በአዲስ አበባ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ መስፋፋቱ ተነገረ

አዲስ አበባን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ከሁለት ሺህ በላይ ሰዎች መጠቃታቸውንና በትንሹ 19 ሰዎች መሞታቸውን ተመድ ገልጿል። የበሽታው ስርጭት እየተባባሰ እንዳይመጣም ከፍተኛ ስጋት አለ።

አስታውሳለሁ፤ የዛሬ አምስት ዓመት አካባቢ በዚምባቡዌ ኮሌራ ተከስቶ ከ40 በላይ ሰዎች በመጠቃታቸውና 17 ሰዎች በመሞታቸው እነ ቢቢሲ ሳምንቱን ሙሉ ነበር በዜና፣ በሪፖርታዥና በውይይት….ስለዚሁ ጉዳይ ሲያኝኩ የሰነበቱት። የሙጋቤ ሀገር ነዋ!
እነሆ እነ “ምን ልታዘዝ?” ሀገር ውስጥ ግን 2ሺህ ሰው መጠቃቱና ካሁኑ 19 ሰው መሞቱ በተመድ እየተነገራቸው የቁራጭ ዜና ያህል እንኳ ሚዛን አልደፋላቸውም።

–ይህ ብቻ አይደለም፤ እንደ ዚምባቡዌ፣ ቡሩንዲ.. በመሣሰሉ በራሳቸው በቆሙ ሀገራት ሕዝባዊ ተቃውሞ ተቀስቅሶ 20 እና 30 ሰው ሲሞት ለስንት ቀናት እንደሚያራግቡት እንመለከታለን። በኦሮሚያ ክልል ሕዝባዊ ተቃውሞውን ተከትሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ 400 ሰዎች እንደተገደሉ እነ ሂዩማን ራይትስ ዎች ሰሞኑን ያወጡት መግለጫ ግን ከቁራጭ ዜና አላለፈም።

Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: