ለአንድ ቀን የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ብትሆኑ . . . (አሌክስ አብርሃም)

ይህ ቀጥሎ የምታነቡት አንቀፅ ከአንድ ፅሁፌ ላይ የተቀነጨበ ነው ….እንግዲህ መግቢያውን እኔ ከፃፍኩት እስኪ እናተ ለአገር ይጠቅማል የምትሉትን የፈለጋችሁን ምክር ፃፉ …ለአንድ ቀን የጠቅላይ ሚንስትሩ አማካሪ ብትሆኑ ልትሉ የምትፈልጉትን ሃሳብ . . .ይሄው ሜዳው ….ሰሚ ኖረም አልኖረም የፈለጋችሁን ትመክሩ ዘንድ እድሉ ተሰጥቷችኋል…

***** ***** *****
መልካም እንግዲህ እኔ አሌክስ አብርሃም የተባልኩ ግለሰብ ….በዚቹ በተከበረች በተፈራች ራሷም በፈራች አየሯና ኑሮዋ ውድ በሆነ መልከአ ምድሯና ሴቶቿም ውብ በሆኑበት …ከስልጣንና ከድህነት ቶሎ በማይወጣባት ታሪካዊ አገር ተወለድኩ! የልደቴን ቀን እርግጡን አላውቀውም …ብቻ እኔ የተወለድኩ ቀን ለትጥቅ ትግሉ ሲባል(( ከጨካኙና ከፋሽቱ የደርግ ባንክ የተዘረፈ)) አንድ ጆንያ ብር የተጫነበት የህወሃት አህያ ወንዝ ሊያቋርጥ ሲል ውሃ ወስዶት ቆይቶ ጫካ ጫካውን እያቆራረጠ ወደታጋዮች መንደር የተመለሰበት ታሪካዊ ክስተት ተፈጥሮ ነበር እየተባለ ሲወራ ሰምቻለሁ …እንግዲህ አስሉታ …ብሩን ሳይሆን እድሜየን! ብሩማ ያው ((ከባንክ ወደባንክ ነው ብሎናል አነዴ ያየነው ዶክሜንተሪ ፊልም !))! ዛሬ ላይ ሁኘ ያ ዘመን ምን ያህል ደግና እንኳን ሰው አህያው ለአገር አሳቢ እንደነበር ሳስበው እንደአንዲት ታዋቂ የአገራችን ተዋናይት ‹‹ይች አገር ወዴት እየሄደች ነው ›› ብየ ብስጭት ብጤ በለጭ በለጭ በለጭ ይልብኛል!!

እውነቴን ነው ክቡርነተዎ…እግዜር ያሳይዎ …ያኔ አህያው የተዘረፈ ብር ይዞ ጠፋና ቆይቶ ሲያስበው ሲያስበው ‹‹ይሄን ከህዝብ ባንክ የተዘረፈ የህዝብ ብር ይዠ ወደውጭ አገር ብጠፋ ቢበዛ የለት ግጦሽ ነው…ህዝቤ መሃል ሁኘ አመድ ላይ ብንከባለል ይሻላል›› ብሎ በአህያ ልቦናው በማሰብ ብሩን ይዞ ተመለሰ ….ዛሬ ዛሬ ያሉ ዘራፊዎች ግን የዚህን አህያ ያህል እንኳን ማሰብ የተሳናቸው ጉዶች ናቸው …ብር ጭነው ከጠፉ ጠፉ ነው አይመለሱም!! እውነቴን ነው ከዚህ አህያ መማር አለብን …..አህያ ቀላል ነገር መስለዎት እንዳይንቁት ጌታየ …በድሮ ዘመን በለአም የሚባል ነብይ ኢስራኤልን ሊረግም አህያውን ጭኖ ሲወጣ አህያው ናት ያስቆመችው ! ካላመኑ መፅሃፍ ቅዱስ ላይ ታሪኩ አለ!
እንግዲህ ይህን ያህል ካልኩ ….. እንደብዙዎቹ አማካሪዎችዎ የቤተ መንግስትዎትን ደጅ ሳረግጥ የለት ጉርስ ሳይሰፈርልኝ ያመት ልብስ ሳይቀደድልኝ ….ለአገሬና ለህዝቤ ስል ቀጥሎ ያለውን ጠቃሚ ሃሳብ ለማማከር እወዳለሁ ….ልብ ብለው ይስሙኝ …..

aseged

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: