በሳውዲ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠየቁ።

ሴፕቴምበር 15 2016 ምሸት ሪያድ ከተማ ውስጥ የዱአ እና ሰደቃ ፕሮግራም በማድረግ ለሃገራቸው ሰላም ጸሎታቸውን ያደረሱት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ድረጀት አስተባባሪነት ኢትዮጵያ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ እና በድርጀቱ ቀጣይ የትገል መረሃግበር ዙሪያ ባደረጉት ሰፊት ውይይት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ኢትዮጵያ እና ህዝቧ አሁን ከገቡበት ቀውስ ለማዳን የሽግግር መንግስት ማቋቋም እንዳልበት ባወጡት የአቋም መግለጫቸው አሳስበዋል ። የኢትዮጵያ ሙስሊም የአወሊያ ን የትምህረት መዕከሉን እና የሙስሊሞች ጉዳይ ከፍተኛ ጉባኤ ካጣበት እና ሀባሽን አልጋትም ብሎ ላለፉት 4 አመታት እልህ አስጨራሽ ትግል ካደረገ በሃላ በከፊልም ቢሆን ከጎኑ ያጣቸው ወኪሎቹ ከእስር ነጻ ወጥተው ለማየት በመብቃታቸው ፈጣሪያቸውን በማመስገን አሁንም የቀሩት ከእስር እንዲወጡ ነጻነታቸውን እንዲያፋጥነው ምኞታቸውን ገልጸዋል ። የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት በወሰደው እርምጃ ግራ የተጋባው ሙስሊሙ ማህበረሰብ ስረአቱ የሰማኝ እንድሆን ብሎ የካቲት 26 2004 ወኪሎቹ ከፌደራል ጉዳዩች ሚንስትር ጋር ውይይት ካደረጉ በሃላ እስላምዊ መንግስት ልታቋቁሙ ነው በሚል በአሸባሪነት በመፈረጅ ሃምሌ 6 2004 ለሊት የአጋዚን ጦር አወሊያን ሰብሮ በመግባት ብዙዎችን ደበደበ አቆሰለ ገደለ የተረፉትን እስርቤት በማጋዝ አንከራተተ አሰቃየ ብለዋል። ሃምሌ 12 2004 ጀምሮ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ደጋፊዎች እና ተባባሪዎች ናቸው ያላቸውን ንጽሀን ከያሉበት አስሶ በመያዝ በማዕከላዊ የስቃይ እስርቤት በማጎር ብርቅ የሃገር አሌታዎችን የስቃይ ሰለባ አደረጋቸው ፡፤ ይህ ባለበት ሁኔታ ላለፉት 4 አመታት ህዝበ ሙስሊሙ በሰላማዊ መንገድ ሲያቀርቡ የነበረውን የመብት ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ግፍ ሲፈጽምባቸው የነበሩትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በነጻ በማሰናበት ከመሸበት በሃላ ህዝበ ሙስሊሙን ለመጨበጥ እያደረገ ያለው ጥረት ተያይዞ ለመውደቅ ካልሆነ በቀር ትርጉም እንደሌለው ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ ባወጡት የአቋም መግለጫቸው ገልጸዋል፡፡ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የዘራውን እያጨደ መሆኑን የሚጠቅሰዋ መግለጫ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በስረአቱ የተነጠቁትን ህገመንግስታዊ መብቶቻቸውን ለማስከበር ጠላትህን ውሃ ሲወስደው እትፍ ብለህ ጨምረበት በማለት ስረአቱ ያበቃለት መሆኑን አመልክቷል፡፤ የኦሮሚያን ህዝብ አመጽ ተከትሎ በአማራ የተቀጣጠለው ህዝባዊ እቢተኝነት ሰረአቱን በአጭር ግዜ ውስጥ ምን ያህል እንዳሽመደመደው ያወሳው መግለጫ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነታቸውን ጠብቀው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ላይ ተመሳሳይ የትግል ስልቶችን ተከትለው ቢሆን ኖሮ ለ አይቀሬው ድል ይበቁ እንደ ነበር በመግለጽ የጎንደር ህዝብ አንድነቱን ጠብቆ በስረአቱ ላይ እያሳደረ ያለው ተጽእኖ ለህዝበ ሙስሊሙ ትምህረት ሊሆን እንደሚገባ ጠቅሷል ፡፤ በተደጋጋሚ ህዝበ ሙስሊሙ ላቀረበው ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ለሚመከረው ምክር እና ለሚጠየቀው ጥያቄ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ያዋጣኛል ባለበት መስመር ህዝብ እየደፈጠጠ እዚህ ደርሷል የሚለው መግለጫ። ትላንት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት በሙስሊሙ ህዝብ ላይ የጀመረውን የግፍ ዱላ በደሃው አርብቶ አደር እና አርሷ አደሩ ላይ በማሳረፍ በኦሮሚያ ያቀጣጠለውን እሳት በአማራው ህዝብ ላይም በመለኮስ የሰፊው ህዝብ ጠላት መሆኑን በገሃድ አረጋግጦል ብሎል። የኦሮሚያ እቢትኝነት ወደ ሰሜኑ ተሸጋግሮ ስትንት የተለፋበት እና ለብዙዎች ስለባ መረብ የሆነው የአንድ ለአምስት የአደረጃጀት መረብ ተበጣጥሶ ምንም መቋጠር አቅቶታል የሚያወሳው መግለጫ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሲመካበት የነበረው የፌደራል እና የአጋዚን ጦር ሃይል በህዝብ ላይ የከፍተው ጥቃት እንደማያዋጠው ተገንዝቦ የጥፋት እጁን በመስብሰብ ህዝቤን ማለት ጀመሯል ብሏል፡፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት መግለጫ በማጠቃለያው ዛሬ ለኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት የምናስተላልፈው መልዕክት እስረኞቼን ፍታ ጥያቄን መልስ ሳይሆን ታስረሃል እና ከዚህ በኃላ የመጨረሻ ስህተት እንዳትሰራ የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ ሃገር እንድትደን በአስቸኳይ ተገቢውን እርምጃ እንድትወስድ በአጽኖት እናሳስባለን ብሏል። ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: