የቀድሞ የፖርላማ አባል አቶ ግርማ፣ ሳይታሰሩ አይቀርም (የትና በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ አይታወቅም)
September 5, 2016 Leave a comment
የቀድሞ የፓርላማ እና የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ዛሬ ቀን ላይ ጨርቆስ በሚገኘው ቢሯቸው አከባቢ ሲቪል የለበሱ ሰዎች መጥተው በፖሊሶች እንደሚፈለጉ ከገለጹላቸው በኋላ ወደፖሊስ ጣቢያ ማምራታቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ቢገልጹም ከዚያ በኋላ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና የት እንዳሉ እስከአሁን ማወቅ አልተቻለም።
ተንቀሳቃሽ ስልካቸው በተደጋጋሚ ቢጠራም አይመልስም። በመሆኑም አቶ ግርማ ዛሬ ታስረዋል ብሎ መገመት ይቻላል።
ባለፈው ሳምንት የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አባል የነበረው ስንታየሁ ቸኮል መታሰሩም ይታወሳል።
