ኮንሶ በአሁኑ ሰአት የጦር አውድማ ሆናለች!

ወያኔ የኮንሶ ነዋሪዎችን ከነቤታቸው በእሳት አቃጥሎ እየገደላቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ኮንሶ ውስጥ የሚሰሩ የመንግሥት ሰራተኞች ለ5 ወራት ደመወዛቸው አልተከፈላቸውም፡፡ ህዝቡ ካለፈው መጋቢት 2008 ዓ.ም. በወታደሮች እየተገደለ፣ እየታሰረና እየተፈናቀለ ነው፡፡ ከዚህ በደል ያመለጠ ቀየየውን ለቆ ወደ አጎራባች ኦሮሚያ ክልል ወረዳዎች እና ሌሎች አካባቢዎች እየተሰደደ ነው፡፡

ህዝቡ ይህ ሁሉ በደል እየደረሰበት ያለው ”ካለን የህዝብ ብዛት እና የቦታ ስፋት አንፃር ከልዩ ወረዳነት ወደ ዞን አስተዳደር በማደግ ራሳችንን እናስተዳድር” ብለው ሰዎቹ ፅፈው በሰጧቸው ሕገ-መንግሥት መሰረት ጥያቄ ሲያቀርቡ፤ ይብሱኑ ወደ ወረዳ አስተዳደር አሳነሳቸው፡፡ ይሄንን የአገዛዙን የኃይል ርምጃ በመቃወም ሰላማዊ ሰለፍ አደረጉ፡፡ ከዚያም በወታደሮች ግድያ፣ እስር፣ ስቃይና ስደት ዕጣ ፈንታቸው ሆነ፡፡ እነሆ ሰሞኑን ደግሞ የመብት ጥያቄውን አስተባብረዋል፣ ደግፈዋል፣…ተብለው በአገዛዙ የተጠረጠሩ፣ ከመጋቢቱ ግድያ፣ እስርና ስቃይ የተረፉትን ”መንግሥት” በያዝነው መስከረም 2009 ዓ.ም. ከነ መኖሪያ ቤታቸው ጋር አብሮ እያቃጠለ ሲሆን፤ ለማምለጥ የሞከሩት ደግሞ በወታደሮች ጥይት እየተገደሉ ነው፡፡

የሠራዊቱ ቁጥር እየተጨመረ ነው እስካሁን ከ2000 በላይ መከላከያ ከ1500 በላይ የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል ከ100 በላይ የሠገን አካባቢ ህዝቦች ዞን ፖሊስ የፌዴራል መከላከያ ምክትል አዛዥ እና የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽኑ አቶ ፊስሃ ጋረደው የሚመሩ ናቸው እስካሁን ድረስ ቃጠሎ ቀጥሏል የሞቱት ሰዎች ከ150 በላይ ሲሆን የቆሰሉ 200 በላይ በዛሬው ዕለት ብቻ የተቃጠሉ ቤቶች ከ159 በላይ ሲሆኑ ከ15,000 በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ሲፈናቀሉ ፤ ከ50 በላይ ሰዎች ታስረዋል ፡፡ የአንድ ባለሀብት ንብረት የሆነው አይሱዙ መኪና በልዩ ኃይል መንገድ ላይ እየሄደ እያለ ጎማ በጥይት ተመትቶ ግለሰቡ አቶ አዲሱ ሙሉ እና የወንድሙ ልጅ ከወንድሙ ጋር አሳስረው ክፉኛ ተደብድበው በህይወት አፋፍ ላይ ናቸው ፡፡ ቤተሰቦቻቸው እንዳይጠይቋቸው ተከልክለዋል ፡፡ እስካሁን ተፈናቃዮችም ሆነ የታሰሩ ሰዎች የሚጠይቅ የመንግሥትም ሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች የሉም ፡፡

ይህ ግፍ ምናልባት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ በአለም ታርክ በኢህአዴግ መንግሥት የጠፋ ብሔር ሆኖ ኮንሶን ሊያስመዘግብ ይችል ይሆናል ፡፡

14355142_877873255646464_8782711721462134178_n 14349126_636354039863263_1654501838_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: