ከእውነቱ በማንኪያ፡- ወልቃይት ላይ ወያኔ በገዛ እጁ አርማጎዶንን እየጠራ ነው!

…የወያኔን የክስ መዓት አየህ? ከሊላይ ብርሃኔ ውጭ ሁሉም ተከሳሾች ከጥቂት ወራት በፊት በዳንሻ ላይ በነበረው ግጭት የታሰሩ ናቸው። የታሰሩበት ምክንያትም ሊላይ ብርሃኔ ከጎንደር ወደ ዳንሻ ሲሄድ በወያኔ ደህንነቶች በመታፈኑ ነው። ታፋኙ ከወልቃይት ኮሚቴ ጋር በቅርበት ሲሰራ የነበረ ሰላማዊ ወጣት መሆኑን ማንም ያውቃል። በዚህ ድፍረት የተቆጡት የዳንሻ ወጣቶች መንገድ በመዝጋት ከወያኔ ታጣቂዎች ጋር ባዶ እጃቸውን ለሁለት ቀናት ተፋጠው እንደነበር አይዘነጋም። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ዛሬ 254 ገፅ ክስ የቀረበባቸው ልጆች እንዲታሰሩ ያደረጉት ቄሶች መሆናቸው ነው። አዎ፣ መንገዱን ለማስከፈትና እልቂት እንዳይፈጠር በሚል ሰበብ ሀሳዊ የሃይማኖት አባቶች ወያኔን ከጭንቅ ለመገላገል ህዝቡን አታለው ሰልፉን ካስበተኑት በኋላ ንቁ የዳንሻ ልጆችን በደህንነቶች ታድነው እንዲታሰሩ አድርገዋል። የታሰሩት የወልቃይት አማሮች የኮሚቴው ደጋፊዎች እንጂ አባሎች አይደሉም። ሁሉም ግን በድፍረት አስተዳደሩን በማንነታቸው የማይደራደሩ መሆናቸውን የሚናገሩ ሰላማዊ ጀግኖች ናቸው።

እነኝህ ወጣቶችን በማሰሩ ወያኔ ቅርቃር ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። የወልቃይት ጠገዴ ህዝብና ሰፋሪው ትግሬ እንዲፋጠጥ እና መተማመን እንዲጠፋ አድርገዋል። አሁን ደግሞ ክሱ የባሰ ህዝቡን አስቆጥቷል። ባይገርምህ እነኝህን ወጣቶች ያሳፈነ ተድላ የሚባል የፋና ሆቴል ባለቤት እና የደህንነት ሰው (ዳንሻ ከተማ) ማንነቱ ባልታወቀ ሰው ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ በ6 በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል። ሟች ከ1987 ዓ.ም. ጀምሮ የደህንነት ስራዎችን ይሰራ ነበር። የመጀመርያው የሽፋን ስራው ሃኪምነት ሲሆን ቀስ በቀስ የዳንሻ ክሊኒክ ሃላፊ ሆኗል። ስንቱን የወልቃይት ንቁ ሰው በህክምና ሰበብ እንዳኮላሸ ፈጣሪ ነው እሚያውቀው። በመጨረሻ ላይ ባንድ ጀምበር ባለሆቴል ሆነ። ይህ ሰው ልጆችን በማሳፈን ብቻ አልቆመም ነበር። ይልቅ የትግራይ ተወላጆችን እየሰበሰበ ህገወጥ መሳሪያ የሚታጠቁበትን መንገድ ሲመክርና ትግሬዎቹም የወልቃይት ተወላጆችን “ወልቄ ጀግና የምትሉት ፉከራ የት ገባ? ይሄው ለቃቅመን ስናስገባቸው ምን መጣ?” እያሉ የእብሪት ፕሮፓጋንዳ እንዲያሰራጩ ያደርግ ነበር። ይህ ሰው በወልቃይቴዎች ጥርስ የተነከሰበት ነበር። ሞቱም በእብሪቱና በክፉ ድርጊቱ በተናደደ የአከባቢው ግለሰብ የተፈፀመ እንደሚሆን ይጠረጠራል።

የዚህን ሰው ሞት ተከትሎም ትግሬዎች በመደናገጥ ህወሓት እርምጃ እንዲወስድ ወትውተዋል። ህወሓትም መሃል ከተማ ላይ ከምሽቱ 2፡00 ላይ ስድስት ጥይት ተኩሶ የወገኑን ደም የመለሰውን ግለሰብ መያዝ ሲያቅተው ሴትና ህፃናትን በጀምላ ማሰር እና ማስፈራራት ቀጠሉ። ጀግናው ግን ሊገኝ አልቻለም። እንግዲህ ይህን ግለሰብ መያዝ ሲያቅታቸው ለዚህ ሁሉ ያበቁን የማንነት ጥያቄ እያሉ የተነሱት ናቸውና እነሱን ከናካቴው ማጥፋት አለብን ብለው ወሰኑ። ኮሚቴዎቹ ሰላማዊና ግጭቶችን የሚያወግዙ እንደሆኑ ቢያውቁም፣ የወንጀል ድራማ አቀናብረው 6 ቀንደኛ የኮሚቴ አባላትን ጎንደር ድረስ ሄደው ለማፈን ሞከሩ፣ ለባሰ ቅሌት ተዳረጉ። አሁን ደግሞ ከወራት በፊት ወዳፈኗቸው ወጣቶች ዞረው 254 ገጽ የፈጠራ ክስ ከምረውባቸዋል። ውጤቱ ምን እንደሚሆን አብረን እናያለን።

ነገር ግን ይህ ሂደት አንድ ነገር ፈጥሯል፥ ከእንግዲህ ትግሬና ወልቃይቴ እስከ ዘላለም እማይፋቅ ደመኝነት ውስጥ ገብተዋል። መላው የወልቃይት አማራ ትግሬን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንዲጠላ ተገዷል። እነኝህ ልጆች ካልተፈቱ የትግሬ ሰፋሪና ቅኝ ገዥ የህወሓት ካድሬዎች ፋታ አያገኙም። ህዝቡን በሃሰት አሸባሪ ብለው ማሰራቸውን እስካላቆሙ ድረስ ጀግኖቹ በሃቀኛ ሽብር ቁምስቅላቸውን እንደሚያበሏቸው አያጠራጥርም። እነሱ እየሰሩት ባለው ግፍ የወልቃይት ወጣት አክራሪ የአማራ ብሄርተኝነትን ገንዘቡ እያደረገ ነው። እድሜ ለእብሪታቸው ዛሬ ማንኛውም የወልቃይት ወጣት ከትግሬ ሰፋሪ ጓደኞቹ ጋር ሻይ መጠጣት እንኳ አቁሟል። ሁሉም በተጠንቀቅ በጥርጣሬ ይጠባበቃል። የወያኔ እብሪት ካላቆመ አርማጌዶን በወልቃይት ምድር መነሳቱ አይቀሬ ነው።”

ድል ለአማራ ሕዝብ!

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: