ሰበር ዜና . . . የብሄራዊ መረጃዉን ዳይሬክተር ጌታቸዉ አሰፋን ፎቶ ግራፍ አንስቶአል የተባለዉ የደህንነቱ ክፍል የጥበቃ አባል በቁጥጥር ሰሮ ዉሎ የደረሰበት አልታወቀም።

ጌታቸዉ አሰፋ ብሄራዊ መረጃን በበላይነት መምራት ከጀመረበት ወቅት አንስቶ የእርሱን የፎቶ ግራፍ መረጃዎች በተመለከተ ከተለያዩ የኮምፒዉተር ኔት ወርክ ገጾች እና የግለሰብ ሰነዶች ማስረጃ ላይ በሙሉ ለማጥራት ብዙ ጥረት ከማድረጉ በተጨማሪ ተንቀሳቃሽ የምስል መረጃዎችንም በሙሉ ተለቅመዉ እንዲጠሩ ቀጫጭን ትእዛዞች ለሚመለከታቸዉ አካላት አስተላልፎአል፤ በመሆኑም የደህንነቱ መረብ ጌታቸዉ አሰፋ በሚንቀሳቀስበት እና በሚገኝበት አካባቢ ላይ ምንም አይነት ተንቀሳቃሽም ሆነ የፎት ግራፍ ቀረጻ እንዳይካሄድ ከፍተኛ ክትትል ያደረጋል፤ የብሄራዊ መረጃዉን አፋኝና ገዳይ ቡድን በቁንጮነት የሚመራዉ ጌታቸዉ አሰፋን ከካሜራ እይታ የመከላከል እና የመጠበቅ ሐላፊነት ማለት ግለሰቡን ከግድያ ሙከራ መከላከል ማለት ነዉ የሚል አቁዋም ያለዉን የደህንነት ብሂልን ተከትሎ ከፈተኛ ጥበቃ የሚደረግለትን ይህን ሰዉ በካሜራ ቀርጾአል የተባለዉ የጥበቃ አባል በሰሞኑ በደህነቱ ሐይሎች ተጠልፎ የደረሰበት አለመታወቁን ታማኝ ምንጮች ጠቁመዋል። በካዛንቺስ አካባቢ ከተወሰኑ የደህንነት አባላት እና ከህወሃት የአመራሮች ጋር የአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት በመሰለ ስፍራ ዉስጥ ተሰብሰበዉ የነበሩትን ጌታቸዉ አሰፋን ከስብሰባዉ ሲወጡ ጠብቆ በጥንቃቄ ፎቶ ሲያነሳ ታይቶአል የተባለዉ ጥበቃ በቁጥጥር ስር ከዋለ ወዲህ በተንቀሳቃሽ ስልኩ ዉስጥ በተደረገዉ ፈጣን ፍተሻ ላይ ምንም አይነት ምስል ባይገኝም የብሄራዊ መረጃዉ ከቴሌ ጋር ባደረገዉ የመስመር ስለላ መሰረት የጥበቃ አባሉ ፎቶ ግራፉን ካነሳ ወዲህ ምስሉን ወደ አልታወቀ አካል ማስተላለፉንና ከስልኩ ዉስጥ መረጃዎችን ማጥፋቱ በመረጋገጡ የጥበቃ አባሉ በደህንነቱ አካላት ትእዛዝ መሰረት ሊታፈን መቻሉን መረጃዎች አመልክተዋል። ይህ የጥበቃ ሁኔታን ተንተርሶ ከዚህ ቀደም ከነበረዉ የጥንቃቄ ዘይቤ ለየት ባለ መልኩ ነገሮች መቀየራቸዉን ግምት ዉስጥ ያስገቡ የመረጃዉ አባላት ጌታቸዉ አሰፋ በዚህ ወቅት ላይ በእጅጉ ያሰጋቸዉ አንዳች የደህንነት ጉዳይ ይኖራል የሚል ጥርጣሬ አጭሮባቸዋል፤ በአሁኑ ወቅት የደህንነት አባላቱ ዉስጥ ከፍተኛ አለመተማመን መፈጠሩን የገለጹልን ምንጫችን አያይዘዉ እነ ጌታቸዉ አሰፋ ብሄራዊ ደህንነት ከማስጠበቃቸዉ ይልቅ የራሳቸዉን ደህንነት በመጠበቅ ስራ ላይ ተጠምደዋል ሲሉ ተናግረዋል፤ ድል አሊትዮጵያ ህዝብ !! ( ጉድሽ ወያኔ )

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: