ከህውአት ቢሮ የወጣ መረጃ .የህውአት አባሎች በዝግ ስብሰባ ተጠምደዋል።

የቀድሞው የህውአት አባልና አዳዲሶቹ የህውአት አባሎች በዝግ ስብሰባ ተጠምደዋል። በስብሰባውም ብዙ የተከራከሩበትና ያልተስማሙበትን ውሳኔ በአማራ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል አሳልፈዋል።
# በአማራ ክልል
የአማራ ክልል እንቅስቃሴ በጣም ጠንካራ እና ከባድ እንቅስቃሴ እና አስጊ ናቸው ብለው ስጋታቸውን እና ፍራቻቸውን አስቀምጠዋል። የአማራው ህዝብ የሚወሰዱት እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በአማራ ክልል በሚኖሩት አባሎች ላይ ከፍተኛ ፍራቻ እና ጉዳት እያስከተለ ነው። ይህ በእንድህ ከቀጠለ በአማራ ክልል የሚኖሩትን አባሎቻችን *ሰላዮች * ካጣን መረጃዎቻችን ማግኘት ስለማንችል ህውአት የሚባለው በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ስልጣኑን አጣ ማለት ነው። ትግሉ በዚህ ከቀጠለ ለኛ የሞት ሞት ነው በማለት በአማራው ክልል የሚደረገው እንቅስቃሴ ባለ በሌለ ሃይላችን ከአማራ ክልል መንግስት ሙሉ በሙሉ ተቀብለን በሃይል ማንበርከክ እና የተቃጣብንን አደጋ መቀልበስ አለብን በማለት ውሳኔ አስተላልፈዋል።
በሌላ ጎኑ በአማራ ህዝብ ላይ የሚወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍለንና መቀልበሻው ሊያጥረን የሚችልበት እንዳይሆን ስጋታቸውን አስቀምጠዋል። ጦሩነቱን በግልጽ በአማራው ላይ ካወጅነው ህዝብ በአንድነት እንዲነሳብን ማድረግ ይሆንብናል በተጨማሪም ብዙ ደም ከተፋሰሰ በኋላ በትግራይ ህዝብ ላይ ከባድ እና መጨረሻ የሌለው አደጋ መጋበዝ ይሆንብናል በማለት ያላቸውን ፍራቻ ተንጸባርቋል። በሁሉም ክልል በሚኖሩት የትግራይ ተወላጅ ላይ የሚያመጣው አደጋ እና ተጽዕኖ ቀላል አይደለም እንደውም የመጥፋት አደጋ በራሳችን ማህበረሰብ ላይ ማወጅ እንዳይሆንብን በማለት ስጋታቸውን በስብሰባው ተነስታል።
የሆነው ሆኖ ከ95% በላይ የህውአት አባሎች በኃይል የሚወስደው እርምጃ ላይ ተስማምቶ ከዛ በኋላ የሚመጣውን ነገር አብረን እናየዋለን የሚል አቃም በመያዝ ወደ ተግባር እንዲለወጥ መወሰድ ያለባቸው ቅድሚያ ዝግጅት ይወሰድ ብለዋል። የትግራይ ወጣቶችንም እንዲዘጋጅ ጥሪ ማድረግ እንዳለባቸውም ወስነዋል።
# በኦሮሚያ
የኦሮሚያ ጉዳይ ብዙም አያሰጋም የሚፈልጉትን ነገር ከሰጠናቸው ዝም ሊሉ ይችላሉ በዚህ ሰዓት የኦሮሞን ጉዳይ እንዲቀጣጠል ማድረግ የለብንም የጠየቁትን በሙሉ መንግስታችን እንደሚፈጽምላቸው በመናገር ማዘግየት እና ማራጋጋት አለብን ብለዋል። ነገሮች ክተረጋጉ በኋላ መልሰን እቅዳችንን ወደምናሳካበት ተግባር መሰማራት እንደሚቻል ተነግረዋል። ነገሮችን ካረጋጋ እና ወደቀድሞ ሁኔታ ከመለስነው በኋላ በኦሮሚያ ውስጥ የህዝብን ንቅናቄ ያደረጉ እና እንቅስቃሴ ውስጥ ንኪኪ ያላቸውን በሙሉ ለቅመን ዋጋቸውን እንሰጣችቸዋለን በማለት ዛቻ አዘል እና አድብቶ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እንደሚፈጽሙ ተስማምተዋል።
ሌላው በጣም የተከራከሩበትና ያጣላቸው ጉዳይ በንብረት ሃብት ጉዳይ ነው።
አማራ እና ኦሮሚያ በተነሳው ህዝባዊ አመጽ የተደናገጡት የህውአት ቢሊዬነሮችና ሚሊዬነሮች አባላት በኦሮሚያና በአማራ ሲዘርፉት የነበሩት ሃብት ስለተቋረጠባቸው ይሄ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ወደ ፊት ሊኖረን የሚችለው ድረሻ እንዴት ነው በማለት ለውይይት የቀረቡ እና ያነታረካቸውና የተለያዩበት ጉዳይ ነበረ። በከፍተኛ ሁኔታ ሃብት የምንሰበስብባቸው አካባቢዎችን ካጣን ወደ አንድ መንደር ልንገባ ነው። ነገሮቹ ተለውጠው ወደትግራይ የምንገባ ከሆነ ደግሞ የምንፈልገውን እና ሁላችንንም እንደፈለገ ሊያንቀሳቅሰን የሚችል ሃብት የለም ማለት ነው።
ለተተከሉትም ማሽነሪዎችንም ጥሬ ዕቃ አቅርቦት የሚመጣው ከትግራይ ክልል ውጪ ነው። ይሄ ደግሞ የማሽኖቹ መተከል ብቻ ዋጋ እንደሌለው እና ሳይሰሩ ከተቀመጡም ለብልሽት እንደሚዳረጉ በመጠቆም የተሰበሰበው ሃብት በምን መልኩ ለህውአት አባሎች መዳረስ እንዳለበት በተነሱት ሃሳብ ላይ ማንም ባለመስማማት ወደ ጭቅጭቅ እና ጸብ በመቀየር ሲነታረኩ ነበረ።በሌላም በኩል ከዚህ ሃሳብ ጋር ተያይዞ የተነሳው ሃሳብ በትግራይ ውስጥ ከሚኖረው የትግራይ ልጅ የበለጠው በሌሎች ክልሎች ላይ የሚኖረው ይበልጣል በቁጥ ቢቀመጥ ትግራይ ውስጥ የሚኖረው 2ሚሊዮን ሲሆን ቀሪው 3 ሚሊዮን እና የበለጠው ከትግራይ ውጪ ነው የሚኖሩት እነዚህ ከትግራው ውጪ የሚኖሩት የትግራይ ህዝቦች በከፍተኛ ሃብት ላይ ያሉና ክልላችንንም የሚረዱ ናቸው።
ይህ እንዲዚ እንዳለ ሆኖ አደጋውን መቆጣጠር ካልቻልነው ሁሉም ወደ ትግራይ ክልል የመምጣት ግዳጅ ቢጣልባቸው ከፍተኛ የሆነ የምግብ እጥረት እንደሚከሰት እና የርሃብ አደጋ ከፊታችን እንደተደቀንብን የታወቀ ጉዳይ ነው። እናም ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ እና ልንወጣው የምንችልበት አደጋ በራሳችን ላይ መጋበዝ አይሆንብንም ወይ በማለት ሃሳብ ሲንሸራሸር ነበረ። አደጋው ቆርጦ ከመጣ ምን አይነት እርምጃ መውሰድ አለብን በሚል መልስ በሌለው ጭንቀት ውስጥ ተወጥረው ነበረ።የሃብት ክፍፍሉ ላይ እንዴት ነው የምንከፋፈለው በማለት ጠንካራ ክርክር የተነሳበት የህልውና ጉዳይ በሚመስል መልኩ ሲያከራክራቸው ነበር። በዚህ ላይ ሁሉም የህውአት አባል የተለያየ ሃሳብና አቋም በመያዝ ተፈረካክሰዋል። ጸብ ቀረሽ ንግግር ሲያደርጉም ተስተውለዋል። በመላው ኢትዮጵያ የተሰገሰገው የህውአት ሃብት ምዝበራ ወደ ትግራይ ሲገቡ የሚመዘብሩት ስለሌለ ያለንን በምን መልኩ እንካፈል በሚል በመለያየታቸው አንዱ አንዱን በጠላትነት እንዲተያዩ አድርጓል ። በተቻለ ፍጥነት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ንብረቶች በሙሉ በተቻለ ፍጥነት ወደ ትግራይ ማጋዝ እንዳለበትም ተስማምተዋል።
በስተመጨረሻ ግን አሁን መጀመሪያ እድል ስላለን እንደዚህ ሰጣ ገባ ውስጥ መግባት የለብንም ሙሉውን የትግራይ ወጣት በመቀስቀስ የተቃጣብንን አደጋ መወጣት የምንችልበትን ስራ መስራት አለብን በሚለው ያልተስማሙበትና የተለያዩበትን ስብሰባ ዘግቷል።
የግሌ ሃሳብ።
ኢትዮጵያኖች ከመቸውም ግዜ በላይ በህውአት ሞት ተደግሶልናል።
በጣም የገረመኝና የደነቀኝ በኦሮሞ ህዝብ ላይ የሚያደርጉት ንቀትና በአማራው ህዝብ ላይ ለመጨፍጨፍ የተነሱበት አላማ ነው፡ የኦሮሞም ሆነ የአማራ ህዝብ ብሎም ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ከናንተ አስተሳሰብ እና ከፋፍለህ ዝረፍ፣ ከፋፍለህ ግደል፣ ከፋፍለህ ግዛ፤ ዕቅዳችሁን ካወቀ በጣም ቆይቷል። የኦሮሞ ጥያቄ የአማራም ብሎም የኢትዮጵያዊያን ጥያቄ ነው። የአማራ ጥያቄ የኦሮሞ ብሎም የኢትዮጵያ ጥያቄ ነው። የሁላችንም የኢትዮጵያ ጥያቄ ደግሞ ወያኔ በቃን ከእንግዲህ በሃላ ህዝብን አጣልተህ እና አናክሰህ መኖር አትችልም ስልጣኑን ለህዝብ አስረክብ ልቀቁ ነው መሆኑን ህዝቡ እየነገራችሁ ነው። በቃን ወያኔ ከአሁን በኋላ አይገዛንም እያለ ነው እንጂ የህዝብን ጥያቄ መመለስ ወይንም አለመመለስ መቻል አይደለም። የህዝብን ጥያቄ መመለስ አይደለም መስማት እንኳን ፍላጎት እንደሌላችሁ 25 አመት ሙሉ አይተናችኋል ስለዚህ የህዝቡን ጥያቄ የመመለሱ ሞራሉም እንዲሁም ብቃቱም እንደሌለህ ለመናገር እወዳለሁ፡ ከእንግድህ በኋላ በወያኔ ሃሳብ ተስማምቶ ወደ ሞት የሚነዳ ኢትዮጵያዊ የለም። ማንም እራሱን አድብቶ ከሚገድል ጋር ቂመኛ ከሆነ ቡድን ጋር አይደራደርም
ስማ!! ስማ!! ስማ!! የሰማ ላልሰማ ያሰማ !!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!
ሞት ለገዳይ ወያኔ!!!

12887398_560186337480034_849900704_o

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ከህውአት ቢሮ የወጣ መረጃ .የህውአት አባሎች በዝግ ስብሰባ ተጠምደዋል።

  1. yidh says:

    weregna yale minchi yemita wera isti inaayalen yeman tigil ethiopian netsa indemiyaweta oromo wey amhara, lenegeru amhara hizib min arege anteneji simetin temtawera koshasha

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: