ለምዕራባውያን ፍጆታ የሚውል ወያኔ ተንኮል ሲጋለጥ

በቃሊቲ ወህኒ ቤት ከሚገኙ እስረኞች መካከል 56 የፖለቲካ እስረኞችና ሌሎች በዛ ያሉ በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በመንግስት ምህረት እንደሚፈቱ ተነግሯቸዋል ።
በምህረት ከሚፈቱት መካከልከል 31ዱ የታሰሩት ከኦነግ ጋር በተያያዘ ሲሆን 8ቱ በአርበኞች ግንባር ፣ 6ቱ ከኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ እንዲሁም 7ቱ ከግንቦት ሰባት በተገናኘ የታሰሩ ነበሩ ።የቀድሞው መንግሥት ባለስልጣን የነበሩትና ከቀይ ሽብር ጋር በተገናኘ የታሰሩት አቶ መላኩ ተፈራ ከሚለቀቁት ይገኛሉ ።
በምህረት እንደሚለቀቁ ለእስረኞቹ ከተነገራቸው በኋላ ወዲያውኑ ከሌሎች ታሳሪዎች እንዲለዩ መደረጋቸው ታውቋል ።በማህበራዊ ሚዲያዎች እንደምትፈታ ሲነገርላት የነበረችው መሪየም ሀያቱ ከእስረኞች አልተለየችም ።
ለእስረኞቹ የምህረት ወረቀቱን ይዞ በመምጣት በቀጥታ ያናገራቸውም የማዕከላዊ ፖሊስ መሆኑ ታውቋል ።ፖሊሱ መንግስት እስረኛውን በምህረት ለመፍታት መወሰኑን ለእያንዳንዱ እስረኛ መናገሩም ተሰምቷል።
እስረኞቹ በተነገራቸው መስማማታቸውን ሲገልጹም ፊርማቸውን በወረቀቱ እንዲያሰፍሩ ተደርገዋል ።
ታሳሪዎቹ ፊርማቸውን የሚያኖሩበት ወረቀት “ከዚህ በታች ስማቸው የሰፈረ ታሳሪዎች በመንግስት ምህረት የሚለቀቁ ናቸው “የሚል ዐረፍተ ነገር የተፃፈበት መሆኑን ሰምቻለሁ። በኤልያስ ከድር የክስ መዝገብ 12ኛ ተከሳሽ የሆነችው መሪየም ሀያቱ የቀረበላት ምህረት ከእርሷ ጋር የተከሰሱትን ባለማካተቱ ሳትፈርም ቀርታለች ።
በምህረት አሰጣጡ አስገራሚው ነገር ገና በቀጠሮ ጉዳይዋን በመከታተል ላይ የምትገኘውን ሀይከቱልን ማካተቱ ነው ።
በቃሊቲና በሌሎች ወህኒ ቤቶች ታዋቂው ፖለቲከኛ አንዷለም አራጌ ዝነኛው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ውብሸት ታዬና ስማቸው የማይታወቅ ብዙዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው ታስረው የሚገኙ ቢሆንም የተሰጠው ምህረት አላካተታቸውም። ይህም የተሰጠው ምህረት ለምዕራባውያን ፍጆታ እንጂ እውነተኛ አለመሆኑን ያሳያል ።Bilderesultat for qilinto fire prisnor
በፍቃዱ ሀይሉ

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: