“ይህ ሁሉ ሰራዊት ሲጨፈጨፍ ምን ትሰሩ ነበር?” ሌ/ጄ ብርሃኑ ጁላ

በጎንደር ህዝብና በመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል በተካሄደው የተኩስ ልውውጥ 19 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲገደሉ 18ት ደግሞ መቁሰላቸው ባለፈው ሃሙስ በባህርዳር በሰፈረው የሰሜን ምእራብ እዝ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ወይም በተለምዶ አጠራር መኮድ በተደረገው ዝግ ስብሰባ ይፋ ሆኗል።

ይህን ተከትሎ በተደረገው የሰራዊት ግምገማ ስብሰባውን የሚመሩት የሰሜን ምእራብ እዝ አዛዥ ሌ/ጄ ብርሃኑ ጁላ ፣ “ ይህ ሁሉ ሰራዊት ሲጨፈጨፍ ምን ትሰሩ ነበር?” የሚል ጥያቄ በቁጣ ሲያነሱ፣ የሰራዊቱ አባላት ዝምታን በመመርጥ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
አዛዡ አክለውም፦ “ወታደሮቹ ሲደበደቡ ጋንታ መሪዎች ምን እርምጃ ይወስዱ ነበር?እነሱ ሲደበደቡ ዝም ብለው ያዩት ከጀርባቸው አንድ ነገር እንዳለ ያሳያልና እርምጃ ይወሰድባቸዋል” በማለት በጋንታ አመራሮች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱም ተናግረዋል።

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: