እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ተፈረደባቸው

-ኤርትራ ድንበርን በማቁዋረጥ አርበኞች ግንቦት 7ን ሊቀላቀሉ ሲያመሩ ተይዘው የሽብር ክስ የቀረበባቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።
ተከሳሾ ብርሃኑ ተክለያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማው እና ደሴ ካሳይ ሲሆኑ፣ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ የመሰረተባቸውን ክስ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማስረዳቱ የጥፋተኝነት ፍርድ መስጠቱን 14ኛ ወንጀል ችሎት ገልጹዋል።
ተከሳሾች 141 መከላከያ ምስክሮችን አስመዝግበው እንደነበር አስታውሶ፣ በተከሳሾች በኩል የተመዘገበው ጭብጥ ግን የፈጸሙት ተግባር ወንጀል ነው ወይስ አይደለም በሚል እንዲመሰክሩ በመሆኑና አንድን ተግባር ወንጅል መሆን አለመሆን በህግ እንጂ በምስክር ስለማይረጋገጥ የምስክሮች መሰማት አግባብነት ስለሌለው መታለፉ ተወስቱዋል።
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ቅጣት አስተያየት ለመቀበል ለሀምሌ 22/2008 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቱዋል።
ተከሳሾች ጥፋተኛ የተባሉበት የህግ ክፍል የጸረ ሽብር አዋጅ 652/2001 አንቀጽ 7(1) ን መተላለፍ የሚል ነው።

Belay Manaye's photo.
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

One Response to እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ ተፈረደባቸው

 1. በለው! says:

  ህወአት ድሮ ጫካ የገባሁት ሕዝብን ከጨቋኝ ሥርዓት ነጻ ለማውጣት፡ ከሽምቅ ውጊያ በቀር ሌላ አማራጭ ስላልነበር ነው ብለውን ነበር።
  ** ለዚህም ስኬት ተቋማት ማፍረስ፡ ባንክ መዝረፍ፡ የገበሬ ጎተራ መገልበጥ፡ የዕርዳታ እህል ከድሃ ሕፃናት ጉሮሮ ቀምቶ መሸጥ ሁሉ ክብርና ሞገስ ሆነው በራዕይ መልክ መሙስና መር ልማታዊ መንግስት ሆኖ ከትውልድ ትውልድ በዱላ ቅብብል ሥልጣን በቤተሰብና በጎጥ ተደራጅተው በኀብረት አመራር? (አመራር በደቦ!) በአንድ የፖለቲካ ጥላ ሥር እያንዳንዱና ሁሉም ተጠልሎ,,,,ተከልሎና ተከልክሎ እንዲኖር ተጠርንፏል።

  *** እንግዲህ እነኝህም ሕፃናት የህወአትን ፈለግ ተከትለው ቢሄዱ ነውር የሆነው ትግሬ አለመሆናቸው ነውን? ፲፬ ዓመት ግራና ቀኝ ሲወጋን ሲሰልለን የነበረውን ትህዴን ድንኳንና በሬ ጥሎ በዕልልታ በተኩስ ከኤርትራ የተቀበለው ኢህአዴግ ሆደ ሰፊነቱ ት ሄደ?
  * በአርግጥ ዴሞክራሲ ስለሠፈነ ታጋይ አያስፈልግም? በእርግጥ በላተኛና ተመልካች ተመጣጥኗል? ፭፻፵፯ የፓርላማ መቀመጫ አንድ ተፎካካሪ ለየት ያለ አመለካከት ያለው ዜጋ ሳይመረጥ ቀርቶ ነው? አሁን ያለው ቡድን ብቻ እንዴት ፍፁማዊ ልማታዊ ሆነ ይህ እንኳን ጫካ ጠላት ቤት ማስኮብለል ምላጭ አያስውጥም?
  ** አንተ እነኝህን የዋሆች ክፉን ያስመለከትካቸው ወሮ በል አስደንባሪ አጋንንት ወጣትነታቸውን ሳትበላ ለቤተሰብና ለሀገር ጠቃሚና አገልጋይ ይሆኑ ዘንድ ቶሎ ፈተህ ልቀቅ በስመ አብ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ ሥም ሶስቱንም ጠርተህ ፍታ!ፍታ!ሌሎችንም አስባቸው ሰውራቸው እግዚዎ ፈጣሪያቸው ሕዝብህን አድን!አሜን!

  Like

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: