ብአዴን ከሽማግሌዎች ጋር ተወያየ- የጎንደር ሰልፍ ለ10 ቀናት ሳይራዘም አይቀርም – ግርማ ካሳ

በሰሜን ጎንደር አስተዳደር ፅ/ቤት ውስጥ ስብሰባ መካሄዱን ከስፍራው የደረሱ ዘገባዎች ይጠቁማሉ። የወልቃይት ኮሚቴዎች ፣የከተማው ህዝብ ፣ ከተለያዬ ቦታዎች የመጡ ወገኖች እንዲሁም የክልሉ መንግስት ወኪሎች በስብሰባው የተሳተፉ ሲሆን ፣ ከጎንደር ውጭ ታፍነው ስለተወሰዱት ኮሚቴዎች ጉዳይ ፤ የት እና በምን ሁኔታ እንዳሉ ፣ ወደ ጎንደር በአስቸኳይ እንዲመጡ፣ የእሁዱን ሰላማዊ ሰለፍ ፍቃድ እንዲያገኝ ማድረግ፣ የወልቃይት ጉዳይ የወልቃይት ወይም የጎንደር ነዋሪዎች ጉዳይ ሳይሆን የመላው የክልሉ ህዝብ ጉዳይ ስለሆነ በአማራው ክልል ስለ ወልቃይት ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በግልፅ እንዲጀመር ፣ የኮሎኔል ደመቀ ጉዳይ.. ….በዋናነት የተቀመጡ አጀንዳዎች እንደሆነ ምንጮች ይጠቁማሉ።

በዚህ ጉዳይ ላይ ጋዜጠኛ መሉቀን ተስፋው፣ ዘግይቶ የደረሰኝ ዜና በሚል በሶሻል ሜዲያ በለቀቀው ጦማር፣ የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባላት በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ዙሪያ ታፈነው የተወሰዱ የኮሚቴ አባላት፣ በአሥር ቀናት ዉስጥ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ለማድረግ እንደሚሞክሩ መግለጻቸውን ጽፏል።

በኢቢሲ፣ ሕወሃት እያከታተለ፣ በጎንደር የተነሳውን ተቃዉሞ ከሻእቢያ ጋር በማገናኘት፣ ተቃዉሞ ያሰማውን ህዝብ የሻእብያ አሽከር እያለ የንቀት ዘገባ ሲያሰማ እንደነበረ ይታወቃል። በዚሁ ስብሰባ የብአዴን ባለስልጣናት ለዚህ የኢቢሲ ዘገባ ማስተባባያ እንዲሰጡ በተጠየቁት መሰረት፣ ያንን ለማድረግ ፍቃደኛ እንደሆኑም ጋዜጠኛ ሙሉቀን ዘግቧል።

ሐምለ 17 ቀን እሁድ በጎንደር ከተማ ሊደረግ የታሰበውን ሰልፍ፣ አስተዳደሩ ለአሥር ቀናት እንዲራዘም ያደረገ ሲሆን፣ የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሕወሃት ከፍተኛ የሆነ ጫና እንደተደረገባቸውም ለማወቅ ተችሏል። አስተዳደሩ ሰልፉ እንዲራዘም ቢጠይቅም፣ ይሄ ሕግ መንግስታዊ መብት እንደመሆኑ፣ የሕዝብ ሽማግሌዎች መክረዉበት ካስፈለገ ህዝቡ ሰልፍ ሊወጣ እንደሚችልና ፣ ጉዳዩን በሕዝብ እጅ እንዳለ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ምንጮቹን ገልጾ አትቷል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: