ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን ፍርድ ቤት ለማቅረብ የሚደረገው እንቅስቃሴ ከህዝቡ ጋር የተደረሰውን ስምምነት የሚጥስ ነው ተባለ

የኮሚቴ አባላቱ ለኢሳት እንደገለጹት የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንም ሆነ በአጠቃላይ የታሰሩትን የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ የኮሚቴ አባላትን ጉዳይ የሚከታተሉ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ኮሎኔሉ ወደ ትግራይ ተላልፈው እንደማይሰጡ እንዲሁም ሁኔታዎች ሲረጋጉ ኮሎኔሉና ሌሎችም የኮሚቴ አባላት ለሽማግሌዎች ተመልሰው እንደሚሰጡ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር። ኮሎኔሉ ራሳቸው ሽማግሌዎች በተስማሙት መሰረት ስምምነቱ ተግባራዊ እንዲደረግ መጠየቃቸውን የተናገሩት የኮሚቴ አባላቱ፣ አሁን ግን ኮሎኔሉ ጎንደር ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሃምሌ 22 ቀን 2008 ዓም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ የሚል መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል።
ሽማግሌዎቹ ዛሬ ከኮሎኔሉ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን፣ በወልቃይት ጠገዴና በጎንደር ህዝብ ላይ ጉዳት ያደረሱትን በህግ ለመክሰስ፣ ታፍነው የተወሰዱ የኮሚቴው አባላት ለሽማግሌዎቹ ተመልሰው እንዲሰጡ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ኮሎኔል ዘውዱ ከፍተኛ ጀብዱ መፈጸማቸውን የሚያወሱት የኮሚቴው አባላት፣ ኮሎኔሉ በሰላም ከተኙበት ለማፈን ሙከራ ያደረገው የህወሃት የሽፍታና ተላላኪ ቡድን እርሳቸውን ለመክሰስ ምንም የሞራልም የህግ ልእልናም ስለሌለው የጎንደርም፣ የአማራም ሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህ ሃይል ከድርጊቱ እንዲቆጠብ ማድረግ አለበት ይላሉ። ስምምነቱ ኮሎኔሉንና የኮሚቴ አባላቱን መልሶ ለሽማግሌዎች ለማስረከብ በመሆኑ ስምምነቱ መፈጸም አለበት ብለዋል
በበየዳ፣ በዳንሻ እና በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩት ህዝባዊ ተቃውሞች ከመልካም አስተዳደርና ገዢው ፓርቲ ከሚከተለው የዘረኝነት ፖሊሲ ጋር እንደሚያያዝ የኮሚቴው አባሉ ተናግረዋል። 

 

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: