የህወሃት ብሔራዊ መረጃ በመሐበራዊ የመገናኛ ዘርፎች ላይ የሚያደርገዉን አፈናና ክትትል በተመለከተ የጥቂት ወራቶችን ሪፖርት ለሚመለከተዉ

99743-esat-radio1

የህወሃት ብሔራዊ መረጃ በመሐበራዊ የመገናኛ ዘርፎች ላይ የሚያደርገዉን አፈናና ክትትል በተመለከተ የጥቂት ወራቶችን ሪፖርት ለሚመለከተዉ አካል አስተላልፏል።
በዚህም መሰረት የብሔራዊ መረጃዉን መድብለ ሪፖርት አጠርና ጠቅለል ባለ መልኩ ለሚመለከታችሁ ሁሉ ለማድረስ እንሞክራለን…
ኢሳትን 24 ሰአት ከማሳደድ ይልቅ ቃናን 24 ሰአት ማንጎድጎድ ስኬታማ ዉጤት እያመጣ ነዉ። ያለዉ የብሔራዊ መረጃዉ በተያያዘ መልኩ የተለያዩ የመሐበራዊ የመገናኛ አዉታሮችን ማለትም እንደ ዘሐበሻ የመሳሰሉ አደገኛ የተባሉትን ድህረ ገጾች ለማዳከም እና ለማጥፋት ተጨማሪ የበጀት እቅዶችን ዘርግቷል።
የብሔራዊ መረጃ ወንበድዉ ክፍል የኢትዮጵያ ህዝብ በብዛት ትኩረቱን ወደ ቃና ቴሌቪዥን እያዘነበለ እንደሚገኝና ኢሳትን እና ተዛማጅ የመረጃ አዉታሮችን የማዳመጡ እና የመከታተሉ ሁናቴ እንዲባረድና እና እንድጠፋ የተደረገ ሲሆን ይህ እንቅስቃሴ ስኬታማ ዉጤት እያመጣ ነዉ ይላል::
ይህ ብሐራዊ መረጃ ቃናን የመሰለ አደገኛ ህዝባዊ ጠላት በሐገራችን ላይ ተክሏል። ከመረጃ ክፍሉ አስገራሚዉ ተዉኔተ ሪርት ዉስጥ ቃና በሐገራችን ላይ ሊያስከትል የሚችለዉ አሉታዊ ተጽእኖ በማላገጥ መልኩ ዳሶታል።
እንደ ሪፖርቱ ከሆንበ ለምሳሌ የሐሰት ቋት ስርጭት ክፍሉ ኢቢሲ ላይ ሊደርስ የሚችለዉ የዉድቀት አደጋ ሲሆን ይህዉም የማስታወቂያ እና የፕሮፓጋንዳ በተለይም ህወሃታዊ ድሰቶች ኪሳራ ላይ እንደሚወድቁ ሲብራራ አዉራ የማስታወቂያ ድርጅቶችም ፊታቸዉን ወደ ቃና እያዞሩ መሆኑ እንዲሁም የልማታዊ አርቲሶችን ቅሬታ በተመለከተ ጥቂት ተብሏል።
ነገር ግን የብሔራዊ መረጃዉ ኢቢሲን በተጭማሪ በጀት እና በድጎማ ማቆየትን እንደ መፍትሄ ሲያቀርበዉ ልማታዊ አርቲስቶቹን በተመለከተ ከቃና ጋር በመተባበር የትርጉም ድምጽ አገልሎት ላይ እንዲሳተፉ በሚል መልኩ ቀልዶባቸዉ ያልፋል የዚህ የብሔራዊ መረጃዉ እቅድ እንደሚያመልክተዉ ከሆነ በቅርቡ ከልማታዊ አር..ቲስቶቹ መካከል የሰራዊት ፍቅሬን እና የሙሏለምን ድምጽ በቃና ተከታታይ ድራማ ላይ እንደምናደምጠዉ ተስፋ አለን። የለቅሶ ዉጤት ነዉ!!!
ብሐራዊ መረጃዉ ተንኮለኛነቱን በማጉላት ረገድ ኢሳትንና መሰሎቹን በከፍተኛ ሁኔታ ለማዳከምና አዉራ ተወካዮችን በተለያየ መንገድ በማጥቃትና እና ከጨዋታዉ ለማውጣት . . . .ስም በማጥፋት፣ ቤተሰቦቻቸዉን በማነጋገርና በማሰር፣ እንዲሁም በድርድር፣ በማባበል፣ በቤተሰቦቻቸዉ ላይ ኢኮኖሚያዉ ተጽኖ በመጣል የሚከወኑ የግፍ አፈጻጸሞች በዉስጡ ይገኙበታል።
የአፋኙ መደብ.. ብሔራዊ መረጃ በብዙ ሐገራት ተወዳጅ ያልሆነዉንና የስንፍና ቫይረስ ስርጭቱን ” የቃና ቴሌቭዥን “በኦሮምኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ለህዝብ እንዲተላለፍ በማድረግ ኢሳት ላይ እየተተገበረ የሚገኘዉን የሚዲያ አፈና ዘዴ የነጃዋር መሐመድ የድካም ዉጤት በሆነዉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ላይ ለመፈጸም በጥብቅ እየሰራ ለመሆኑ ሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።
ዉድ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በሙሉ ይህ የወንጀለኛዉ የብሔራዊ መረጃ መዋቅር ከኢስት እስከ ፌስ ቡክ ድረስ የተዘረጋ የመጨረሻ መፍጨርጨር መሆኑን እንድትገነዘቡ እያሳሰብን አቀጣዩ በፌስ ቡክ ላይ የሚያካሐዱትን ተራ የአፈና እንቅስቃሴ ለመመልከት እንሞክራለን፡፡
ድል ለኢቶጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: