በተመድ የኢንተርኔት መጠቀም መብት ውሳኔ ሐሳብ ላይ ኢትዮጵያ ድምፀ ተአቅቦ አደረገች

14203073_10205312842779177_1040209973_o

ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶችን ዜጐች በኢንተርኔትም እንዲጠቀሙ አገሮች የማስተዋወቅ፣ ከለላ የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው የሚያስታውሰው የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ እ.ኤ.አ. ጁን 27 ቀን 2016 በፀደቀበት ወቅት፣ በጄኔቭ የሚገኘው የኢትዮጵያ ልዑክ ድምፀ ተአቅቦ ማድረጉን መረጃዎች አመልክተዋል፡፡መሠረታዊ መብቶቻቸውን ዜጐች በኢንተርኔትም ጭምር እንዳይጠቀሙ የሚገድቡ፣ የሚከላለክሉና ኢተርኔትን የሚዘጉ አገሮች እንደሚያሳስቡት የውሳኔ ሐሳቡ ይገልጻል፡፡ በማያያዝም ማናቸውም ዓይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለአብነትም ገረፋ፣ ግድያ፣ ሕገወጥ እስር፣ መሰወርና የመሳሰሉት ዜጐች ኢንተርኔትን በመጠቀማቸው ሊደርስባቸው አይገባም በማለት አውግዟል፡፡በተመሳሳይም ዜጐች ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት ግንኙነት እንዳያደርጉ የሚገድቡ አገሮችን በማውገዝ ይህንን የሚተገብሩ አገሮች ከተግባራቸው እንዲቆጠቡ በውሳኔ ሐሳቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡በተጨማሪም በኢንተርኔት የጥላቻ ንግግርን ለመግታት መቻቻልን ወይም በንግግር ማመንን ማስተዋወቅ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥቶታል፡፡ኢትዮጵያ በዚህ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ድምፀ ተአቅቦ ያደረገችበትን ምክንያት ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ በተመድ ኢትዮጵያን ከሚወክለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት የተደረገውም ሙከራ አልተሳካም፡፡ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በውሳኔ ሐሳቡ ላይ ድምፀ ተአቅቦ ባደረገች በሁለት ሳምንት ውስጥ በተግባር ኢንተርኔትን በከፊል በመዝጋት የውሳኔው አካል እንዳልሆነች አሳይታለች፡፡የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ሐምሌ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ መንግሥት ፌስቡክ የተባለውን ማኅበራዊ ድረ ገጽ ለአራት ቀናት የዘጋው ተማሪዎች ተረጋግተው እንዲፈተኑ መሆኑን ገልጸው ነበር፡፡መንግሥት ከዚህ በኋላ ኢንተርኔትን በእንደዚህ ዓይነት አጋጣሚዎች እንደማይዘጋ ምን ማረጋገጫ እንደሚሰጥ የተጠየቁት ሚኒስትሩ፣ ‹‹ቢያንስ እስከመጪው ፈተና ዜጐች ፌስቡክ የመጠቀም መብታቸው የተከበረ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ተመሳሳይ የፈተና ስርቆት ውዥንብር ከተነዛ ግን መንግሥት እንዲሁ ለአራት ቀናት ፌስቡክን ሊዘጋ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም ግን ቫይበርና ዋትስአፕን የመሳሰሉ አፕሊኬሽኖች ፈተናው ካለቀ በኋላ ለአሥር ቀናት አገልግሎት አይሰጡም ነበር፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም እንደ ፋይበርና ዋትስአፕ ያሉ አፕሊኬሽኖችን ኢትዮጵያ ውስጥ መሥራት እንዳይችሉ የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ባለቤት መሆኑን ከወራት በፊት መግለጹ ይታወሳል፡፡የተለያዩ የሰብዓዊ መብት አቀንቃኞች ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በኢንተርኔት ሐሳብን የመግለጽ የዜጐች ነፃነትን እየተጋፋች እንደሆነ በተደጋጋሚ እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ለዚህ በማሳያነት የሚያቀርቡም ‹‹ዞን 9›› በሚባል መጠሪያ የሚታወቁ ጦማሪያንና ጋዜጠኞችን ኢንተርኔትንበመጠቀም አመጽ በማነሳሳት የሽብር ተግባር ክስ ያቀረበባቸው መሆኑንና ጦማሪያኑና ጋዜጠኞቹ ከ18 ወራት እስር በኋላ በፍርድ ቤት በነፃ መለቀቃቸውን ነው፡፡ በዚህ የውሳኔ ሐሳብ ላይ ኢትዮጵያ ተአቅቦ ብታደርግምየውሳኔ ሐሳቡ አስገዳጅ ባለመሆኑ የሚያመጣባት ጉዳት እንደሌለ ታውቋል፡፡

Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: