የአዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ዶክተሮች የፍራቻውን መጋረጃ ቀደዱት !!!

የተማረ ይግደለኝ ይልሃል ደጉ ህዝባችን እሱ እየተራበና ባለመማሩ ሞቱን ከሞት በላይ እየተመኘ፡፡ አለመማር የብዙ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስንክሳር መብዛት ምክንያት እንጅ በራሱ የመጣ የስራ ግብር መገለጫ አለበዚያም የሂዎት እጣ ክፍል አይደለም ፡፡ ህዝብ ያልተማረ የሚሆነው አዕምሮ ስለሌለው፣መማር ስለማይፈልግ፣ለትምህርት ያለው ግንዛቤ አነስተኛ ሆኖ ሳይሆን የመማር እድሉን በተለያዩ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ምክንያት ስላጣው ብቻ ነው፡፡ ያም ሆኖ ግን እሱ ያመለጠውን የትምህርት እድል ልጆቹን በማስተማራ የትምህርት ቁጭቱን የተበቀለ ወገናችን አያሌ ነው ፡፡ ያም ሆኖ ግን የአገራችን 85% ህዝብ አርሶ አደር ሲሆን ከዚህ ውስጥም አብዛኛው በወጉ ያልተማረና ሂዎቱን በከፍተኛ ማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ ብሎም ኢኮኖሚያዊ ጫና ውስጥ ከቶ እሱ ሳይኖር ገዥህ ነን የሚሉትን እየተጠማ ያጠጣል፣እየተራበ ያበላል፣እየታረዘ ያለብሳል፣እሱ እየሞተ እነሱን ያኖራል ፡፡

ለመግቢያ ያክል ስላልተማረውና ስለተማረው ማህበረሰብ ያሉ የስነልቦና እና የማህበራዊ አኗኗር ጥቂት ለማለት ወወድሁ እንጅ ዋናው ሀሳቤ የሚያጠነጥነው ግን ስለ አዲስ አበባ የጥቁር አንበሳ ዶ/ክተሮች ለህዝብ ያላቸውን ወገንተኝነትና አጋርነት ጥቂት ለማለት ወድጀ ነው፡፡

ምክንያቱ ደግሞ ሳይማር ላስተማራቸው ነገር ግን በግፍ አየሞተ ላለው ወገናቸው ሞትህ ሞታችን ነው፣ጥያቄህ ጥያቂያችን ነው ብለው በእርግጥም በመማራቸው የወያኔን እኩይ ሴራ ጠንቅቀው ቢረዱትም የእኛ ሞት ከህዝባችን ሞት አይበልጥም ብለው የፍራቻ ግንቡን ስለናዱትና አጋርነታቸውን ስላሳዩን ነው፡፡

አዎ በአሁን ስዓት ኢትዮጵያኖች በወያኔ ቅልብ አልሞ ተኳሾች እያለቁ ይገኛሉ ይህም የሆነው መሞታችን ይብቃ፣ ኢትዮጵያ የኛም ናትና ማንነታችን ይከበር፣ከእርስታችን ያለምንም በቂ ድጎማና ምትክ እየተነሳን ስርዓቱእና የስርአቱ ጉምቱ ባለስልጣናት (ወያኔዎች) ኪሳቸውን እያደለቡበት ነው፣የራሳቸውን ዜጋ እያመጡ እያሰፈሩበት ነው ብለው በሰላማዊ መንገድ ድምፃቸውን በማሰማታቸው ብቻ ሞተዋል ከአገራቸው ተሰደዋል፡፡ ታዲያ በዚህ ሳይማር ባስተማራቸው፣እሱ እየሞተ እነሱ ግን እንዲገሉት ፍቃደኝነቱን የገለፀላቸው የተማሩ ዶክተሮች የኦሮሞና አማራ ወንድሞቻችን ግድያ ይቁም ብለው ወያኔን በሰላማዊ መንገድ ድምፅ በማሰማት መጠየቃቸው በእርግጥም የምሁራንን የፍራቻ ቆፈን ያፍታቱ ትክክለኛ የህዝብ ልጅነታቸውን ያሳዩ በመሆናቸው ልናመሰግናቸውና ከዚህ በላይ በመላ አገሪቷ ያሉ ምሁራኖች በአንድ ላይ በመሆን ድምፃቸውን እንዲያሰሙ እንጠይቃለን፡፡

አንባ ገነኑ የወያኔ መንግስት በእብሪት እና በማን አለብኝነት ለድፍን 25 አመታት ሲገዛ ዜጎች እርስ በእርሳቸው እንዲጠላሉና እንዳይስማሙ አያሌ የሴራና ደባ ስራ ቢሰራም እነዚህ ከኢትዮጵያ አብራክ የወጡ ወንድሞቻችን አንድነትን ሰብከዋል፣የፍራቻና ይሉኝታን ፀሊም መጋረጃ ቀደዋል፣ ስርአቱንም እንዲበቃው መክረዋል በመሆኑም ሳይማር ላስተማራቸው ወገናቸው አጋርነታቸውን ዘግይተውም ቢሆን መግለፃቸው ይበል ያሰኛልና ልናመሰግናቸው ይገባል፡፡

ኢትዮጵያዊያነን ከዚህ ሊማሩ የሚገባው ነገር በአንድነት ሊመክሩና አንባ ገነን ስርአቱን ሊያስወግዱ ይገባል እንጅ በተናጠል ፖለቲካ የትም ሊደረስና ለውጥ ሊመጣ እንደማይችል አብዝተው ሊገነዘቡ ይገባል በመሆኑም የደቡቡ፣የሰሜኑ፣የምስራቁና የምዕራቡ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በተመሳሳይ ስአትና ግዜ ሆ ብሎ በመነሳት ለስርአቱ እግር እሳት በመሆን አንባ ገነኑንና ዘረኛውን የወያኔን መንግስት አስወግዶ ነፃና እኩልነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ሊመሰርት ይገባል፡፡

ወልቃኢት የአማራ ምድር ሲሆን ህብረተሰቡም የአማራ ማንነት ያለው ነው፡፡

እኔም ኮ/ር ደመቀ ነኝ!!!

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ

ሞትና ውርደት ለወያኔና ተላላኪዎቹ፡፡

 aseged tamene photo
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: