አሳዛኝ ሰበር ዜና! ርሸናው ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተሸጋግሯል

ትላንት ቅዳሜ ነሐሴ 28/2008 ለሊት 8 ሰዓት አካባቢ መንግስት ኮሚቴዎቻችን በሚገኙበት በቃሊቲ እስርቤት በዞን 1 ውስጥ ታስረው ከሚገኙ ታሳሪዎች መካከል 2 ሰዎችን የረሸነ ሲሆን ሁለቱን ደግሞ በጥይት መቶ ማቁሰሉን ማረጋገጥ ችያለሁ፡፡ መንግስት ከትላንት በስቲያ ለሊት በቂሊንጦ ከወሰደው ዘግናኝ የቃጠሎና የግድያ እርምጃ በኋላ ምሽቱን ደግሞ በቃሊቲ እስርቤት ተመሳሳይ አሰቃቂ ወንጀል የፈፀመው ‹‹እስረኞቹ ለማምለጥ በመሞከራቸው ነው›› የሚል የሐሰት ውንጀላ ያቀረበ ቢሆንም፤ ይህ የመንግስት ውንጀላ ግን ከእውነት የራቀ መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ገልፀዋል፡፡
የተረሸኑት ሁለቱ እስረኞች ማንነታቸውን ለማጣራት እየሞከሩ እንደሆነ የውስጥ ምንጮች የዘገቡ ሲሆን፤ ሟቾቹ የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ኡስታዝ አህመዲን ጀበልና ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ባሉበት ክፍል ውስጥ የታሰሩ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የሕዝበ ሙስሊሙ ወኪሎች ግን እስካሁን ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ለማወቅ ችያለሁ፡፡
መንግስት በቅርቡ በቃሊቲ ዞን 1 እና ዞን 2 ‹‹ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ታሳሪዎች ስም ዝርዝር›› በሚል ከ140 በላይ የሚሆኑ ታሳሪዎችን ስም ለጥፎ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ቀድሞውኑ ሊረሽናቸው ያሰባቸውን አካላት አሰናድቶ ያስቀመጠው መንግስት በአሁኑ ሰዓት በየእስርቤቱ ያለምንም ሃይ ባይና ከልካይ በማን አለብኝነት ዜጎቻችንን መረሸኑን ተያይዞታል፡፡
እነዚህ እጆቻቸው ባዶ የሆኑ፣ ያልታጠቁና በሕግ ስር የሚገኙ የፖለቲካም ሆነ የሃይማኖት ታሳሪ ኢትዮጵያውያንን በጨለማ በመረሸን መንግስት እያደረገ ያለውን አረመኔያዊ ተግባር በአስቸኳይ ሊያቆም ይገባል፡፡ ወኪሎቻችን ላይ አንዲት እንኳ ችግር ቢደርስ ከችግሩ ጋር የተያያዙ አካላቶች በሙሉ ከሙስሊሙ ኢላማ ሊያመልጡ እንደማይችሉ አምባገነኑ መንግስት ማወቅ አለበት፡፡
ድል ለተጨቆኑት በሙሉ!

13819494_611651515666849_1114674654_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: