ሰበር ዜና… ህወሃት በሰሜኑ ግንባር ተጨናንቋል

በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በምእራብ ትግራይ ሂሞራ በታች የማይካድራ ነዳጅ ማጠራቀሚያ አካባቢና እስከ ሰቲት ሁመራ እንዲሁም ጉናና ኡማህጂር ምስራቅ ትግራይና ዓዲ ግራት ድረስ የተሰማራዉ ከተለያዩ ክፍለ ጦሮችና ልዩ ሐይል እንዲሁም አካባቢ ሚሊሻዎች ተወጣቶ በስምሪት ላይ የሚገኘዉ የጸረ ሽብር ቡድን ወደ ግንባር እንዲሰማራ ባለመ መልኩ እየተበተነና እየተሰባጠረ እንደሚገኝ ታማኝ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል።
ይህዉ የጸረ ሽብር ቡድን በተለይም ከደረሰበትና እየደረሰበት ከሚገነዉ ድንገተኛ ጥቃት ምክንያት እጅግ በመመናመኑና በመዳከሙ ለስምሪት የአካባቢዉ ክፍለ/ጦሮች እንዲተኩ የተወሰኑ ሲሆን ከላይ የተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በአካባቢዉ ላይ ከሚደረገዉ ወታደራዊ መሯሯጥ የተነሳ ስጋት ስላደረባቸዉ አካባቢያቸዉን ወደ መልቀቁ ደረጃ ሊሸጋገሩ እንደሚችሉ እማኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።
የህወሃት አዲስ ምልምልና ቅጥር ወታደሮች በመክዳት ምክንያት ከፍተኛ አደጋ እያስከተሉ በመምጣታቸዉ ወደ ደጀን ጦር የሚደረገዉ ዝዉዉር ከሰቲት ሁመራ ጀርባ ሲካተቱ ነባሮች በስምሪት እና ጸረ ሽብር ስምሪቱን እንደቆጣተሩ ሆኗል።
በሰሜን ጎንደርና በምእራብ ይትግራይ አካባቢዉ ተሰማርተዉ የሚገኙት 24ተኛና ክ/ጦሮች ከ 25ተኛ ክ/ጦር ጋር ቅይጥ ብረት ለበስ ሜካናይዝድ በማደራጀት ይጥምር ዉህድ የሚመስል ስልታዊ ክንዉን እያደረጉ ሲሆን ለዚህ ያለመረጋጋትና የመበታተን ጦስ ዋነኛዉ ምክንያት በየእለቱ በሰራዊቱ ላይ የሚደርሱ አነስተኛ ጥቃቶች እና የዉስጥ አርበኞች የፈጠሩት ጫና በአንኳርነት ተጠቃሽ ከመሆኑ በተጨማሪ የኢትዮ ኤርትራ የጦርነት ስጋት የፈጠረዉ ትርምስ በራሱ የተያያዘ መጨናነቅ መፍጠሩን ባሳለፍነዉ ሳምንት ከሰሜኑ ግንባር ተነጥለዉ በጎረቤት ሐገር በተጠለሉ የም/መቶ አለቃ ደጀኔ ጥላሁን እና የወታደር በኩር ገ/ስላሴ ለታማኝ ምንጮቻችን ተናገረዋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

 Aseged Tamene Picture
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: