በሰሜናዊ የፈረንሳይ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በጩቤ ተወግቶ ተገደለ

በሰሜናዊ የፈረንሳይ ግዛት በምትገኘው ካላይስ የስደተኞች ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ በነበሩ ስደተኞች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት አንድ ኢትዮጵያዊ ደረቱ አካባቢ በጩቤ ተወግቶ ህይወቱ ማለፉን የዘገበው የድረ ገጽ ጋዜጣ የሆነው ላ ቮስ ደ ኖርድ ሌሎች ስድስት ስደተኞችም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል፡፡
ጋዜጣው የካላይስ አካባቢን ፖሊሶች በመጥቀስ እንደዘገበው የ37 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ ለሞት የተዳረገው ደረቱና ጀርባው ላይ በጩቤ በመወጋቱ ነው፡፡
የሱዳን፣የኤርትርና የአፍጋኒስታን ስደተኞች በቡድን ካሳለፍነው ሰኞ አመሻሽ ጀምሮ እስከ ማለዳው ሲደባደቡ መቆየታቸውን የጠቀሰው የድረ ገጽ ጋዜጣው አራት ሰዎች ጉዳት ማስተናገዳቸውንና አንደኛው ክፉኛ መጎዳቱን አውስቷል፡፡
ዛሬ ረፋድ ላይ በድጋሚ በተቀሰቀሰ ጸብ 200 ያህል ስደተኞች መሳተፋቸውንና ሁለት ስደተኞች ከፍተኛ ጉዳት ማስተናገዳቸው ተነግሯል፡፡
የካላይስ የስደተኞችን ጊዜያዊ መጠለያ በቅርቡ ፈረንሳይ ያፈረሰችው ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በዋናነት ብዙ ሺህ አፍሪካዊያን ስደተኞች እንደሚገኙበት ይታወቃል፡፡ስደተኞቹ በአብዛኛው ወደ እንግሊዝ ለመግባት አካባቢውን እንደመሸጋገሪያ እንደሚጠቀሙበትም ይነገራል፡፡

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: