በአቶ ሀብታሙ አያለው ላይ በግላጭ የሞት ቢይን ተላለፈ!!

በሞት የተቀጣ ወንጀለኛ እንኳን የሞት አፈፃፀም ተግባራዊ እስክሆን ድረስ በበሽታ፣ በሥጋት ወዘተ እንዲሰቃይ አይደረግም፡፡ ሀብታሙ ወንጀለኛ አይደለም፡፡ በህግም፣ በሰውም በፈጣሪ ዘንድም ንፁሁ ሰው ነው፡፡ ዛሬ በሀብታሙ ላይ የተላለፈው የሞት አፈፃፀም << # ተሰቃይቶ እንዲሞት>> የሚል ነው፡፡
በጽኑ ህመም ላይ የሚገኘው አቶ ሀብታሙ አያሌው ወደ ውጭ ሀገር ወጥቶ ይታከም ዘንድ በህግ አግባብ ጥያቄ መቅረቡ ሐቅ ነው፡፡ ብዙ ክርክሮችም ተካሂዷል፡፡ በተጨማሪም ሰብዓዊነት የሚሰማው አብዘኛው የኢት/ያ ህዝብ ኢህአዴግን ሲማፀን መሰንበቱም ይታወሳል፡፡ ሀብታሙ ህክምና የማግኘት መብት ዙሪያ በሰብዓዊነትም ሆነ በዴሞክራሲያዊ ድንጋጌዎች የተጠበቀ መሆኑን አስመልክተው የተለያዩ የህግ፣ የጤናና የፖለቲካ ባለሙያዎች ጠንከር ያለ አስተያየትና ትንታኔ ሲሰጡ መቆየታቸው፤ የተቀሩቱ ደግሞ እንደየሃይማኖታቸው ለፈጣሪያቸው ፀሎት ሲያደርሱ መሰንበታቸውም አይዘነጋም::
ባጠቃላይ ህክምና የማግኘት መብቱን መነፈጉ ግን ሰብዓዊነት ለሚሰማው ሁሉ ልብን ያደማ መሆኑም ግልጽ ነው፡፡ ከብዙ ብዙ ውጣ ውረድ፣ ልመና፣ እንባና እንግሊት በኀላም ቢሆን ፍትህ እንዲያኘኝ ሁሉን ጥረት አድረገናል፡፡ ግን ዛሬ ልሳካልን አልቻለም፡፡ ውሳኔው ከህግ ገበታ ሳይሆን ለሀብታሙ ከተማሰለት ከጥልቁ ጉድጓድ በመሆኑ ያቀረብናቸው የህክምናና የህግ ሠነዶች ሁሉ ዋጋ አጥተዋል፡፡
ከካዲስኮ አጠ/ይ ሆስፒታል እና ከጤና ሚ/ር ማብራሪያ አምጡልን በማለት # ለመስከረም 25ቀን 2009 ዓም ሌላ ተጨማሪ ቀጠሮ ተሰጠን፡፡ አይ ቀልድ!!! የተባለው ማብራሪያ ከምር አስፈላጊ ቢሆን እንኳ በየቢሯቸው እየዞርን ማብራሪያ መጠየቅ የእኛ ኃላፊነት አይደለም፡፡ ስለዚህ በእኔ እምነት ጉዳዩ ዛሬ እልባት አግኝቷል፡፡ በርግጠኛነት ሀብታሙ ላይ ሠይጣናዊ ውሳኔ መወሰኑን ስላረጋገጥን በዚህ ጉዳይ ፍትህ ለማግኘት ዳግም ወደ ፍ/ቤት ላለመላለስ ወስነናል፡፡ በቃን!!!
የምቀረን የኢ/ያ ሕዝብንና የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ምላሽን መጠበቅ ነው የሚሆነው፡፡
ሀብታሙ ፍትህ ለማግኘት ይህንን ያህል ወርዶ መለመን አለበት?? ለምን? ዛሬም ጥያቄዬ ይህ ነው፡፡
<<… ስለዚህ አቶ ሀብታሙ ያጣው አንድ ነጠላ ፍርድን ሳይሆን ህይወቱን ነው፡፡ ነገ ሁላችንም ተመሳሳይ ዕጣ ነው የምጠብቀን !!>>
ኢህአዴግም የምታመጡትን እስቲ አምጡ በማለት በትዕቢት እየፎከረ ይገኛል፡፡
በቃ!!!!!

13872703_626767320820956_4233458964259478747_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to በአቶ ሀብታሙ አያለው ላይ በግላጭ የሞት ቢይን ተላለፈ!!

  1. Ras Dejen says:

    Why Ethiopians are so fearful? Why have they not inherited heroism and dying for human values?
    Why aren’t they daring to kill the criminals?
    Why do they die without attempting killing their enemies?

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: