አዲስ አበባ በጀሞ ፉሪ ህዝበ ሙስሊሙ ድንገተኛ ተቃውሞ አደረገ!

መላው የኢትዮዽያ ህዝብ አንቅሮ የተፋው የትግራይ ወራሪ ወንበዴ ባደባባይ ሽንፈትን የተጎነጨው ሰንበትበት ቢልም በአልሞት ባይ ተጋዳይነት እየትፍጨረጨረ ይገኛል።

ይህንን የህዝብና የሀገር ጸር መንግሎ ለማጣል በሚካሄደው ትግል የኢትዮዽያ ህዝብ ዘር፣ሀይማኖት፣ቋንቋ ሳይለይ በአሁኑ ሰአት በጋራ_ጠላቱ ላይ በሙሉ አቅሙ ተነስቷል።

በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በሰላማዊ መንገድ ጸረ ወያኔ ትግሉን የጀመሩት የሙስሊም ወገኖቻችን ትግል ዛሬ ላይ በሰፊው የኦሮሞና  የአማራ ህዝብ ህብረትና አብሮነት ታግዞ በወያኔ መንደር ፍርሀትና ጭንቀትን ወልዶ የስርአቱ ቀጣይ አገዛዝ ህልም ሆኖ ቀርቷል።አሁን የተፈጠረውን አገር አቀፍ ጸረ ወያኔ ትግል በህዝብ ድል አድራጊነት ሊደመደም የብዙ ወገን መሰዋትነት ተከፍሏል።

የአዛዥናዛዥነት ህልሙ የጨነገፈበት የትግራይ ነጻ አውጭ ጉጅሌም ገሚሱ እግሬ አውጭኝ ብሎ እየፈረጠጠ ሲሆን ቀሪዎችም በቀቢጸ ተስፋ በመሳሪያ ሀይል በመፍጨርጨር ላይ ናቸው።

ይሄን ተከትሎም ቀደም ሲል ለአገዛዙ ቢጫ ካርድን በማሳየት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን ሲገልጹ የነበሩት የሙስሊሙ ማህበረሰብ በዛሬው #የኢድ በአል ላይ  ቀይ_ካርድ በማሳየት ትግሉን ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረውታል።ከሰሞኑምበተከታታይም የሞተውን የፋሽስት ወያኔ አገዛዝ ወደግብዓተ አፈሩ የመመለስ ስራ በአራቱም ያገራችን ማዕዘን ይጀመራል።

Aseged Tamene

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: