የአማራ ተወላጅ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ ትግራይ አንሄድም አሉ!

ዛሬ ከ 800 በላይ የአማራ ተወላጅ የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም ተመድበው በሚማሩባቸው ትግራይ ውስጥ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች አንሄድም በማለት ጎንደር ላይ ተሰብስበው ነበር። የትግሬ ተማሪዎች በመላው የአማራ ክልል ውስጥ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች መልቀቂያ እየወሰዱ በትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትዕዛዝ በትግራይ ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ ተደርጓል። ትግራይ ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ተመድበው የሚማሩ የአማራ ተወላጆች ትግራይ ሄደው መልቀቂያ ሲጠይቁ ትምህርት ሚንስተር አግዷል የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። ይህን ግፍ ለሚመለከተው አካል ባፋጣኝ አሳውቀው ባያገኙም አንድም የአማራ ተማሪ ትግራይ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ለመሞት አይሄድም ብለዋል።
*በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ትግራይ ውስጥ የክረምት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የነበሩ ብዛት ያላቸው የአማራ ተወላጆች አካላዊ ጥቃትና ከእዚህ ካልሄዳችሁ እንገድላችኋለን የሚል ዛቻ እንደደረሰባቸው ፅፈን ነበር። ትግራይ ውስጥ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ የአማራ ተወላጆች እንኳን ትግራይ ሄደን እዚሁ ቤተሰቦቻችን ጋር ተቀምጠንም ለደህንነታችን በከፍተኛ ሁኔታ እየሰጋን ነው ብለዋል። በትግራይ ኗሪ የሆኑ አማሮች “ዘመዶቻችሁ መንግስትን የሚቃወሙት የትግሬ ስለሆነ ነው” በሚል ከፍተኛ እንግልት፣ ግድያና የንብረት ጥቃት እየደረሰባቸው እየተሰደዱ ነው። አሁንም “ትግሬዎች በክልላችሁ መማር ተከልክለው ወደትግራይ ለመምጣት እየተገደዱ እናንተ እንዴት በእኛ ሃገር መጥታችሁ ትማራላችሁ?!” በሚል ልጆቻችን ላይ የከፋ የበቀል እርምጃ እንደማይደርስባቸው በፍፁም እርግጠኛ መሆን አይቻልም። የትግራይ ተወላጆች “አማራን ለመበቀል” በሚል በወያኔ ታጥቀውና ተደራጅተው ጎንደር ድረስ በመዝለቅ በአማራ ሰርቶ አደር ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ ባሉበት በአሁኑ ሰዓት፣ ሃገራቸው ድረስ የሚሄዱላቸውን የአማራ ልጆች ምን ሊያደርጓቸው እንደሚችሉ መገመት አይከብድም። ስለዚህ እነዚህ አማራ ተማሪዎች ባሉበት አካባቢ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማመቻቸት አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው። የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮም አግባብ ያለውን የተማሪዎቹን ስጋት ተቀብሎ ሃላፊነቱን እንዲወጣ እናሳስባለን። ይህን ለማድረግ ፍቃደኛ ካልሆነ ግን ልጆቻችን ከድል በኋላ ባሻቸው ዩኒቨርሲቲና ዲፓርትመንት ውስጥ ተመድበው እንዲማሩ ይደረጋል።
ይህ ከታች የምታዩት የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በአማራ ክልል ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ትምህርታቸውን ይከታተሉ የነበሩ የትግራይ ተማሪዎችን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተቀብሎ እንዲያስተምር ትዕዛዝ ያስተላለፈበት ደብዳቤ ነው። በተመሳሳይ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮም ሃላፊነቱን እንደሚወጣ ተስፋ እናደርጋለን።

14012564_10205198112430990_355381106_o

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: