የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢትዮጵያውያን ከአፋኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት እንዲተባበሩ ጥሪ አቀረበ

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር /ኦዴግ/ ከጎንደር ህዝብ ጎን እንደሚሰለፉ አስታወቁ። የጎንደር ህዝባዊ እንቅስቃሴ መሪዎች ትግላቸውን ከኦሮሞ ህዝባዊ እንቅስቃሴ ጋር እንዲያቀናጁና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከአፋኝ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል። በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (አዴግ) ሰኞ ሃምሌ 11 ፥ 2008 ባወጣው መግለጫ ህዝብ ለነጻነት፣ ለዲሞክራሲና ለመብት ትግል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዕመቃ እንደማያቆመው፣ በኦሮሚያ የቀጠለውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ አስታውቀዋል።
የጎንደር ህዝብ እንደ ኦሮሞ ወንድምና እህቶቹ የህወሃትን አግላይነት ለመታገል ተንቀሳቅሰዋል በማለት የቀጠለውን የኦዴግ መግለጫ የነጻነት ትግል ከድል በመለስ ምንም ሃይል እንደማይገታው አስገንዝቧል። የኦሮሚያና የጎንደር ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች የህወሃትን ፍጻሜ እንዲያመጡና የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ እንዲወጣ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ህዝባዊ እንቅስቃሴውን እንዲቀላቀሉ ኦዴግ ጥሪውን አቅርቧል።
በመላው ኦሮሚያ ለ8 ወራት በቀጠለውና አሁንም የጎንደር ህዝብ የጀመረውን ህዝባዊ እንቅስቃሴ፣ በሁሉም የሃገሪቱ ክልሎች እንዲቀጣጠል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ለፖለቲካ ሃይሎችና ለሲቪክ ድርጅቶችም ጥሪ አቅርቧል። የህወሃት 25 አመታት አገዛዝ እያበቃለት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የአፈናና የግድያ ስርዓት ቢቀጥል፣ ሃገሪቱ ወደ ቀውስ ታመራለች ሲልም ስጋቱን ገልጿል። ተቃዋሚዎችን መድፈቅ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነቱን ማስቀጠል፣ ኢፍትሃዊ የሆነው የሃብትና የመሬት ቅርምት፣ እንዲሁም ተቋማዊ የሆነው ዘረፋና የሃገሪቱ ተቋማት እየተዳከሙ መሄድ በቶሎ ካልተገታ ኢትዮጵያን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ይከታታል ሲልም አሳስቧል።
የኦሮሞ ዴሞክራዊያዊ ግንባር (አዴግ) በመጨረሻም ለጎንደር ህዝብ ያለውን ሙሉ ድጋፍ በማረጋገጥ የንቅናቄው መሪዎች ትግላችንን በጋራ እናስተባብር ሲል ጥሪ አቅርቧል። ሌሎች ኢትዮጵያውያንም የኦሮሚያንና የጎንደርን ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርቧል። ከህወሃት አገዛዝ የኢትዮጵያን ህዝብ ነጻ እናውጣ በማለትም መልዕክቱን አስተላልፏል።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: