በደቡብ ጎንደር እብናት ከተማ ሕዝቡ የራሱን አስተዳደር መሰረተ

ኢሳት ዜና :-እየተቀጣጠለ የመጣው ሕዝባዊ እቢተኝነት አድማሱን በማስፋት በእብናት እና አርባያ ከተሞች ጨምሮ በአጎራባች የገጠር ገበሬ ማኅበራት ሕዝቡ የጎበዝ አለቃዎች በመምረጥ የራሱን አስተዳደር መስርቷል።
የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች ራሳቸውን በማደራጀት ከተማዋን ተቆጣጥረው አስተዳዳሪዎቻቸውን ከመምረጣቸውም በተጨማሪ በግፍ የታሰሩ ወጣቶችን አስፈትተዋል።
በከተማዋ ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴ የሌለ ሲሆን የመንግስት ቢሮዎችን ጨምሮ የግል ድርጅቶች ዝግ ሆነው ሕዝቡ በቤት ውስጥ ተቀምጧል።
ከዚህም ሌላ አቅም ለሌላቸው ዜጎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች ገንዘብ በማዋጣት ነጋዴዎችና ወጣቶች አስተዋጾ እያደረጉ እንደሆነ ተገልጻል።
ወጣቶቹ እብናትን ከሌሎች ከተማዎች የሚያገናኙ አውራ ጎዳናዎችን በመዝጋት እራሳቸውን ከጥቃት በመከላከል ላይ ናቸው።
የገዥው ፓርቲ ታጣቂዎች ሙሉ ለሙሉ ከከተማዋ ተጠራርገው የወጡ ሲሆን፤ ሕዝቡ ካሁን በኋላ በህወሃት ኢህአዴግ አስተዳደር አንገዛም ሲል የአቋም መግለጫ ማውጣቱም ታውቋል።

13872703_626767320820956_4233458964259478747_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: