ከህወአት የደህንነት ቢሮ ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው በአማራው ስም በማህበራዊ ድህረ ገጽ እየተንቀሳቀሱ ያሉ

ጥብቅ ምስጢር14037783_10205234208373366_1048345346_o
በማህበራዊ ድህረ ገጽ በስፋት በቤተ አማራ ስም ስማቸው በተደጋጋሚ የሚነሳው ሁለቱ ግለሰቦች ማለትም መልከ ሀራ እና የሰሜን ኮከብ ከህወአት የደህንነት ቢሮ ከፍተኛ በጀት ተመድቦላቸው በአማራው ስም እየተንቀሳቀሱ ሌሎች ብሄሮችን እና የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎችን በመዝለፍ የተጀመረው ህብረት እውን እንዳይሆን በርትተው እንዲሰሩ ግዳጅ እንደተሰጣቸው ከደህንነት ቢሮ አፈትልኮ የወጣ መረጃ አጋለጠ።ይህም እንዳይታወቅ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኩል ሁለቱን ገለሰቦች በሚመለከት በማህበራዊ ሚዲያ ሽብር የሚነዙ ጥላቻን የሚያራግቡ ተብሎ መወራቱ ይታወቃል።የደህንነት ቢሮው ይህን ያደረገው ግለሰቦቹ በመንግስት በዚህ መልኩ ከቀረቡ ከተቃዋሚዎች ብዙ መረጃ ሊያገኙ ይችላሉ ከሚል እና ከጥርጣሬ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጎ የተሰራ ማደናገሪያ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።
እነዚህ ግለሰቦች በብዛት የግንቦት ሰባትን ንቅናቄ እና የንቅናቄውን መሪ የዶ/ር ብርሀኑ ነጋን ስም እንዲያጠፉ እና በህዝቡ ያላቸውን ተቀባይነት ለማሳጠት እና እምነት እንዲያጣ በስፋት የሚንቀሳቀሱ መሆናቸው ይታወቃል።ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ አርበኞች ግንቦት 7 ጸረ-አማራ ናቸው ከማለት ጀምሮ እንደ ህወአት ሁሉ የኤርትራ ተላላኪ ናቸው በማለት በከፈተኛ የስም ማጥፋት ስራ ላይ ተጠምደዋል።ዛሬም በማህበራዊ ድህረ ገጻቸው የጀመሩትን የበሬ ወለደ ዜና አርበኞች ከግንቦት ሰባት ተነጠለ ሲሉ ወሬውን በስፋት አሰራጭተው የተጀመረው ትግል እና የአንድነት መንፈስ ወደኋላ የሚጎትት የመሰላቸውን ነገር ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ።ቀደም ሲልም ታጋይ ተስፋሁን አለምነህን ግ7አሳፈነው የሚል የፈጠራ ወሬ ሲያናፍሱ እንደነበር ይታወቃል።
መልከ ሀራ የተባለው ፌስቡከኛ ቀደም ሲል የቤተ አማራ ተወካይ ነኝ ሲል የነበረ ቢሆንም ድርጅቱ ባደረገው መፈንቅለ ምርጫ በሌላ ተተክቷል።
የሰሜን ኮከብም በተመሳሳይ የግለሰቦችንም ሆነ የብሄሮችን እኩልነት የማይቀበል በአማራው ስም ቂምና ጥላቻን በማህበራዊ ሚዲያ ከማሰራጨት አልፎ በተለያዩ ሰአት እገሌን ለገደለ 50000 ብር እከፍላለሁ በማለት የህዝቡን ባህል እና እምነት በሚጋፋ መልኩ ወንድም ወንድሙን እንዲገድል ወራዳ ተግባርን እየፈጸመ ይገኛል።ከዚህ አንጻር ተነስተን ስንገመግመው እነዚህ ሰዎች ከህወአት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ የሚያሳይ እንዴውም ራሳቸው ቢመቻቸው ለገንዘብ ሲሉ ሰዎችን ከመግደል የማይመለሱ በመሆናቸው ሁላችንም ይህን የጥፋት መንገዳቸውን ተረድተን ሀይ ልንላቸው የገባል።
አርበኞች ግንቦት ሰባት የሀገራችን የተጠራቀመ ችግር ወያኔን ብቻ በመጣል ይፈታል ብሎ ስለማያምን ነገ የምትመሰረተው ኢትዮጵያ በህዝቦች መፈቃቀር እና እኩልነት ላይ የታነጸች እንድትሆን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ተቀራርበው በጋራ እንዲሰሩ በሩን ልድርድር እና ለውይይት ክፍት በማድረግ ሩቅ አልሞ የሚንቀሳቀስ ተስፋ የተጣለበት ድርጅት ነው።
የነ መልከሀራ እና የሰሜን ኮክብ ጠላት እንግዲህ ህወአት ሳይሆን አግ7 የሆነበት ምስጢር ምን ይሆን?
ከዚህ ስም ጀርባ ማን አለ?ለምን ከአማራው ስም ውጭ ሌላው እንዲነሳ አይፈልጉም?
እውነተኛ ዲሞክራሲ የሰፈነባት፥የአማራው ጥቅሙ እና ድህንነቱ የተጠበቀባት ኢትዮጵያ እንዳትኖር ለምን ፈለጉ?መገንጠል የአማራው ህዝብ ጥያቄ ነው ወይ?ሌሎች አማራጮችስ የሉም ወይ?
እነዚህ ጥያቄዎች እና ቤተ አማራ የሚያራምዷቸው አቋሞች በደንብ ሊቃኙ የሚገባቸው ናቸው።
ድል ለሰፊው ህዝብ!
ሞት ረግጠው መግዛት ለሚፈልጉ አንባገነኖች!

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: