በኮንሶ 60 ቤቶች ተቃጥለው ነዋሪዎች ለስደት ተደርገው በከፍተኛ መከራ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ከአካባቢው ህዝብ ተነጥለው ለመንግስት ያደሩ የኮንሶ ካድሬዎች በታጣቂ ኃይል ታግዘው አባሮባ ቀበሌ አማራማ መንደር 60 ቤቶችን አቃጥለው ነዋሪዎቹ ለስደት መዳረጋቸውንና በከፍተኛ ችግር ውስጥ ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ዜጎች ቤት በተቃጠለበት ወቅት ድርጊቱን የተቃወመው አቶ አያኖ ሃልገዮ ተገድሏል፡፡
ቤታቸው የተቃጠለባቸው ነዋሪዎች ማለያ ሰገን ት/ቤት እና በጃርሶ ቀበሌ ‹‹ ሞራ›› (ሞራ- በኮንሶ ብሄረሰብ የመንገደኛ ማረፊያ ነው) ውስጥ ሰፍረው እንደሚገኙና የአካባቢው ነዋሪዎች የተቻላቸውን ድጋፍ እያደረጉ ቢሆንም ከአቅማቸው በላ በመሆኑ በተለይ እናቶች፣ ህጻናትና አረጋዊያን ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ፣የአካባቢው ምንጮች በከፍተኛ ሃዘን ስሜት ገልጸዋል፡፡
ይህንኑ ችግር ተከትሎ ተፈናቃዮቹ ካረፉባቸው አካባቢዎች የአገር ሽማግሌዎች ወደ አባሮባ ቀበሌ ስለሁኔታው ለመረዳትና ተፈናቃቹ ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ ለመጠየቅ ቢሄዱም ድርጊቱን በፈጸሙት ካድሬዎችና ታጣቂ ኃይሎች እንደተባረሩ የገለጹት ምንጮች ይህ በኮንሶ ህዝብ ለረጅም ጊዜ የተካሄደውን የአከላለል ጥያቄ ህዝቡን እርስ በርስ በማጋጨትና በመከፋፈል ጥያቄውን ለማፈን ፣እንዲሁም በቀጣይ በህዝቡ መካከል ያለውን ጠንካራ ማኅበራዊና ባህላዊ ትስስርና ቁርኝት ለማጥፋትና ጥርጣሬ ለመፍጠር ሆን ተብሎ የተፈጸመ የሴራ ድርጊት ነው በማለት አስረድተዋል፡፡
ካድሬዎቹና ታጣቂ ኃይሉ አሁንም አካባቢውን ያለቀቁ መሆኑን ምንቾቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

Bilderesultat for konso city''

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: