ሰበር ዜና…. ሐገራችን ኢትዮጵያ በትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን የጎጥ ሐይል እጅ ከወደችበት ወቅት አንስቶ በገዢዉ ሀይል ላይ እንደዚህ ያለ ጭንቀትና ዉጥረት ተፈጥሮ አያዉቅም ለማለት ያስደፍራል!!

ህዝባዊ ተቃዉሞዎች ከድምጸትና ከመፈክሮች ዘለዉ መስዋትነት እየተከፈለባቸዉ ከመገኘት ባለፈ መልኩ መንግስት ተብዬዉ አጥቂ ህዝብ ደግሞ ተከላካይ ሆኗል።
አሁን ነገሮችን መቆጣጠሩ እጅግ የተሳነዉ ህወሃት በተጠንቀቅ የቆሙ የነጻነት ሐይሎች በሐገር ዉስጥ ያለዉን የአመጽ እንቅስቃሴ ተገን አድርገዉ የማያዳግም እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ የሚል ስጋት አስጠብቦታል።
በኦሮሚያ ምእራብ ወለጋ ከቤጊ( Begi ) እስከ ቶንጎ( Tongo ) እንዲሁም አሶሳ ( Asosa ) ዙሪያዉን የመከላከያ ሰራዊት እንዲሰማራ ከተደረገ የሰነበተ ቢሆንም በሐገር ዉስጥ የተቀሰቀሰዉን የዉስጥ አመጽ በማክሸፍ በወንጀል ላይ የሚገኘዉን የልዩ ሐይልንና የአጋዚን ቅጥረኛ ጦር ግዳጅ በመደገፍ መከላከያዉ ስለተሰማራ ህወሃት መራሹ ቡድን ከፍተኛ የሐይል እጥረት ላይ ወድቋል።
በተጨማሪ በሰሞኑ በጎንደር የተቀሰቀሰዉን ህዝባዊ አመጽ ተንተርሶ በሰሜኑ ክንፍ ጠርምሶ ይገባል ተብሎ በእጅጉ የተፈራዉን አርበኞች ግንቦት 7ን በተለይም በህወሃት መከላከያ ሰራዊት ዉስጥ አንዳርጋቸዉ እየተባለ የሚጠራዉን ክ/ጦር ለመቆጣጠር የመከላከያ ሰራዊት 5 ክ/ጦሮች በሰሜኑ እዝ ዉስጥ በአንድ ተቋጥረዉ የቃኘዉ ስለላ፣ የብረት ለበስ ( ሜካናይዝድ ) ፣ የእግረኛ ግንባርና ደጀን ፣ የአየር ሐይል ጊዜያዊ ስምሪት፣ የልዩ ሐይል፣ የአካባቢ ሚሊሻዎች ፣ የጸረ ሽብር ቡድን ባጠቃላይ ያለ የሌለዉ ሐይል ተሰማርቶ ይገኛል።
ህወሃት አለኝ የምትለዉ ይህዉ መከላከያዋ ድንገተኛ የሆኑ ማንነታቸዉ ያልተረጋገጠ መጠነኛ ጥቃቶች እያስተናገደ ሲሆን የሰሞኑን የህወሃት መከላከያ ሰራዊት ወታደራዊ ስትራተጂ እና አወቃቀር ተጠልፎ መዉጣቱን ከ25ተኛ ክ/ጦር አመራሮች የተገኘዉ ፍንጭ አረጋግጧል ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

Gudish Weyane's photo.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: