በአገራችን ላይ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አለምንም እያነጋገረ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ የእያንዳንዱ ዜጋ የፖለቲካ አስተሳሰቡ በሚፈለገው ደረጃ እየሄደ ይገኛል፡፡
ምክንያቱም እያንዳንዱ ዜጋ ፖለቲካን ከማህበራዊ ኑሮው እና ኢኮኖሚው ነጥሎ መተው አይችልም፡፡ አንፈልገውም ብንል እንኳ እለት በእለት ከሚኖረን ህይወት ጋር ተያያዥነት ስላለው የእያንዳንዳችን ቤት ማንኳኳቱ አይቀርም፡፡

በአሁኑ ሰዓት የዜጎች ፖለቲካዊ ተሳትፎው አጥጋቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ማለት አይቻልም፡፡
ያሁኑ ትውልድ እጅግ አደንዛዥ ከሆኑ ዕፅ፣ ከፊልም ፣ ከኳስ ሱስ በመውጣት አንዴ ቆም ብለን እናስብ!!! አደራ አለብን!!! እንንቃ እንሳተፍ!! ገለልተኛ መሆናችን ይብቃ!! የኛ ዝምታ ሌሎችን እንዲሞቱ እየፈቀድን መሆኑን መረሳት የለበትም፡፡

ወያኔ 25 አመት ሙሉ ከደርግ በከፋ አገዛዝ ስርዓት ኢትዮጵያን እያጠፋ ይገኛል፡፡
ባለፉት አመታት በዘመነ ወያኔ ብሔር ከብሄር ለማጋጨት ታሪክ እየተቀየረ ትውልድ እንዲማረውና የዘረኝነት አስተሳሰብን ይዞ፡ ያውም በውሸት ታሪክ ተመርዞ ብዙ ህዝቦች እርስ በርስ ከመጠላላትም አልፎ ወደ ግድያና መፈናቀል የተካሄደበት ዘመን!!!
*** እንግዲህ ወገኖች ከተኩላወች ተጠበቁ ነውና***

የወያኔን ታሪክ ፈጠራ ተምረን !!አምነን!! ኖረን ግን ውጤቱን አይተናል!!
መበታተን!! መከፋፈል !!! መተቻቸት!!! በቃ ውጤቱ ይህ ነው!!!
በአሁን ሰዓት **እውነትና የህዝብ ጆሮ በትክክለኛው ሰዓት ላይና አቅጣጫ ላይ ይገኛል!!!!!
እውነት ጊዜን ጠብቃ የብርሃን አድማሷን ጎህ እየቀደደች ነው፡፡
ህዝብ የጆሮውን ኮምፖስ አዙሯል፡፡
ወያኔ ወቅታዊውን ጉዳይ አስመልክቶ በተለያዩ መድረኮች ላይ ተሸናፊዎች የሚወስዱትን አቋምና እርምጃ እያካሄደ ይገኛል፡፡
* የወያኔ ግድያ፣ እስራት የህዝብን ትግል ማስቆም ሳይሆን ማስቀጠል እንደሆነ የተረዳው አይመስልም፡፡
ህዝብን እየገደሉ እያሰሩ መግዛት ማሰብ የፖለቲካ እንጭጭ መሆኑን እንረዳለን፡፡
** ወያኔ ተመልሸ አስተካክለዋለሁ ወደማይለው አዘቅት ውስጥ ገብቷል፡፡ በአንፃሩም የህዝብ ትግል አድማሱን እያሰፋ ገና ይቀጥላል!!
**በዚህ ትውልድ ታሪክ ይቀየራል!!!!
ከዘረኝነት ከመከፋፈል የፀዳችና ህዝቦች እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑባት ኢትዮጵያን እንፈጥራለን!!!!
ይህ የሚሳካው ሁሉም ዜጋ ፖለቲካዊ ተሳትፎ ሲያደርግ ብቻ ነው!!!
ድል ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ህዝብ!!!!!

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: