ሰበር ዜና በገዢው ሥርዓት ህወሓት-ኢህአዴግ የተገደሉ ንፁሐን ዜጎችን ለማሰብ ብሔራዊ የኀዘን ጥሪ ያቀረቡት በቂሊንጦ የሚገኙ በዞን 1 ውስጥ ያሉ የፖለቲካ እስረኞች ጨለማ ቤት መወርወራቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት ገለጹ::

ጥሪውን በዋናነት ያቀረቡት በዞን 4 የሚገኙት 9 የፖለቲካ እስረኞች(በቀለ ገርባ፣ ደጀኔ ጣፋ፣ አዲሱ ቡላላ፣ ጉርሜሳ አያኖ፣ ዮናታን ተስፋዬ፣ ፍቅረማሪያም አስማማው፣ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ አበበ ኡርጌሳ እና ብርሃኑ ተክለ ያሬድ) ቅጣት ቤት ይገኛሉ::

እስረኞቹ ፀጉራቸውን መላጨታቸው የታወቀ ሲሆን በቅርቡ የእስረኞች ልብስ ብርቱካናማ ቀለም ያለው ቱታ እንዲለብሱ ግዴታ በመጣሉ ጥቁር ልብስ መልበስ እንዳልቻሉ ኢሳት ለመርዳት ችሏል:: ሆኖም በዞን 1 ያሉት እስረኞች ጥቁር ለብሰው በመታየታቸው ጨለማ ክፍል እንዲገቡ ተደርጓል::
የእስረኞቹን ጥሪ በመስማት በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችና በመንግሥት ተገፍተው የተሰደዱ ኢትዮጵያውያን ጥቁሩ ለብሰው ፀጉራቸውን ተላጭተው በግፍ የተገደሉ ወገኖቻቸውን አስበዋል::

በተያያዘ የእስርቤት ዜና የ እስርቤት የሌሊት ጠባቂዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው መሰወራቸው እየተነገረ ነው። ሁኔታው በመንግሥት ላይ ድንጋጤ ፈጥሮ በእስር ቤቱ ዙሪያ ግርግር እንደነበር ተገልጿል::ኢሳት ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ጥረት እያደረገ ይገኛል::በዚህ ዓመት ብቻ በጠባቂዎች ተመሳሳይ እርምጃ ሲወሰድ ለ3ኛ ጌዜ ነው::

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: