” በአማራ ክልል ሊካሄዱ የታሰቡ የኢንዱስትሪ ልማቶችን ለመደገፍ የተመደበ 4.5 ቢሊዮን ብር ለትግራይ ክልል መተላለፉ በብዓዴን አባላት ዘንድ ቁጣ ቀሰቀሰ “

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በየትም አገር የሌለ እጅግ ኋላ ቀር የሆነ የአፓርታይድ ስርአትሲስተም የሚፈፀባት አገር ነች ። ወያኔ ከ95 ሚሊዮን ህዝብ አፍ እየነጠቀ ለ 5 ሚሊዮን ህዝብ ኬክ ይጋግራል። ከዚህም ይባስ ብለው ” እኛ ሰማይ ጠቀስ ፎቅ እየገነባን ክልላችንን እያበለፀግን ስንኖር እናንተ እያጨበጨባችሁልን ካልኖራች ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያ እናፈራርሳታለን ይሉናል።
ሌላው አሰልችው እና የኢዮብን ትእግስት ያለውን ሰው እንኳን የሚፈታተነው ውሸት “ትግራይ በዚህ ስርአት አልተጠቀመችም” የሚለው በሬ ወለደ ውሸት ነው ።

ባለፈው ጃስሚን ራያ ይሄን ጉዳይ በማስረጃ ስታቀረብ ነበር። በአጠቃላይ ይሄ ጉዳይ እጅግ የሚያስተዛዝብና ከእነሱ ጋር የአንድ አገር ዜጋ ተብሎ ለመጠራት የማያስመኝ ነው።
ባደባባይ ያፈጠጠ ሃቅ፣ ባደባባይ መካድ?!?! እስከመቼ አገር ያወቀውን ፀሃይ የሞቀውን ጉዳይ እየሸመጠጡ መቀጠል ይቻላል:?

1. የባቡር መንገድ ከቡናው መገኛ ከጅማ ወይም ከወርቁ አገር ሻኪሶ ይልቅ ቀድሞ መቀሌ የሚዘረጋበት አምባሻ ለመጫን ወይስ ቁልቁዋል export ለማረግ ነው?

2. ትግራይ (ለአምስት ሚሊዮን ህዝብ) 4 ዩኒቨርሲቲ ሲኖራት (መቀሌ፣ አዲግራት፣ ማይጨው፣ አክሱም፣ በፌደራል መንግስት የሚሰሩ አያሌ ሆስፒታል፣ ኮሌጆች፣ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ትተን) በሃገር ደረጃ መቶ ሚሊዮን ህዝብ 80 ዩኒቨርሲቲ ሊኖረው ይገባ ነበር። አሁን ሌሎች ክልሎች ከትግራይ ጋር ሲነጻጸር አንድ ሶስተኛ ብቻ ነው የተሰራላቸው፣

3. የአማራ ክልል በስፋትም ሆነ በህዝብ ብዛት የትግራይን ቢያንስ ሶስት እጥፍ ሲሆን፣ ትግራይ ውስጥ ከለሙና ከተሰሩ ፋብሪካዎች (አዲግራት መድሃኒት ፋብሪካ፣ ዉቅሮ ዘመናዊ መኪና መጋጣጠሚያ፣ መቀሌ ሞተር ማምረቻ፣ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ (አልመዳ፥ በሃገሪቱዋ ትልቁ) ሲሚንቶ፣ ብረታብረት፣ ወዘተ፣ ወዘተ፣ ጋር ሲነጻሰር አማራ ክልል ውስጥ አንድ አስረኛው እንኩዋ የለም፧

4. የኢትዮጵያ ሲቪል አቭየሽን ባለስልጣን በሃገር ውስጥ 21 የአውሮፕላን ጣቢያ ቦታዎች አሉት። ከነዚህ ውስት 4ቱ ትግራይ ውስጥ ናቸው (መቀሌ፣ አክሱም፣፣ አድዋ ፣ እና ሽሬ)። መልመጃ፤ ለአምስት ሚሊዮን ህዝብ አራት አውሮፕላን ጣቢያ ከተሰራ ለመቶ ሚልዮን ህዝብ ስንት አውሮፕላን ማረፊያ ያስፈልጋል?!?! እውነት አራት ለአንድ እየመራችም ትግራይ አልተጠቀመችም?!

5. የኢትዮጵያ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ትግራይ ውስጥ 14 የመንግስት ሆስፒታሎች ሲኖሩት አማራ ክልል ውስጥ ደግሞ 17 የመንግስት ሆስፒታሎች አሉት። ለ 5 ሚሊዮን የትግራይ ህዝብ 14 ሆስፒታል ሲገነባ፣ ለ 35 ሚሊዮን የ አማራ ህዝብ ስንት መገንባት ነበረበት?!?!

6. ከአምስት አመት ወዲህ ተከዜ ለሃገሪቱ የሚያመነጨው ኤሌክትሪክ 0% የሆነበት ምክንያት ሙሉ በሙሉ ለትግራይ እርሻዎች ማልሚያ በመዋሉ ነው። አማራ ክልልስ?? ይሄው ጣና በለስ፣ መገጭና ርብ ለግድብነት ከተጀመሩ ሶስተኛ ገዢዎች ላይ ነን (ንጉሱን ጨምሮ)። የአባይን ልጅ ውሃ ጠማው ማለት ይሄ ነው።
እና አሁንም ትግራይ የአውሮፓን ህብረት መቀላቀል እስክትችል ድረስ ሌላው ክልል ገደል ይግባ ነው ሂሳባቸው። በነገራችን ላይ የመቀሌው ባቡር ሆን ተብሎ የአማራ ክልልን ከተሞች እንዳይነካ ተደርጎ ነው መቀሌ የገባው። “አዋሽ፣ ወልዲያ፣ መቀሌ” የሚሉትን ማደናበሪያ ወልዲያ ሄዳችሁ ማየት ትችላላችሁ። ከወልዲያ 15 ኪሎ ሜትር ርቆ በሃራ ገበያ በረሃ ነው የሚያልፈው።

ወይ ትግራይ አልተጠቀመችም!! እስኪ ዙሪያችሁን እዩ ትግራይ ላይ የሌለ ፍብሪካ አለ
ሌላው ጋርኮ የዱቄት እና ቢራ ፍብሪካ ነው የሞላው ። የትግራይ ህዝብ ከስርአቱ ተጠቃሚ ነው የሚለውን ጥሬ ሃቅ እንድታምኑ የግድ
6 ሚሊዮን ትግሬዎች ሚሊየነሮች መሆን አለባቸው ወይ?

ሀይሉ ቢታንያ

13819494_611651515666849_1114674654_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: