዎች ያገኙትን ትኩስ መረጃዎች ለደህንነቱ ክፍል ኮድ ss32*999hsh56325 በማስተላለፍ የቅድመ ዝግጅት አስቸኳይ መመሪያዎችን ይተገብራሉ። በመሆኑም በመሐበራዊ ሚዲያ ግንኙነት ላይ በተለይም የፌስ ቡክ ድህረ ገጽ ተጠቃሚዎች ከታች የተዘረዘሩትን ጥንቃቄዎች በማድረግ የመረጃ ሚስጥሮቻችንን አንዳናቀብል ይታሰብበት።

1. ዜናዎቻችንም ሆነ መረጃዎቻችን የደህንነት ቡድኑን ሊጠቅሙ በማይችሉ መልኩ እንዲሰሩ ይሆኑ ዘንድ መጣር

2. ህወሃታዊዉ የደህንነት ክፍል ሆን ብሎ ህዝብን ለማስፈራራት የሚለቃቸዉን መረጃዎች ለምሳሌ ወዲዚህ አካባቢ የተጠናከረ ከፍተኛ ሐይል እየመጣ ነዉ የሚሉ የማስፈራሪያ ጽሁፎችን ፖስት ከማድረግ በፊት መጠንቀቅ ወይም በዉስጥ መስመሮች መረጃዎችን መለዋወጥ

3. በዚህ አካባቢ እንዲህ ያለ ነገር ቢፈጸም ወያኔን ሊያኮላሽ ይችላል የሚሉ ጥብቅ የጥቃት ጽንሰ ሐሳቦችን ከመበተን ይልቅ ፍንጩ ለሚጠቅማቸዉ አካላት ማቀበል

4. በዚህ አካባቢ የተደራጁ ሐይሎች እርምጃ ሊወስዱ ነዉ ወይም ሊወስዱ ይችላሉ የሚሉ ፍንጮችን መደበቅ

5. በተለይም የአንዳንድ መንግስታዊ የሚባሉ የህወሃታዊያን ድርጅቶችን እንከን በመጠቆም ህወሃታዊያን ችግሮቻቸዉን እንዲፈቱ የሚያደርጉ መረጃዎችን አለማቀበል

6. የህወሃት ወታደራዊ ጉድለቶችንና ስህተቶችን ፌስ ቡክ ላይ ፖስት ከማድረግ መቆጠብ ይልቁንም በተጻራሪዉ ግድፈቶችን ሊጠቀሙበት ለሚችሉ የነጻነት ታጋዮች ማድረስ ከላይ የተዘረዘሩት ዋና ዋናዎቹ የህወሃት መረጃ ክፍል የቅድመ ዝግጅት ንድፈ ሐሳቦች ሲሆኑ የመሐበራዊ ድህረ ገጽ ታጋዮች በሙሉ ጥንቃቄ እንድናደርግ ከወዲሁ ይታሰብበት።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

12887398_560186337480034_849900704_o

 

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a comment