ሆላንድ ካር የመኪና መገጣጠምያ ፋብሪካ ባለቤትን በፖሊስ

ሆላንድ ካር በሁለት መቶ ቋሚ ሰራተኞች ስራውን ጀመረ።
– ኢንጅነር ታደሰ ተሰማ ዓለሙ የውጭ ሀገር ስራቸውን ትተው ቦሌ መንገድ ሸዋ ዳቦ ቤት ፊት ለፊት የሚገኘው ጌቱ ኮሜርሻል ህንፃ ስር የድርጅታቸውን ቢሮ እና ሽያጭ ክፍል ሞጆ እና ታጠቅ አካባቢ ደግሞ የመገጣጠምያ ፋብሪካውን ከፈቱ።
– ድርጅቱ ስራውን የጀመረው እኤአቆጣጠር 2005 ዓም ሲመሰረት ´´ትረንቶ ኢንጂነሪንግ´´ እና ´´ኢትዮ-ሆላንድ´´ ኩባንያ በሽርክና የላዳ መኪናዎችን ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ነበር።
– እኤአቆጣጠር 2007 ዓም ላይ ´´አባይ እና ሸበሌየተሰኙ መኪናዎች ገጣጥሞ ከአምስት ዓመት ዋስትና ጋር ለገበያ አቀረበ፣
– በ2009 እኤአቆጣጠር ሆላንድ ካር የ2009 ዓም የመላው አፍሪካ የንግድ ፈጠራ ሽልማት አሸናፊ ሆነ
– በቀጣይ ዓመታት ድርጅቱ ስራውን ለማስፋፋት የካፒታል እጥረት ስለገጠመው እና የስራ ማስኬጃ ገንዘብ በተመረቱት መኪናዎች ላይ በመያዙ ብድር ከባንክ እንዲሰጠው ጠየቀ መንግስት ግን ከማበረታታት ይልቅ መንገዱን ዘጋበት፣
– እኤአቆጣጠር ሚያዝያ 16/ 2013 ዓም አውራምባ ታይምስ እና ሪፖርተር ኢንጅነር ታደሰ ተሰማ በኢንተር ፖል እንዲያዙ እንዲደረጉ የሚል ዜና አሰራጩ በመቀጠል ድርጅቱ ከገበያ እንዲወጣ ተደረገ።

2/ የፈረንሳዩ ፔጆ መኪና መገጣጠምያ በውቅሮ፣ትግራይ በሪባን
===================================
– ትናንት ሰኔ 25/2008 ዓም የኤፈርት አንዱ የሆነው መስፍን ኢንጂነሪንግ ውቅሮ ትግራይ ላይ የፔጆ መኪና መገጣጠምያ ፋብሪካ በሪባን ተመርቆ ሥራ መጀመሩን ፋና አስታወቀ።
– ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረቁት የተባለው ፋብሪካ በ25 ሚልዮን ብር የተመሰረተ እና በዓመት 1200 መኪናዎች ያመርታል ተብሏል።

ማጠቃለያ
=========
አገር በቀል ካምፓኒዎችን ማበረታታት እና ቢያንስ በብድር ማገዝ የጤነኛ መንግስት ሥራ ነው። ከስድስት ዓመታት በፊት በአሜሪካ በተከሰተው የምጣኔ ሀብት ቀውስ ላይ ግዙፉ የአሜሪካ ኩባንያ ´´ጀነራል ሞተርስ ´´ የገንዘብ እጥረት ስለነበረበት ፈድራል መንግስት በቀጥታ ደጉሞት ነበር። ሆላንድ ካር የጠየቀው ድጎማ ሳይሆን ብድር ነበር።ሆኖም ግን ማግኘት አልቻለም።የፈረንሳይ ፔጆ ግን ከመስፍን ኢንጅነሪንግ ጋር ተጠግቷል እና ብድር ይፈቀድለታል።ለጥሬ ዕቃም ሆነ ለወደብ ትራንስፖርት ባያመችም ውቅሮ ላይ ተከፍቷል።እንዲህ ነው ነገሩ። እሰይ ትግራይ ፋብሪካ በፋብሪካ ሆነች! እም!

ከስር የሚታየው ፎቶ የሆላንድ ካር መስራች እና ባለቤት ኢንጅነር ታደሰ ተሰማ ናቸው።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: