ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በእንግሊዝ ፖሊስ ተያዙ

በእንግሊዝ ፖርትስማውዝ ፖሊስ 28 ስደተኞችን መያዙን አስታውቋል፡፡ከስደተኞቹ መካከል ሁለት ሴቶችና አንድ ህጻን እንደሚገኝ የዘገበው የእንግሊዙ ዴይሊ ሜይል የስደተኞቹ ዜግነት 11 ኤርትራዊያን፣10 ሱዳናዊያንና ሰባት ኢትዮጵያዊያን ነው ብሏል፡፡
ስደተኞቹ በዕቃ መጫኛ መኪና ተጭነው ሲጓዙ ከቆዩ በኋላ ለመጸዳዳት በመውረዳቸው ለእይታ በመጋለጣቸው በቁጥጥር ስር ለመዋል በቅተዋል ተብሏል፡፡በሞባይል እንደተቀረጸ የተነገረለት የቪዲዩ ምስልም ስደተኞቹ ከፖሊስ ለማምለጥ ሲሯሯጡ ያሳያል፡፡የእሳት አደጋ መኪኖችና አምቡላንሶችም በብዛት ወደ አካባቢው መድረሳቸውን ቪዲዩው አመላክቷል፡፡
የአይን ምስክሮች ስደተኞቹ ለማምለጥ ፖሊስ እነርሱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ያደረገው ትንቅንቅ፣የአምቡላንሶቹና የእሳት አደጋ መኪኖች ጩህት ትልቅ ቀውስ የተፈጠረ አስመስሎት ነበር ብለዋል፡፡
ፖሊስ አንድ ስደተኛ በመጎዳቱ ለሆስፒታል መዳረጉን በመጥቀስ ህጻኑ ለማህበረሰብ አገልግሎት ሰጪ ተቋም መሰጠቱን አስታውቋል፡፡

Aseged Tamene pictur

source: dailymail.co.uk

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: