ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የዐማራ ሕዝብ እሁድ በጎንደር ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል

በወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎች ላይ የሚደርሰውን አፈናና ግድያ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ እሁድ ሐምሌ 17 ቀን 2008 ዓ.ም. ለማካሔድ የአገር ሽማግሌዎችና የሕዝብ ተወካዮች ለከተማ አስተዳደሩ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ ጥያቄ አቅራቢዎቹ እንደገለጹት አርብ ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሰአት በኋላ አዎንታዊ መልስ እንደሚሰጣቸው ከከተማ አስተዳደሩ ተነግሯቸዋል፡፡
እሁድ ዐማሮች በሚያደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ እንደሚወጣ ብሎም በሕወሓት የሚደርሰውን አፈናና ግድያ እንደሚያወግዝ ሲሆን በጎንደር ታሪክ ታላቁ ሰላማዊ ሰልፍ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የዐማራው ሕዝብ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ የሚያደርገውን ሰልፍ በሰርጎ ገብ የወያኔ ሰዎች ችግር እንዳይፈጠርም ጥንቃቄ ተደርጓል ተብሏል፡፡ በጎንደር የተጠየቀው የሰላማዊ ሰልፍ ጥያቄ በምንም መልኩ ሊከለከል እንደማይችል አዘጋጆች አክለው ገልፀዋል፡፡ ‹‹የከተማ አስተዳደሩ በሕወሓት ጫና ሰላማዊ ሰልፉን ፈቃድ ቢከለክልስ ምን ዋስትና አላችሁ›› በማለት ለሰልፍ አዘጋጆች ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹እኛ የጠየቅነው ሰላማዊ ሰልፍ ነው፤ የከተማ አስተዳደሩ ሕወሓትን በመፍራት ሕዝቡን ይከለክላል የሚል እምነት የለንም፤ ካደረገው ግን ሥርዓት አልበኝነትን እንዲነግሥ ይሻል ማለት ነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በባህር ዳር፣ ደሴና ደብረ ብርሃን ከተሞች ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ኮሚቴዎች ተመርጠው እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተያያዘ በጎንደር የሚገኘውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ጨምሮ ወደ ማእከላዊ ተወስደው ከባድ የወንጀል ምርመራ እየተደረገባቸው ያሉትን የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ የዐማራ አመራሮች መበራከታቸው ታውቋል፡፡ ወደ ማእከላዊ የተወሰዱት የጥያቄ አቅራቢው አባላትና የወልቃይት ዐማራ ተወላጆች በቤተሰቦቻቸው ለመጠየቅ ቢሄዱን እስካሁን አልተፈቀደላቸውም፡፡

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: