የሰሜንና አካባቢዉ የዉስጥ አርበኞች የቁርጥ ቀን ጥሪ!!

ይድረስ ለመላዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ!! እኛ በሐገራችን ኢትዮጵያ ከሁሉም ማሕበረሰብ ጋር ተስማምተን ተከባብረን ለመኖር የተፈጠርን ከአንዲት የእናት ምድር ምድረ ከርስ የተፈለቀቅን እርስ በእርሳችን ለዘመናት የተከባበርን አማራዎች፣ ኦሮሞዎች፣ ቤንሻንጉልና፣ ኦጋዴኖች፣ ጉራጌዎችና ትግሬዎች የተለያዩ ህብረ ቀለማት የልዩነት ዉበቶች ነን ። እኛ ጥቂቶች የምንመስል በነብር ዥንጉርጉርነት የምንገለጽ አንዳችን ለአንዳችን የምንቆስልና የምንደማ! ስንነካ እንደ አራስ ነብር የምንቆጣ! አናብሶች! ኢትዮጵያዊያኖች ነን!! እናንተ የምትሞቱለት ፓርቲ እንጂ ህዝብና ሐገር እንደሌላችሁ ጠንቅቃችሁ እወቁት እኛም ጠንቅቀን አዉቀናል! በሁለታችን መካከል ትልቅ ልዩነት ተፈጥሯል!~ እርሱም እምነት ነዉ! ይህ እምነት ለእናንተ የመኖር ዛሬን የማደር ፍላጎት ሆኖ አግኝተነዋል! ለእኛ ግን እምነት ያ እናዳልሆነ ተረዱት!! በእኛ እምነት ዉስጥ ትዉልድ አለ! አርቀን የምንመለከተዉ ትዉልድ! ያ ትዉልድ ዛሬ ልብላ ዛሬ ልጥገብ የሚል ሆድ የለዉም! ያ ትዉልድ በሚቀጥለዉ የተረካቢነት ምሕዋር ዉስጥ እራሱን ለማኖር የእኛን የዛሬ ማንነት አጮልቆ የሚመለከት ዛሬ በእናንተ እንደ አልባሌ የሚታሰር፣ የሚገደል የሚሰድደ ጨቅላ ትዉልድ ነዉ! ያ ትዉልድ ከኦሮሞ፣ ከአማራ፣ ከአፋር፣ ከቤንሻንጉል፣ ከጋምቤላ፣ ከትግሬ፣ ከጉራጌ ከሁለመናችን የተከፈለ የደምና የስጋ ፍልቃቂ የኢትዮጵያዊነት ነጽብራቅ ነዉ። ትናንት ኦሮምን ስትገሉ አማርን የምትገሉ አልመሰላችሁም ነበር! አማራን ስትገሉ ኦሮሞን የምትገሉ አልመሰላችሁን ነበር! ቤንሻንጉልን ስትጭፈጩ እንዲሁ ሌላዉን የምትጨፈጭፉ አልመሰላችሁም ነበር! የአንዱ ሐዘን ሌላዉ ደም ዉስጥ እንዳለ ለማወቅ አልፈለጋችሁም ነበር! ኢትዮጵያዊ ሁሉ የለቅሶ ቤት ድንኳን ዉስጥ ሲገባና ለቅሶ ሲቀመጥ ብሔር እንደማይጠይቅ ፈጽሞ አልተገነዘባችሁም የአንዱ ሐዘን የሌላዉ እንደሆነ አልገባችሁ ሊገባችሁም አትፈልጉም! በደላችሁ ሲደራረብ የእኛምዝምታችን ጣራ ሲደርስ ቂም የሚቋጥርባችሁ አልመሰላችሁም ነበር! ትልቅ ስህተት ደጋግማችሁ ሰራችሁ!! እንናተ የዘንዶዉ ደም የነካችሁ የህወሃት አባላቶች በተለይም ተለጣፊ ጭፍሮች ኦህዴድ እና ብአዴን የመሳሰላችሁት፦…… እንዲሁም የህወሃት የመከላከያ ሰራዊት አባላቶች ሁላችሁ….አሁን ሰአቱ አልቋል ! ከእንዲህ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ሁሉ ከህወሃት እርሱም፦ በትግሬ ስም ከተቋቋመዉ የግፈኞች ስብስብ ጋር የተሰለፈ ሁሉ ደሙ ደመ ከልብ የሚሆንበት ወቅት ላይ ደርሰናል!! በዚህ ወሳኝ ወቅት ላይ የመከላከያ ሐይል የምትባሉ ሁሉ ከህዝብ ጎን እንድትቆሙ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ትጠየቃላችሁ!! የመከላከያ እና የፖሊስና ሰራዊት እንዲሁም የልዩ ሕይል እና የአካባቢ ሚሊሻ ሌላም ሌላ የተባላችሁ ሁሉ ዘር ቀለም ቋንቋ ሐማኖት ሳይለያችሁ ዉስጥ ለዉስጥ ተደራጁ ተነጋገሩ ተመካከሩ እና እራሳችሁን ለቁርጡ ቀን አዘጋጁ ወደ ጠላት እንጂ ወደ ህዝብ መተኮስ እንዳትሞክሩ!!! እንዳታስቡ!!! ወደደም ጠላ ነገ ህወሃት ይሄዳል እናንተና እና ቤተሰቦቻችሁ ግን ከእኛ ጋር አብረን እንዘልቃለን እና አደራ…. ደም አንቀባባ!! የሰሜን እና አካባቢዉ የዉስጥ አርበኞች፦ የቁርጥ ቀን ጥሪ!! ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! ! ( ጉድሽ ወያኔ )

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: