አስከሬን ፍለጋ ጳውሎስ ሆስፒታል የሄዱ ቤተሰቦች በፖሊስ ተደበደቡ

በትናንትናው እለት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የተከሰተውን የ እሳት ቃጠሎ ተከትሎ እስካሁን የተረጋግጠ 49 አስከሬኖች በጳውሎስ; በፖሊስ እና በጦር ኃይሎች ሆስፒታሎች እንደሚገኙ ዘ-ሐበሻ በትናንትናው ዕለት መዘገቧ አይዘነጋም:: ይህን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸው በቅሊንጦ የታሰሩባቸው ወገኖች ዛሬ አስከሬን አሳዩን በሚል ወደ ጳውሎስ ሆስፒታል ሄደው ነበር:: ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ግለስብ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት ጳውሎስ ሆስፒታልን የ እስረኞች ቤተሰቦች አጨናንቀውት ነበር::
የሟች አስከሬኖችን አሳዩን በሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከበላይ በመጣ ትዕዛዝ የተነሳ ይህን ማድረግ እንደማይችሉ ገልጸው ቤተሰቦቹን ለመመለስ ቢሞክሩም ቤተሰቦቹ ግን አስከሬን ካላየን አንሄድም በማለታቸው ፖሊስ መጥቶ እየደበደበ ከስፍራው እንዲሄዱ አስገድዷቸዋል::
እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ከቅሊንጦ ማረሚያ ቤት የመጡ የ22 እስረኞች አስከሬን ይገኛል::
ትናንት ዘ-ሐበሻ እስረኞች ከቅሊንጦ በ20 መኪና ተጭነው መሄዳቸውን ዘግባ ነበር:: እነዚህ እስረኞች ዝዋይ; ሸዋሮቢት እና ቃሊቲ መወሰዳቸው ሲታወቅ ዛሬ ቅሊንጦ የሄዱ ቤተሰቦችም አንድም እስረኛ እዚህ የለም መባላቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል::

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: