የሳምንቱ አበይት ዜናዎችና ሌሎች መጣጥፎች የሚገኙበት ራዲዮ ያድምጡ

የህወዓት አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ የኦሮሞ ዜጎችን በመማታቸው ክስ ቀረበባቸው ተባለ።

ዛሬ ሁለት የኦሮሞ ዜጎች ኤደንና ኪያ ወደ ኢትዮጵያ ኢንባሲ በመግባት ተቃውማቸውን ማሰማታቸው ተነግራል ይህንንም ተከትሎ ሁለቱም ሰዎች ላይ በአባሳደር ግርማ ብሩ ድብደባ እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል

ኤደንና ኪያ ወደ ኢንባሲ መኖርያ ስፍራ በሰኩርቲ ተመርተው የሄዱ ሲሆን እዛም እንደደረሱ ግርም ብሩን አንተ የኦሮሞ ህዝብ ነኝ ትላለህ ወይ ተተያቂነቱ የቱጋርነው ማፈርአለብህ ብለው በሚቃወሙ ጊዜ ነበር በ አባሳደሩ ተደብድበው እንዲወጡ የተደረጉት ተብላል

በዚህም በጆርዋቸውና በፊታቸው ላይጉዳትበማስከተሉ ወደ ክስ ማምራታቸው ተናግረዋል

 

 

አውሮፓ ህብረት  በወያኔ መንግስት ላይ መአቀብ ጣለ!!!
በወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው የኢትዮጵያ መንግስት ከአውሮፓ ህብረት በየአመቱ ዳጎስ ያለ እርዳታና ብድር ሲገኝ መቆየቱ ይታውሳል። ህብረቱ ባሳለፍነው ሳምንት በአወጣው መግለጫ ገዳዩና ዘረኛው የትግሬ ወያኔ መንግስት እየፈጸመ ባለው ልክ ያጣ የሰበዊ መብት ጥሰት ከግዜ ወደ ግዜ እየባሰበት በመሄዱ እና ምንም መሻሳል ባለማሳየቱ ከዛሬ ጀምሮ ምንም ከህብረቱ ምንም አይነት የገንዘብ እና የቁሳቁስ እርዳታ እንደያገኝ እና ከዚህበፊትም የተፈራረማቸው የእርዳታና የድጋፍ ዉሎችን በመሰረዝ መአቀብ ጥሏል። ህብረቱ እንደነ አሜሪካ ፣ የአለም ባንክ፣ የአለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ለሌሎች አካላትንም አካሄዳቸዉን ባስቸኳይ መርምረው እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል።

አዲስ የተቋቋመዉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰራተኞችን የሚመድበዉ ዘር እየቆጠረ መሆኑ ተደረሰበት
———————————–
ቀደም ሲል በአራት ልዩ ልዩ መስሪያ ቤቶች ስር የነበረዉ የአቃቤ ህግ አወቃቀርን በአንድ አመጣለሁ በማለት በቅርቡ አዲስ የተቋቋመዉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰራተኞችን የሚመድበዉ ዘር እየቆጠረ መሆኑን ከስራ የተቀነሱ ባለሞያዎች በምሬት እየገለጹ ነዉ::
በፍትህ ሚኒስቴር: በጸረ-ሙስና : በግሙሩክ እንዲሁም በንግድና እንዱስትሪ መስሪያ ቤቶች ስር በተናጠል ይመራ የነበረዉ የአቃቤ ህግ ስራን በአንድ በማምጣት የተሻለ የአቃቤ ህግ ስራን በሀገሪቱ ለማስፈን ተዋቅሪያለሁ ሲል የተነሳዉ አዲሱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገና ከመነሻዉ በዘረኝነት እና በወንጀለኛ አሰራር ተተብትቧል::
ከአራቱ መስሪያ ቤቶች ይሰሩ የነበሩ አቃቤ ህግ ሰራተኞችን ብዙሃኑን አግልሎ ከአንድ አናሳ ጎሳ ብቻ ነጥሎ (የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ አባላትን ብቻ) የመዉሰድ ስራ እየተሰራ ነዉ::በተለይም አሁን በሀገሪቱ ከተነሳዉ የህዝባዊ ተቃዉሞ እና ተጋድሎ ጋር ተያይዞ የኦሮሞ እና የአማራ አቃቤ ህግ ባሌሞያዎችን አናምናቸዉም በማለት ቀጥተኛ የማንሳፈስ ስራ እየተሰራ መሆኑን በደሉ የደረሰባቸዉ ባለሞያዎች ገልጸዋል::
በህግ ጉዳይ: በስለላ ጉዳይ: በጸጥታ ጉዳይ: በወታደራዊ ጉዳይ: በዲፕሎማሲያዊ ጉዳይ በአጠቃልይ ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ አቅም ባላቸዉ ጉዳዮች ላይ ወያኔ 95 % የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አያምንም:: በመሆኑም በነዚህ ዘርፎች ላይ ዘር እየመረጠ ይመድባል:: ብዙሃኑን የማህበረሰብ አካላትን ያገላል::
ስለሆነም የጠቅላይ አቃቤ ህግ መቋቋምም ዋና አላማዉ ከብዙሃኑ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተገኘዉን የአቃቤ ህግ ባለሞያ ለማግለል እና የአቃቤ ህግ ስራዉን በአንድ አናሳ ጎሳ አባላት ብቻ (የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ አባላትን ብቻ) ለመሙላት እንደሆነ አሁን ግልጽ ሆኗል:: ልክ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽንን በማፈራረስ የብዙሃኑን ኢትዮጵያዉያንን ማህበረሰብ ባገለለ መልኩ በአንድ አናሳ ጎሳ ብቻ በመሙላት በአዲስ መልክ እንዳዋቀሩት አሁን ደግሞ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሚል አካሄድ የአቃቤ ህግ ዘርፉን በአንድ አናሳ ጎሳ ብቻ ለመቆጣጠር ወስነዋል::
ከዚያም በንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ላይ ያለወንጀላቸዉ ወንጀለኛ እያሉ የሚከሱ ህሊናቢስ እና ወንጀለኛ አቃቤ ህግ ባለሞያዎች እንዳሰኛቸዉ ወንጀል ለመፈብረክ እና ያለ ነቃሽ ህዝቡን ሁሉ ለመወንጀል ይችላሉ ማለት ነዉ::

 

በጎንደር ከተማ ሲካሄድ የሰነበተው የፌደራል ፖሊሶች ስብሰባ ባለመግባባት ተበተነ፡፡

ፌደራል ፖሊሶች በጎንደር ከተማ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ውስጥ ከጳግሜ 2 2008 ጀመሮ ሲያካሂዱት የሰነበቱት ስብሰባ ምክትል ኮማንደር ሞላ ያስብ እና ምክትል ኢንሰፔክተር ታደስ አብርሃ በተባሉ የህወሓት ሰዎች ነበር የተመራው፡፡ ተሰብሳቢዎች እንዲወያዩበት የመድረኩ መሪ ከሆኑት ከእነኚህ የህወሓት ሰዎች የቀረበላቸው ሃሳብ “የፌደራል ፖሊስ ሰራዊት ስራ በቃን ማለትና የውጊያ ሞራል መላሸቅ” የሚል ነበር፡፡
በስብሰባው ላይ በርካታ ቅሬታዎች የተነሱ ሲሆን በተለይም ደግሞ ተደጋግሞ የሚወሳው በፌደራል ፖሊስ ተቋም ውስጥ የሰፈነው የህውሓት ሰዎች የበላይነት ዋነኛውና ሰፊ ጊዜ ወስዶ ያነታረከ የችግሩ ሰንኮፍ ነው፡፡

ህወሓቶች በሰራዊቱ ውስጥ በመንደር ተድራጅተው የበላይነት ከመያዛቸው በተጓዳኝ ፍፁም ቆራጭ ፈላጭ እና የለየላቸው አምባገነኖች መሆናቸው “በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ” እንደሆነባቸውም ጭምር ተስብሳቢዎች ተናግረዋል፡፡

ተደራራቢ ኃላፊነት ይዘው የወጣላቸው አምባገነኖች ከሆኑት የፌደራል ፖሊስ አዛዥ ከሆኑ የህወሓት ሰዎች መካከል ኮማንደር ካህሳይ በስብሰባው ላይ ስሙ ተነስቷል፡፡ ኮማንደር ካህሳይ የትራንሰፖርት ኃላፊ፣ የአጠቃላይ በጀት ኃላፊ፣ የወንጀል መከላከል ኃላፊ፣ የልዩ ገቢዎች ኃላፊ… እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

በስብሰባው ተሳታፊ የነበሩ አብዛኞቹ የፌደራል ፖሊስ አባላት በሰራዊቱ ውስጥ የሚታየውን የመንደርተኝነት መዋቅርና የዘረፋ መስመር የዘረጉት ኮሚሽነር ግርማይ ማንጁስ እና ረዳት ኮሚሽነር ተክላይ እንደሆኑ በመጥቀስ ከእንግዲህ ወዲህ ከህወሓቶች ጋር መስራት እንደማይፈልጉ አቋማቸውን አስታውቀዋል፡፡

በአጠቃላይ በጎንደር ከተማ ሳንይንስ አምባ አዳራሽ ሲካሄድ የሰነበተው የፌደራል ፖሊሶች ስብሰባ ከጭቅጭቅ፣ ንትርክና እርስበርስ ከመወነጃጀል የዘለለ ፋይዳ አልነበረውም፡፡ በመሆኑም ባለመግባባት ተደምድሟል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ዛሬ የኢድ በአል ላይ ድንገተኛ ተቃውሞ ማድረጋቸው ተሰማ!

መላው የኢትዮዽያ ህዝብ አንቅሮ የተፋው የትግራይ ወራሪ ወንበዴ ባደባባይ ሽንፈትን ሲጎነጨው ሰንበትበት ቢልም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት እየትፍጨረጨረ ይገኛል።

ይህንን የህዝብና የሀገር ጸር !መንግሎ ለማጣል በሚካሄደው ትግል የኢትዮዽያ ህዝብ ዘር፣ሀይማኖት፣ቋንቋ ሳይለይ በአሁኑ ሰአት በጋራ_ጠላቱ ላይ በሙሉ አቅሙ ተነስቷል።

በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በሰላማዊ መንገድ ጸረ ወያኔ ትግሉን የጀመሩት የሙስሊም ወገኖቻችን ትግል ዛሬ ላይ በሰፊው የኦሮሞና  የአማራ ህዝብ ህብረትና አብሮነት ታግዞ በወያኔ መንደር ፍርሀትና ጭንቀትን ወልዶ የስርአቱ ቀጣይ አገዛዝ ህልም ሆኖ ቀርቷል።አሁን የተፈጠረውን አገር አቀፍ ጸረ ወያኔ ትግል በህዝብ ድል አድራጊነት ሊደመደም የብዙ ወገን መሰዋትነት ተከፍሏል።

ቀደም ሲል ለአገዛዙ ቢጫ ካርድን በማሳየት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ የነበሩት የሙስሊሙ ማህበረሰብ በመላው ኢትዮዽያ በዛሬው የኢድ በአል ላይ  ቀይ_ካርድ በማሳየት ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገራቸው ተነግራል።

በተያያዘ ዜና

በአዲስ አበባ በተለያዩ ቤተክርስቲያናትና አድባራት ሙዳየ ምጽዋትንና አስራትን ባለመክፈል ወያኔ ያስቀመጣቸውን ቦርጫም ካህናትና ዲያቆናት ምዕመኑ መቅጣት ጀምሯል።
ይህ ይበል የሚያሰኝ ጅማሬ ነው።
በጎጃምና በጎንደር የሚገኙ አድባራትና ገዳማትም በወያኔው ሲኖዶስ ላለመገልገል በመወሰን ስርአተ አምልኮ (ቅዳሴ) ላይ የአባ ማትያስን ስም ባለመጥራት ተቃውሟቸውን መጀመራቸውም ተነግራል።

የኢትዮጵያዊያን ማህበር በኖርዌይ ሮግላንድ የአዲስ አመት ዋዜማን በሀገራችን በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን የሻማ መብራትና የፀሎት ስነስርሀት አደረጉ

በኖርዌይ ሮግላንድ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ማህበር/Ethiopian Community Rogaland/ በስታቫንገር ከተማ አዲስ አመትን አስመልክተው ባዘጋጁት ዝግጅት ላይ በሀገራችን በግፍ ለተገደሉ ወገኖቻችን የሻማ መብራትና የፀሎት ስነስርሀት የተካሄደ ሲሆን በኦሮሚያ ደምቢዶሎ በልጅዋ ሬሳ ላይ አስቀምጠው በመደብደብ ጉዳት ያደረሱባትን ምስኪን ለመርዳት የገንዘብ መዋጮ ተደርጋል በመጨረሻም በአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ የተወያዩ ሲሆን እንደ ማህበር ምን ማድረግ እንዳለበት ተወያይተው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅዋል

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: