አዲሱ የ40/60 ኮንዶሚንየም የማስተላለፊያ ዋጋ ጭማሪ ጥናት የ60% በላይ ጭማሪን ይጠበቃል!

የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፤ የአ.አ. ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር በጋራ ባጠኑት የዋጋ ማሻሻያ ጥናት ለአንድ ካሬ ሜትር በምዝገባ ወቅት ከተተመነው የብር 2,100 ጭማሪ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ይገልፃል።

በዚህ ስሌት መሰረት የ40/60 የቤቶች ግንባታ በ2004 ዓ.ም. ሲጀመር ለአንድ ሜትር ካሬ እንዲከፈል የተወሰነው፤ ለባለ አንድ መኝታ ከ2289 ብር ወደ4389 ብር ለባለ ሁለት መኝታ ከ3300 ብር ወደ5400 ብር ለባለ ሦስት መኝታ ከ3860 ብር ወደ 5960ብር የቤት እድለኞች እንዲከፍሉ ይገደዳሉ።

ለጭማሪው እንደ ምክንያት የተጠቀሱት የግንባታ ቁሳቁስ ዋጋ መጨመር፣ የሠራተኛ ደሞዝ፣ የመሬት ዋጋ፣ የውሃ፣ የመብራት፣ የሕንጻ ዲዛይን ዋጋ መናር ናቸው።

ከከንቲባው ጠረቤዛ ላይ የሚገኘው የዋጋ ክለሳ ጥናት ከፀደቀ በምዝገባ ወቅት የነበረው የቤቶች ዋጋ ከ162,000, 250,000 እና 386,000ብር ዋጋው በአማካኝ ከ60% በላይ እንዲያሻቅብ ያደርገዋል።

ከ165ሺ በላይ ለተመዘገበት ይህ የ40/60 የቤቶች ግንባታ ፕሮግራም በሦስት አመት ውስጥ አንድም ቤት ለእድለኞች ማስተላለፍ አልተቻለም።

 
Advertisements

About Aseged Tamene
Your rights are your security. When you, 'give up your rights for security", it's not security you get, but slavery.'

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: