ህወሀት 12ኛዋ ሰአት ላይ ተቀምጠው የንጹሀንን ደም ያፈሳሉ።

አንባገነኖች እውር እና ደንቆሮም ናቸው። ከታሪክ የምንረዳው ይህንኑ ድንቁርናቸውን ነው። ሁሉም አንባገነኖች 12ኛዋ ሰአት ላይ ተቀምጠው የንጹሀንን ደም ያፈሳሉ። ሌላም ወንጀል ይፈጽማሉ። እራሳቸውን አዙረው ማየት እና መመርመር ግን አይችሉም። እነሱ ከህግ በላይ ሆነው ይሰየማሉ። እነርሱው ገድለው ህዝብን ሲከሱ ይገኛሉ። ይህን የዛሬ አራት እና አምስት አመታት በሙባረክ፣ በጋዳፊ አይተነዋል። ይቅርታን አለመፈለጋቸው ከሁሉም ያስገርማል። እናም የመጨረሻዋ ሰአት ስታልቅ ከልክ ያለፈ ፍርሀታቸውን እናያለን። የሁሉም አንባገነኖች ፍርሀት አንድ ነው። ሂትለር እና ሞሶሎኒ የአንባገነኖች ሁሉ ደቀመዝሙራን ነበሩ። ከእነርሱ በኋላ የተነሱ አንባ ገነኖች ሁሉ የእነርሱን ጭካኔ እና አረመኔነት ገልብጠው ይጠቀሙበታል። ሕዝባቸውንም ሰብአዊ እና ተፈጥሮ የሰጠችውን ነጻነት ይገፉታል። የመጨረሻ ሰአት ቀርባ ንስሀ ሳይገቡ እንደተርበተበቱ ያልፋሉ። ሞሶሎኒ ከሕዝቡ ባለፈ በአለም ህዝቦች እና በተለይም በኢትዮጵያ የፈጸመው በደል ልክ እላፊ ነበር። ሒትለርም እንዲሁ። የሁለቱ አንባገነኖች ህልፈት ታሪክ እንዳስተማረን የፍርሀት ቆፈን ተላብሰው አልፈዋል። በአንቀጠቀጡት ሕዝብ ፊት ተዋርደዋል። ሞሶሎኒ ከሴት ጓደኛው ጋር ተዘቅዝቆ ነው የተንጠለጠለው። ሒትለር የሳነአይድ የመርዝ እንክብል ውጦ ህይወቱ አለፈች። ላለማየት እና ጠላቶቹን ፊት ለፊት ገጥሞ እነርሱን ገሎና በጠላት ጥይት አይደለም የወደቀው። ይህ የመጨረሻ ፈሪነትን ያሳየናል።
የትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች የመሶሎኒ እና የሂትለር ግልባጭ ናቸው። ሂትለር የጀርመን ናዚ ፓርቲን ጸረ ይሁዳውያን አቋም እንዲይዝ አደረገ። 6 ሚሊዮን ይሁዳውያንንም ገደለ። የአገዳደሉ አይነት እና ልክም የተለያየ ነበር። የትግራይ ጠባብ ቡድን የመጀመሪያ አቋምም ይኸው ጸረ ሕዝብ የሆነ እና በዘር ላይ የተመረኮዘ ነው። የትግራይ የበላይነትን የማስጠበቅ ስራ ነው የሚሰሩት። ያንን ለማድረግ ዘርን ከዘር ማጋጨት። ሌሎችን በጠላትነት መፈረጅ ብሎም መግደል እና ማሰቃየት ነው። ይህን ሁሉ በ25 አመታት ተግባራዊ አድርገዋል። ሕዝብ እና ሀገር ለንስሀ በቂ ግዜ ለግሳቸው። ግን አለሆነም የመጨረሻ ጽዋን ለመጋት ልክ እንዳለፉት ዘረኞች፣ አንባገነኖች ሁሉ በጎዳና ላይ ናቸው።
ባለፉዉ ሳምንተት የአዘዞ የጦር ካንፕ የመሳሪያ መጋዝንን መሳሪያውን ተገፏል። ጎንደር ፒያሳ አደባባይ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ተሰቅሏል። የዚህ ትውልድ አርበኞች እንደያ ትውልድ ጀግኖች ዳግም ጀግንነትን አሳይተዋል። ይህ ድል እና ትግል ቀጣይ ነው። በድርቦታቦር፣ ማክሰኝት፣ አዲስ ዘመን፣ ጋይንት በአርማጭሆ፣ በጭልጋ ትግሉ ፍሟል። የዚህ ትውልድ ጀግኖች አይበገሬነታቸውን በትግል አውድማው ቆመው አሳዩን።
ይህ ትግል
በባህር ዳር እና መላ ጎጃም እየተፋፋመ። የአዲስ አበባ ተርብ ወጣቶች የዚህ ትውልድን የጎንደር አርበኞች ፈለግ ይከተሉ ዘንድ ጥሪ እየቀረበላቸው ነው። ይህን ታሪካዊ ጉዞ ያመለጠው ሁልጊዜ የበታችነት ስሜት ይዞት ይኖራል። አያምልጣችሁ።
በኦሮሚያ ጀግና ታጋዮች እየትካሄደ ያለው የሞት እና የሽረት ትግልም ቀጥሏል። ይህ በአይነቱ ልዩ የሆነው የዚህ ትውልድ የኦሮሞ ልጆች ተጋድሎ ድፍን አመቱን ዘልቆ ሌላ አጥቢ ላይ ነው። የህኛው አጥቢያ ግን የድል እንደሚሆን መጠራጠር የለብንም።
የትናንቶቹ አርበኞች የነአሞራው ውብነህ፣ የነበላይ ዘለቀ፣ የነገረሱ ዱኪ
የ60 ወቹ ወጣት አርበኞች ለአመኑበት የወደቁት ጎንደር ማሩ ሰማ፣ ሄኖክ አማረ፣ ዘዋለ ዘገየ ዛሬ ብዙ ሽህ አርበኛ ወጣት ትውልድ ተነስቶ እምቢ ለሀገሬ ሲል ቢያዩ ምን ያህል በተደሰቱ። የእነርሱ የጀግንነት ታሪክ ዛሬም እየተደገመ ነው።

ሞት ለሕወሐት/ኢሕአዴግ እና መጋዣ ተከታዮች !!!!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!!!
አንድነት ሀይል ነው !!!!!

13925404_701627863308854_2282274968808861391_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: