ከአንድነት ውጭ ያለው መንገድ ባርነትን ማስረዘም ነው

አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት አጣብቂኝ አውጥቶ ወደ ምንፈልገው የነፃነት፣ የእኩልነትና የመከባበር ዘመን ለመሻገር መላው የአገራችን ህዝቦች አንድ ሆነን ወያኔን ከመፋለም የተሻለ አማራጭ የለንም። በተለያዬን ቁጥር የተዳከመውን የወያኔ ስርዓት ተጨማሪ አየር እንዲያገኝ እድል ከመስጠት ውጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ ይዞ ይመጣል ብሎ መመኘት የመከራን ዘመን ማራዘም ነው። የአማራ የማንነትና የህልውና ጥያቄ፣ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት ትግልና ሌሎችም የአገራችን ህዝቦች መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት በሰለጠነ መንገድ መቀራረብ፣ መነጋገርና አንድ ሆኖ በመታገል ወደ ጋራ የነፃነትና የፍትህ ዘመን መጓዝ መተኪያ የሌለው መንገድ ነው። በአገራችን ውስጥ ባለፉት 25 ዓመታት የተፈጠሩት የፓለቲካ ድርጅቶች ዋና መነሻ የራስን ማንነት በማስቀደም በመሆኑ የተነሳ የተፈለገውን እርቀት ሳይጓዙ ተፍረካክሰው ቀርተዋል። ስለዚህ ወያኔ በግለሰብ ደረጃ ፓርቲ አቋቁሞ የዘረፋና የጥፋት ዘመኑን ለማራዘም ሲሯሯጥ እኛም እሱ በቀደደልን ቦይ ገብተን መፍሰስ በጥፋት ጎርፍ ተጠርገን ከመወሰድ ውጭ ብዙም ፋይዳ የለውም።
አሁን በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተጀመረውን የነፃነት ተጋድሎ ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ሁሉም የአገራችን ህዝቦች አንድ ሆነው መቆም አለባቸው። በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ያለን ትውልዶች ወደ አስራ ሶስተኛውና አስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ሄደን መኖርና ማሰብ የለብንም። ዓለም አንድ እየሆነ በሄደበት ዘመን ልዩነትንና ብቸኝነትን መዘመር አዋጭ መንገድ አይመስለኝም፣ ደግሞም አይደለም። ይህን ስል እንደ አማራ ልጅነቴ ሌሎች የአማራ ወንድሞቼ የሚሰማቸውን የአማራ በደልና ጥቃት ብሎም ወያኔ በአማራ ህዝብ ላይ በስውር ያወጀውን የዘር ማጥፋት ስትራቴጅ ሳልረዳ ቀርቼ አይደለም። ነገር ግን አሁን ከሚታየው የአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ለብቻችን ተነጥለን የምናደርገው ትግል ረጅም መንገድ አያስኬደንም። በመሆኑም መላው የአማራ ህዝብ ከኦሮሞ ወንድሞቹና ሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ጋር ተሰልፎ የተጀመረውን ወያኔን የማንበርከክ ትግል ማቀጣጠል አለበት። በአማራ ክልል የተጀመረው የማንነትና የህልውና ተጋድሎ የሌሎች ኢትዮጵያዊ ወንድሞቹ ድጋፍ ያስፈልገዋል፣ በኦሮምያ የሚደረገው ትግልም እንዲሁ። አሁን ያለንበት ጊዜ የሚጠይቀው አንድነትን እንጅ መለያየትን አይደለም። በአጠቃላይ በሰው ልጆች እኩልነትና ነፃነት ላይ የተመሰረተች አዲሲቷን ዲሞክራሲያዊት አገር ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሁሉም የአገራችን ህዝቦች የተቀናጀ ትግል መተኪያ የሌለው መሳሪያ ነው። በመሆኑም ከአንድነት ውጭ ያለው መንገድ ባርነትትን ከማስረዘም የዘለለ ፋይዳ ስለማይኖረው መላው የአገራችን ህዝቦች የጋራ ጠላታችን በሆነው ወያኔ ላይ በአንድነት እንነሳ። ነፃነት ለሃበሻ

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

አንድነት ኃይል ነው!!!
ድል ለመላው የአገራችን ህዝቦች!!

13718112_608021232696544_729113258_o

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ከአንድነት ውጭ ያለው መንገድ ባርነትን ማስረዘም ነው

  1. Lopez says:

    Living with TPLF is worse than brain cancer. All must take a piece from them we may opt for lasting enslavement. Now, Amara & Oromo have joined to stand in unison to free themselves, where are Wolytas? Where are the Sidamas? What happen to Guraghes? Where are the Ogadenis? Extend invitations to all once and for all. Strike throughout! Walk out everywhere in solidarity. March as one nation to resist slavery in own land. Chant March demand full rights. Refuse to be cheated, ruled by the most cruel elements that are devoid of humanity. Demand election now! Election without harassements, without fake boxes full of bogus ballots. TRUE & DEMOCRATIC ELECTION IS THE ONLY SOLUTION TO THE CURRENT IMPASSES. BRAVO AMHARA-OROMIA solidarity.

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: