ሕወሃት ለጎንደሩ ሰልፍ በፋና በኩል ንቀቱን ገለጸ (ግርማ ካሳ)

የብአዴን ሜዲያ የጎንደሩ ሰልፍ ፍጹም ሰላማዊ መሆኑ፣ ሰልፈኞቹ ያቀረቡ ጥያቄዎችን ለክልሉ አስተዳዳሪዎች እንዳቀረቡ በመግለጽ ፣ በሰልፉ የነበረዉንም ሁኔታ የሚያሳይ ቪዲዮም በመለጠፍ ነበር ዘገባውን ያቀረበው።

ሆኖም ሕወሃት በፋና ራዲዮ በኩል ለዚህ አስደዳሚ የሕዝብ ትይንት ግን ያለውን ትልቅ ንቀት እንደገና አሳይቷል። በፋናና በኢቢሲ በኩል ህወሃቶች የጎንደር ሕዝብን የሻእቢያ ተላላኪዎችና አሸከሮች እያሉ ሲሳደቡ እንደነበረ ይታወቃል። ሕዝቡ፣ እውቅና አልተሰጠም ተብሎም ማንም እውቅና የመስጠትና የመፍቀድ ስልጣን በሕግ መንግስቱ አልተሰጠውም በሚል፣ በተደራጀና አስደናቂ በሆነ መልኩ ድምጹን ከማሰማት ግን አላፈገፈገም።

በጎንደር የተለያዩ መፈክሮች ይሰሙ ነበር። ” በሰልፉ የሀገሪቱ ሰንደቅ አለማ ያልሆኑ አርማዎችን ከመያዝ ጀምሮ ሌሎች ህገ መንግስቱን የጣሱ እና የሀገሪቱን አንድነት የመሸርሸር አላማ የነበራቸው ጥያቄዎች እና ድርጊቶች መታየታቸውንም ።” ሲል ነበር ፋና የጻፈው።

ፋና የወያኔ ምልክት የሆነው ሰማያዊ ኮከብ የሌለበት አረንጓዴ ቢጫ ቀን ሰደንቅ አላማችንን ነው እንግዲህ “የአገሪቱዋ ሰንደቅ አላማ ያልሆነ” የሚለው።

ፋና አቶ ንጉስይ የተባሉ የክልሉ መንግስት የኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን በመጥቀስ ነው ይሄንን ዘገባ የሰራው። ሆኖም ግን አቶ ንጉሱ በሚመሩት የአማራው ክልል ሜዲያ በኩል ግን ፋና እንዳለው የተናገሩት ነገር የለም። ፋና አቶ ንጉሱ ያላሉትን አሉ ብሎ ሳይዘግብ እንዳልቀረም ይገመታል። በነ ፋና “እገሌ እንዲህ አለ” ተብሎ የሚቀርብ ዜና፣ በኦዲዮና በቪዲዮ ካልተደገፈ በቀር ማመን አስፈላጊ አይደለም። በአሁኑ ጊዜ አብዝኛው የባደነ አባል ከሕዝቡ ጎን የተሰልፈበት ሁኔታ ነው ያለው። ህወሃት በብአዴኖች ዘንድ መከፋፈል እንዲኖር እስከ መጨረሻ ደም ጠብታ መንፈራገጡ አይቀርም።

13886393_1847156028850945_2302386033266202402_n

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to ሕወሃት ለጎንደሩ ሰልፍ በፋና በኩል ንቀቱን ገለጸ (ግርማ ካሳ)

  1. leave this trash-media. ” yamedam were new”

    Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: